መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር

ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር

ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ መሥራች አባላት ሐምሌ 13 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በሕጋዊ መንገድ ተመሠረተ።

ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር፦ ራዕይ እና ተልዕኮ

ራዕይ

አካባቢያችን እና ማኅበራዊ ዕሴቶቻችን በአግባቡ በመጠበቅ በ2025 የአባላትን የገቢ ደረጃ በማሳደግ በምስራቅ አፍሪካ ሞዴል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር መሆንመሆን

ተልዕኮ

ለአባላት አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የፋይናስ አገልግሎቶችን በማቅረብ፣ እንዲሁም ብቁ ግብአቶችን በማሟላት የኅብረት ሥራ ማኅበር መዋቅራዊና ኢኮኖሚያዊ ቅንጅት በመፍጠር፤ እንዲሁም አካባቢያዊ፣ ማኅበራዊ እና የአየር ንብረትን በአግባቡ በመንከባከብ አረንጓዴ ልማትን በማፋፋት እና ታዳሽ ኃይልን በመጠቀም የአባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

መደበኛ ቁጠባ

የቁጠባ መጠን ብር በትንሹ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ወይም የገቢውን 15% ያህል ነው። ይህም እያንዳንዱ አባል በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ቁጠባውን መቶጠብ ይኖርበታል። የቁጠባ ወለዱም 7% ነው።

የጊዜ ገደብ ቁጠባ

የማኅበሩ አባል የሆኑ ወይም ያልሆኑ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከ6 ወር በላይ እና ከብር 3000 (ሦስት ሺህ ብር) ጀምሮ የሚቆጥቡበት ሂሳብ ሲሆን፤ እንደተቀማጩ የገንዘብ መጠን እና ከሚቀመጥበት ጊዜ መነሻ ተደርጎ ከ9-12.5% ወለድ ይከፈላል።

የህጻናት ቁጠባ

በማኅበሩ የሥራ ክልል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት፤ የማኅበሩ አባላትም ሆነ አባል ያልሆኑ ልጆች በወላጆቻቸው አማካኝነት 8% ወለድ የሚታሰብለት ከብር 25 (ሃያ አምስት ብር) ጀምሮ መቆጠብ የሚችሉበት የቁጠባ ሂሳብ ነው። እድሜያቸው 18 ዓመት ሲሆናቸው ያለመመዝገቢያ ክፍያ የማኅበሩ አባል መሆን ይችላሉ።
አባሉ ለብድር የሚሆነውን ቅድሚያ ቁጠባ በሚቆይበት ወራት ከፋፍሎ መቆጠብ ይኖርበታል።
የቁጠባ ቆይታየብድር መጠን በብርቅድሚያ ቁጠባመመለሻ ጊዜወለድ በመቶኛ (%)
2 ወር75,000የብድሩን አንድ ሦስተኛ (1/3) የቆጠበ18 ወራት 12.5
5 ወር300,000የብድሩን አንድ አራተኛ (1/4) የቆጠበ36 ወራት13.5
6 ወር400,000የብድሩን አንድ አራተኛ (1/4) የቆጠበ36 ወራት13.5
9 ወር500,000የብድሩን አንድ አራተኛ (1/4) የቆጠበ42 ወራት14.5
12 ወር600,000የብድሩን አንድ አራተኛ (1/4) የቆጠበ60 ወራት15.5
18 ወር በላይ1,000,000የብድሩን አንድ አራተኛ (1/4) የቆጠበ84 ወራት16.5
 • በደመወዝ ዋስትና፦ እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር ድረስ መበደር ይቻላል
 • የቁጠባ ዋስትና፦ አባል የሆኑ ግለሰቦች ባላቸው የቁጠባ መጠን እርስ በእርስ ዋስ የሚሆኑበት እና ብድር የሚያገኙበት መንገድ
 • የንብረት ዋስትና፦ የመኪና ሊብሬ ወይም የቤት ካርታ በዋስትና በማስያዝ መበደር የሚቻልበት መንገድ
 • ለመኪና እና ለቤት መግዣ የሚሆን ብድር፦ የ30% ቅድመ ቁጠባ በመቆጠብ እና የሚገዛውን መኪና ወይም ቤት በዋስትናነት በማስያዝ
 • ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ እና ከአባላት ጋር ተመሳሳይ ፍላጎትና ዓላማ ያለው
 • የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የመተዳደሪያ ደንብ እና ልዩ ልዩ መመሪያ እና ደንቦችን የሚቀበል
 • የመመዝገቢያ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) እና ዝቅተኛውን የዕጣ ክፍያ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) መክፈል የሚችል
 • በማኅበሩ ውስጥ በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲመረጥ ያለ ክፍያ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ
 • አንድ አባል አባል ከሆነ ከሁለት ወር ጀምሮ ብድር መስጠቱ
 • ብድር በአነስተኛ ወለድ መስጠቱ
 • የብድር ወለድ የሚታሰበው በቀሪ ዕዳ ላይ መሆኑ
 • በደመወዝ ዋስትና ብቻ እስከ 100 ሺህ ብር ብድር መስጠቱ
 • ዋስትና ማቅረብ ለማይችሉ የቡድን (የጠለፋ) ዋስትና መጀመሩ
 • በዝቅተኛ ብር አባል አንዲሆን ማደረግ መቻሉ
 • አባላት ለኅብረት ሥራ ማኅበራቸው በሚለፉበት ጊዜ ማበረታቻ ሽልማት መስጠቱ
 • የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እና አባላትን በማሳተፍ በኅብረት ሆነው የሚሠሩበትን እና የሚለወጡበትን አገልግሎት መጀመሩ
 • የወል ቁጠባ መጀመሩ
 • ከተመሠረተ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 27.5 ሚሊዮን ብር ቁጠባ መሰብሰቡ መቻሉ እና 45.5 ሚሊዮን ብር ብድር ለአባላት መስጠቱ
 • በዚህ እድሜው ኅብረት ሥራ ማኅበሩ 31.4 ሚሊዮን ብር ሃብት ማፍራት መቻሉ ልዩ ያደርገዋል።
 • የአንድ እጣ ዋጋ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ሲሆን አንድ አባል መግዛት የሚችለው ዝቅተኛ መጠን 5 እጣዎችን ነው።
 • ማንኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በማኅበሩ የቁጠባና እጣ ንፅፅር 3.5፡1 መሰረት በየጊዜው ተጨማሪ እጣ መግዛት ይጠበቅበታል።

ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር፦ አድራሻ እና ስልክ

ተ.ቁአድራሻስልክ ቁጥር
1ዋና ቢሮ፦ ልደታ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፣ ዳሽን ባንክ አ.ማ.፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁ 2-04011 5 57 75 10
2ጀሞ 1፦ ታክሲ ተራ፣ ከለላ ሕንጽ፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 09011 4 62 59 61
3ኮተቤ 02፦ ጆሲ ሞል፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 103 011 6 73 39 12
4አየር ጤና፦ ሳሚ ካፌ ሕንጻ፣ 1ኛ ፎቅ011 3 69 42 24
5ገርጂ መብራት ኃይል፦ የዜድ ፕላዛ ሕንጻ፣ 1ኛ ፎቅ011 6 39 45 54

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።  

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …