አማራጭ የኮድ 3 ሜትር ታክሲ እና የኮድ አንድ ታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ኅብረተ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባን ባሕል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ታኅሳስ 9 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 50 አባላትን …
ተጨማሪየግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት
ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኀበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኀብረት ሥራ ማኅበር አዋጅ መሠረት በቁጥር 985/2009 ሲሆን፤ ሕጋዊ ሰውነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኀብረት ሥራ ኤጀንሲ በነሐሴ 2005 ዓ.ም. ፈቃድ አግኝቶ በሥራ ላይ ይገኛል። “ቤተል ውስጥ ሁላችንም አለን!!”
ተጨማሪእስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር
እስታቴር ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ የተቋቋመ ሲሆን ዋናው ቢሮውም በኮልፌ አጠና ተራ ይገኛል።
ተጨማሪቀንዲል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.
ቀንዲል በአብዛኛው ሀገሪቱ ክልሎች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ለሥራ ተነሳሽነት ያላቸው ዜጎች በተለይም ለባንክ አገልግሎት ዕድል ለተነፈጉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ በማግኘት የተቋቋመ ነው። ለቁም ነገር ተበደሩ፣ በጊዜው ክፈሉ፣ ዘወትር ቆጥቡ!
ተጨማሪተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ተደራሽ ማኅበረ ሰብ አቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር “ትንሽ ቆጥበው ትልቅ ይሁኑ” የሚል መሪ ቃል ይዞ የተመሠረተ ተቋም ነው።
ተጨማሪአጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር
ኅብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን እውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።
ተጨማሪቤተሰብ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም
ቤተሰብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። ማኅበሩ ዝቅተኛውን የማኅበረሰብ ክፍልን እና የሥራ ፈጣሪዎችን በተለይ ሴቶችን ማዕከል በማድረግ የጋራ በሆኑት ዕሴቶች ላይ ማለትም ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።
ተጨማሪኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.
ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 626/2001 መሠረት በአንድ መቶ ሚሊዮን ብር (ብር 100,000,000) ካፒታል የተቋቋመ የፋይናንስ ተቋም ነው። ተቋሙ በቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ኤልሳቢ በዋናነት የባንክ አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ማኅበረ ሰቦች (ጥቃቅን ሥራ ፈጣሪ እና አነስተኛ …
ተጨማሪሳር ቤት የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ሳር ቤት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በሳር ቤት አካባቢ ተወልደው ባደጉ አብሮ አደጎች መነሻ ሃሳብ አመንጪነት የመኖሪያ አካባቢን መሠረት አድርጎ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው። ዋነኛ ዓላማው አድርጎ የተነሳው የአባላቱን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች የቁጠባን ባህል በማስረፅ እና በእቅድ በመበደር የሚፈቱበትን መንገድ ማበጀት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የአባላቱን …
ተጨማሪየአብሮነት ተምሳሌት በተግባር – ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም
ዮቶር በዋናነት በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባላት ንግዳቸውን የሚያንቀሳቅሱበት እና የሚያስፋፉበት እንዲሁም አብሮነታቸውን የሚያጠነክሩበት፤ ብሎም መካከለኛ የገንዘብ ዓቅም በማዳበር የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለማሟላት የሚውል የገንዘብ አቅርቦትን ለመፍጠር በሠለጠነ የሰው ኃይል እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ጠንካራ የኀብረት ሥራ ማኅበር በመፍጠር እስከ 2026 ዓ.ም ድረስ የአባላቱን …
ተጨማሪ