መነሻ / ሥራ ፈጣሪዎችና ሥራ ፈጠራ

ሥራ ፈጣሪዎችና ሥራ ፈጠራ

በዚህ ሥር፣ ስለ ስኬታማ ሥራ ፈጠራ፣ የሥራ ፈጣሪዎች ተሞክሮ፣ የሥራና አጠቃላይ ቢዝነስ ልዩ ልዩ ዘዴዎች፣ ልዩ ልዩ ትንታኔዎች፣ ቢዝነስን ፈር ማስያዣ መንገዶች እና የመሳሰሉት ላይ ጽሑፎችን ያገኛሉ።

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ምን አያደርጉም?

የራሳቸውን ቢዝነስ የሚመሩ ወይም በአንድ ቢዝነስ ውስጥ በየትኛውም ደረጃ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የሚሠሩ ሰዎች፣ አካላዊ ጤና እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ የአእምሮ ጽናትም ያሻቸዋል። በተለይ አንድ ቢዝነስ በሁለት እግሩ እንዲቆም ለማደረግ ለሚጥሩ ኧንተርፕረነሮች፣ የአእምሮ ጽናት እጅግ አስፈላጊ ነው። የአእምሮ ጽናት ሲባል ራሱ ጽናት፣ አይበገሬነት፣ በቀላሉ አለመረበሽ፣ ይሳካል ብሎ ማመን እንዲሁም በትናንሽ “ውድቀቶች” ተስፋ አለመቁረጥን …

ተጨማሪ

የቢዝነስ መመዘኛ ዘዴ

አንድ ቢዝነስ እንዲሰምር፣ ጠንካራ እና ደካማ ጎንን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዚህም በመነሣት፣ ከጠንካራ ጎኑ የሚመነጩ ዕድሎችን፣ እንዲሁም ከደካማ ጎኑ የሚነሡ ሥጋቶችንም በቅጡ መረዳት አለበት። እንዲህ ሲሆን፣ ድካሙን አካክሶ፣ ጠንካራ ጎኖቹን አዳብሮ የተሳካ ቢዝነስን ማስኬድ ይችላል። ይህ ሃሳብ፣ የቢዝነስ ጠበብት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል “SWOT” ብለው የሚጠሩት የቢዝነስ ሂደት መመዘኛ መስፈርት ሆኖ …

ተጨማሪ

ግብ እንዴት ልቅረጽ?

ለቢዝነሳችንም ሆነ ለግል ሕይወታችን የት እና እንዴት መድረስ እንደምንፈልግ ግልጽ የሆነ ግብ መያዝ ከመባከን ያድነናል። ይሁን እንጂ ሰዎችም ሆኑ ቢዝነሶች ብዙ ጊዜ ግባቸውን ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ይቸገራሉ፤ አንዳንዴ እንደውም ጭራሽ ምንም ግብ ሳይቀርጹ ይቀራሉ። የትኛውም ዓይነት ግብ ሲቀረጽ፣ በሚከተለው መልኩ ቢሆን ለመቅረጽም፣ ለመከታተልም፣ እንዲሁም ለመተግበር ያመቻል። ይህ የግብ አቀራረጽ …

ተጨማሪ

“የቢዝነስ ሰሌዳ” መጠቀም

የቢዝነስ ሰሌዳ (Business Canvas) አዲስ ሥራ ለመጀመር ለተነሣ የቢዝነስ ሰው/ ድርጅትም ሆነ ሥራ ላይ ለቆየ፣ ሥራን ውጤታማና ትርፋማ ለማድረግ ሁነኛ መሣሪያ ነው። የቢዝነስ ሰሌዳ፣ እንደ ቢዝነስ ማጤን ያለብንን ዋና ዋና ነገሮች እንዳንስት ይረዳል። ውጤታማና ትርፋማ ለመሆን፣ በሰሌዳው ላይ የተቀመጡትን ነጥቦች ልብ ማለት ይበጃል። ሰሌዳውን በወረቀት ላይ አትሞ፣ በእያንዳንዱ ነጥብ ሥር …

ተጨማሪ

የስኬታማ ሥራ ፈጣሪ (ኧንተርፕረነር) መለያዎች

አንድ ሰው የተሳካለት ሥራ ፈጣሪ ወይም ኧንተርፕረነር (አዲስና የተለየ የቢዝነስ ሃሳብ ወይም ዘዴ ይዞ የተነሣ) ለመሆን፣ የያዘው ሃሳብና ሃሳቡን ተግባራዊ ማድረጊያ ገንዘብ ወሳኝ መሆናቸው አይጠረጠርም። ሆኖም፣ እነዚህ ሁለቱ ብቻ ኧንተርፕረነሩ የተሳካለት የቢዝነስ ሰው እንዲሆን አያስችሉትም። ኧንተርፕረነር፣ ስኬትን መቀዳጀት እንዲችል ወይም ጉዞው ወደ ስኬት የሚገሰግስ እንዲሆን፣ ዓይነተኛ የሆኑ የሰብዕና መገለጫዎች ያስፈልጉታል። …

ተጨማሪ

ሽያጭ እና ገበያ ጥናት

ማንኛውም ምርት ወይም አገልግሎት አቅራቢ፣ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ተጠቃሚው “እንዲገዛው” ማድረግ መቻል ይኖርበታል። የአንድ ቢዝነስ ህልውና ቀጣይ ሊሆን የሚችለው ሽያጭ ማከናወን ሲሳካለት ብቻ ነው። አንድ ምርት ወይም አገልግሎት ጥሩ ሽያጭ እንዲኖረው አንዱ ሁነኛ የሚባለው ዘዴ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 4 የሽያጭ ዘዴ ምሰሶዎችን ልብ ማለት ነው። እነዚህ አራቱ ምሰሶዎች ለሽያጭ ዘዴ …

ተጨማሪ

ቢዝነስ አስተዳደር እና ሂሳብ አያያዝ

አንድን ቢዝነስ ስኬታማ በሆነ መልኩ ማስተዳደርና መምራት ከፍተኛ ኃላፊነት ነው። በተለይ በቂ ልምድ ከማዳበራችን በፊት ያሉት የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት፣ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥሩብንና ውጥረት ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ። ይህንን ጫናና ውጥረት ለመቀነስና ቢዝነሳችንን በተሳካ መልኩ ለማስኬድ፣ የወጪ ገቢውን ፍሰት የተስተካከለ ለማደረግ፣ የቢዝነስ አስተዳደር ባለሙያዎችና ቢዝነሶችን በመምራት ተሞክሮ ያላቸው ሰዎች የሚስማሙባቸው አንዳንድ ጠቃሚ …

ተጨማሪ