ከአንድ የኢንተርፕራይዝ ደረጃ ወደ ሌላው ማደግ የሚቻለው እንዴት እና መቼ ነው?
አንድ ኢንተርፕራይዝ ከአንድ የዕድገት ደረጃ ወደ ሌላ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ደረጃውን ማሳደስና ወደ ሌላ ደረጃ መሸጋገር ይችላል።
የዕድገት ደረጃ ማሳደግ የሚቻለው ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ብቻ ሲሆን፣ ከህዳር 1 እስከ 30 ደግሞ ከጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ጋር የዕድገት ደረጃ ሊታደስ ይችላል።
ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ የዕድገት ደረጃ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?
- ምስረታ ወይም ጀማሪ
- ታዳጊ ወይም መስፋት
- መብቃት
- ታዳጊ መካከለኛ
ማንኛውም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ እስከ 5ኛ ዓመት ድረስ የዕድገት ደረጃውን ቢያሻሽልም ባያሻሽልም ወደ ታዳጊ መካከለኛ መሸጋገር አለበት። ይህ ካልሆነ የዕድገት ደረጃ ሰርትፍኬቱ ተሰርዞ ከየትኛውም የጥቃቅንና አነስተኛ የድጋፍ ማዕቀፎች ውጪ ሊሆን ይችላል።