መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ድጋፍ / በጀማሪ ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ

በጀማሪ ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ

በምሥረታ ወይም ጀማሪ ደረጃ ላይ የሚገኙ (ገና በመቋቋም ላይ የሚገኙ ወይም ለመቋቋም የሚያስቡ) ኢንተርፕራይዞች፣ የሚያገኙት ድጋፍ ደግሞ እንደሚከተለው ነው።

በምሥረታ ወይም ጀማሪ (Start-up) ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ

እንዲህ ዓይነቱ ድጋፍ የሚያካትተው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመመስረት በመፈለግ በማኅበር እና በግለሰብ በህግ አግባብ ተደራጅተው የራሳቸውን ቁጠባና ከተለያዩ ፋይናንስ ተቋማት ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ የገቡትን ነው።

የምስረታ/ጀማሪ ደረጃ ኢንተርፕራይዙ ህጋዊ አቋም ይዞ ማምረትና አገልግሎት መስጠት የሚጀምርበት ደረጃ ነው። በምስረታ/ጀምሪ ደረጃ ላይ ላለ ኢንተርፕራይዝ መንግስት የሚሰጣቸው የድጋፍ ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

  • የመነሻ ካፒታል ማመቻቸት
    • ኢንተርፕራይዝ ለመመስረት ፍላጎቱ ያላቸውን በራሳቸው እንዲቆጥቡ ማበረታታትና የራሳቸው ቁጠባ ሲኖራቸው ለብድር ቅድሚያ እንዲያገኙ ማመቻቸት
  • ህጋዊ አቋም እንዲኖራቸው ማብቃት
    • በምስረታ ላይ ያሉ ኢንተርፕራይዞች በመረጡት ህጋዊ አደረጃጀት ተጠቅመው እንዲቋቋሙ መደገፍ
    • በሁሉም ዓይነት ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የህጋዊ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እንዲያገኙ ማድረግ
  • የቢዝነስ ሥራ አመራር፣ ኧንተርፕረነርሺፕና ሂሳብ አያያዝ ብቃት ማሳደግ
    • ኢንተርፕራይዞቹ መሠረታዊ የቢዝነስ ሥራ አመራርና ኧንተርፕረነርሺፕ ክህሎት እንዲኖራቸው ማስቻል
    • መሠረታዊ የሂሳብ አያያዝ ስልጠናዎችን መስጠትና ሞዴል የሂሳብ አያያዝ ማኑዋሎችን አዘጋጅቶ መስጠት
    • የክህሎትና የቴክኒክ ስልጠናዎችን መስጠት

 

ይህንንም ይመልከቱ

enterprise-support

ለኢንተርፕራይዞች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎች

ይህ ጽሑፍ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን ዓላማውም ኢንተርፕራይዞች ማግኘት የሚችሉትን …