ወቅታዊ መረጃ

በዚህ ሥር፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ልዩ ልዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

kefta-care-training-2

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው ኢንተርፕራይዞቹ በኬር ኢትዮጵያ በተመቻቸላቸው ዕድል የ”ከፍታ” አገልግሎትን ተጠቅመው እንዴት የጨረታ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ በተጨማሪም እንዴት አድርገው ድርጅታቸውን፣ ምርታቸውን እና አግልግሎታቸውን እንደሚያስተዋውቁ ነው።

ተጨማሪ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች

TUC_NSP_2merkato_poster_ad_20221031-04

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ኢንተርፕራይዞች ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል (The Urban Center) የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች በነጻ ይሰጣል። ሥልጠናዎቹ የሚሰጡት በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ነው፦ 1. በአልሙኒየም ሥራ 2. በቀለም እና ሕንጻ ማጠናቀቅ ሥራ 3. በእንጨት ሥራ

ተጨማሪ

ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በብድር ሊያገኙ ነው

አዋሽ ባንክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። ባንኩ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (ለአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት) ለማበደር ካቀደው በጀት ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ብድር ተጠቃሚ ከሚሆኑ ዘጠኝ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር ባለፈው ሐሙስ ሐምሌ 21 ቀን …

ተጨማሪ

የሮያሊቲ ክፍያ ለባህላዊ ወርቅ አምራቾች ሙሉ በሙሉ ተነሳላቸው

artisanal-miner

በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ የሚያቀርቡ አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረው የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች መነሳቱ ተገለጸ። ይህን የገለጹት የማዕድን እና የኢነርጂ ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በፌስቡክ ገጻቸው ነው፤ ውሳኔውንም የሚመሰገን ነው ያሉት ሚኒስትሩ አክለውም “ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር የሰጠነው ትኩረት ማሳያ ነው” ብለዋል። የባህላዊ እና …

ተጨማሪ

የከተማ ግብርና፦ በአዲስ አበባ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ5000 ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር ተሸፈነ

የከተማ-ግብርና

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከአምስት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር መሸፈኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደሮችና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መኮንን ሌንጅሶ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በመሆን የከተማ ግብርና የሥራ እንቅስቃሴን በቦሌ ክፍለ ከተማ በመገኘት የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

ተጨማሪ

የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ

BoJCED-Tamiru-Debela

በኮቪድ ተፅዕኖ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑን የአዲስ አበባ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገለጸ። በ2014 አዲስ ዓመት ዋዜማ ኤግዚብሽንና ባዛር በዐሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች አንድ ሺህ ዐሥር ኢንተርፕራይዞች መሳተፋቸውን በቢሮው የገበያ ልማትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡

ተጨማሪ

ለኢንተርፕይዞች ማገገሚያና መቋቋሚያ ብድር

ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕይዞችን ማገገሚያና መቋቋሚያ ፕሮጀክት ይህ ፕሮጀክት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተርካርድ ፋውንዴሽንና ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ የደረሰውን የንግድ መቀዛቀዝ ለመገዳደር ጥረት እያደረጉ ያሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማገዝ ነው። ፕሮጀክቱ ዝቅተኛ ወለድ እና የእፎይታ ጊዜ ያለው ብድር በተመረጡ የፋይናንስ …

ተጨማሪ

በኮሮና ምክንያት ለተጎዱ በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፍ ለተሰማሩ ሰራተኞች የ4.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

በኮሮና ምክንያት ለተጎዱ በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፍ ለተሰማሩ ሰራተኞች የ4.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የተጎዱ  በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፍ ተሰማርትው የሚሰሩ ሠራተኞችን ለመደገፍ የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል። ድጋፉ የሠራተአኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒቴር  ከአለም አቀፉ የስራ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ይፋ …

ተጨማሪ

አዋሽ ባንክ ለአነስተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በአይነቱ የተለየ የባንክ አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገለፀ

አዋሽ ባንክ ለአነስተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በአይነቱ የተለየ የባንክ አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገለጸ። ይህ አገልግሎት ኢንተርፕራይዞች ሥራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመሥራት እና ውጤታማ ለመሆን እንደሚያስችላቸው ነው ባንኩ የገለጸው፤ በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ከአዋሽ ባንክ ጋር በማነጋገር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጾአል። የዜና ምንጭ፡ ፋና ብሮድካስቲንግ

ተጨማሪ

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፈተ

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚብሽን እና ባዛር በአዲስ አበባ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ከታኅሣሥ 21፣ 2013 ዓ.ም ተከፍቷል ። ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ እስከ የገና በዓል ዋዜማ ረቡዕ ታህሳስ 28 ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል። አቶ ታምሩ ደበላ፣ የአዲስ አበባ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞችል ልማት ቢሮ የገበያና ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለከፍታ …

ተጨማሪ