ወደ ታዳጊ መካከለኛ ደረጃ ለማደግ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማራ ጥቃቅን/አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
- በሥራ ዕድል ፈጠራ
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ30 ሰዎች በላይ
- የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በዓመት ውስጥ ከ20 ሰዎች በላይ
- በሃብት መጠን
- ጠቅላላ ሃብት ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
- በብድር ካገኘው ገንዘብ ቢያንስ 70% ለቋሚ ንብረት ያዋለ
- የሃብት እና የእዳ መግለጫ (ኦዲት ሪፖርት) ህጋዊ እውቅና ባለው ኦዲተር ያረጋገጠ
- በትርፋማነት
- በ1 ዓመት ካደረገው ሽያጭ እስከ 30% ትርፍ ያስመዘገበ
- ከትርፉ ላይ ለሥራ ማስፋፊያ ያዋለው ወይም የቆጠበው፣ ከተጣራ ሃብቱ ቢያንስ 50% የሆነ
- በገበያ መጠን
- የ1 ዓመት ሽያጩ ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ
- እንደየ ንዑስ ዘርፉ፣ ተከታዩ መጠን ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የሆነ
- ኮንስትራክሽን – ቢያንስ 50%
- ብረታ ብረትና እንጨት – ቢያንስ 80%
- ሌሎች ንዑስ ዘርፎች – ቢያንስ 90%
- ለሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በንዑስ ኮንትራት በ1 ዓመት ቢያንስ 5 ጊዜ የገበያ ትስስር የፈጠረ
- ቢያንስ አምስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
- ለደረጃው በተዘጋጀ ኤግዚቢሽንና ባዛር ቢያንስ በዓመት ሁለቴ የተሳተፈ
- በምርታማነት
- ካለው ሙሉ የማምረት አገልግሎት የመስጠት አቅም ቢያንስ 85% የተጠቀመ
- ለሚያመርታቸው ምርቶችና አገልግሎቶች ዘመናዊ የሥራ አመራርን የተከተለ የቁጥጥር ሥርዓት የዘረጋ
- ለገቢ ወይም ለወጪ ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችን ወይም ገቢ ምርቶችን የሚተካ፣ ወይም ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን ማምረት የቻለ
- ከኢንተርፕራይዙ አባላት ወይም ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ ቢያንስ 90% ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያላቸው
- በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት
- ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ያደረገና ስትራቴጂክ ዕቅድ ያለው
- የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ያዋለና ኦዲት ያስደረገ
- የማምረቻ ማዕከሉ አደረጃጀት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽሕናውን የጠበቀ
- የሠራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እና እንደ ንዑስ ዘርፉ ዓይነት የደህንነት መሣሪያዎች የተሟሉለት
- ሥራውን ሊያስፋፋ የሚያስችል በጽሑፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ያለው
- ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥም ሆነ በጋራ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል የንግድ ግንኙነት የፈጠረ
- በመንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም
- የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግባር ላይ አውሎ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣና የአሠራሩን ተሞክሮ ለሌሎች ማካፈል የሚችል
- ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ጋር በትብብርና በኩባንያ ውስጥ ስልጠና የሚሳተፍ
- ተደጋጋሚ የብድር ተጠቃሚ ሆኖ ያልተመለሰ ውዝፍ ብድር የሌለበት
- የማምረቻ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆነ፣ የውል ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ
- በመንግስት የሚሰጠውን የገበያ ትስስር በገባው ውል መሠረት በአግባቡ እየሠራ ያለ ወይም ሠርቶ ያስረከበ
- ወደ ኢንዱስትሪ ዞን ለመግባት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ
- ከንግድና ልማት ባንኮች ለመበደር የሚያስችል የብድር ዋስትና ያዘጋጀ
- በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጪ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ የሆነ
- የምርትና አገልግሎት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ወቅታዊና የተሻሻለ አሠራር ተጠቃሚ የሆነ
- ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም የአግልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ 85% የአካባቢ ብክለት የማያስከትሉና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ
- ግዴታን ስለመወጣት
- የሚጠበቅበትን የ1 ዓመት ገቢ ግብር የከፈለ
- ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እድሳት ያካሄደ
- የተሠጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት የመለሰ
በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማራ ጥቃቅን/አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
- በሥራ ዕድል ፈጠራ
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ20 ሰዎች በላይ
- የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በዓመት ውስጥ ከ15 ሰዎች በላይ
- በሃብት መጠን
- ጠቅላላ ሃብት ከ500,000 ብር በላይ (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
- በብድር ካገኘው ገንዘብ ቢያንስ 40% ለቋሚ ንብረት ያዋለ
- የሃብት እና የእዳ መግለጫ (ኦዲት ሪፖርት) ህጋዊ እውቅና ባለው ኦዲተር ያረጋገጠ
- በትርፋማነት
- በ1 ዓመት ካደረገው ሽያጭ ቢያንስ 30% ትርፍ ያስመዘገበ
- ከትርፉ ላይ ቢያንስ ለሥራ ማስፋፊያ ያዋለው ወይም የቆጠበው፣ ከተጣራ ሃብቱ ቢያንስ 30% የሆነ
- በገበያ መጠን
- የ1 ዓመት ሽያጩ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ
- ከሽያጩ ቢያንስ 90% ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የተገኘ
- ቢያንስ አምስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
- በምርታማነት
- ካለው ሙሉ የማምረት አገልግሎት የመስጠት አቅም ቢያንስ 85% የተጠቀመ
- ለሚያመርታቸው ምርቶችና አገልግሎቶች ዘመናዊ የሥራ አመራርን የተከተለ የቁጥጥር ሥርዓት የዘረጋ
- ለገቢ ወይም ለወጪ ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችን ወይም ገቢ ምርቶችን የሚተካ፣ ወይም ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን ማምረት የቻለ
- ከኢንተርፕራይዙ አባላት ወይም ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ ቢያንስ 90% ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያላቸው
- በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት
- ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ያደረገና ስትራቴጂክ ዕቅድ ያለው
- የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ያዋለና ኦዲት ያስደረገ
- የማምረቻ ማዕከሉ አደረጃጀት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽሕናውን የጠበቀ
- የሠራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እና እንደ ንዑስ ዘርፉ ዓይነት የደህንነት መሣሪያዎች የተሟሉለት
- ሥራውን ሊያስፋፋ የሚያስችል በጽሑፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ያለው
- ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥም ሆነ በጋራ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል የንግድ ግንኙነት የፈጠረ
- በመንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም
- የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግባር ላይ አውሎ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣና የአሠራሩን ተሞክሮ ለሌሎች ማካፈል የሚችል
- ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ጋር በትብብርና በኩባንያ ውስጥ ስልጠና የሚሳተፍ
- ተደጋጋሚ የብድር ተጠቃሚ ሆኖ ያልተመለሰ ውዝፍ ብድር የሌለበት
- የማምረቻ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆነ፣ የውል ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ
- በመንግስት የሚሰጠውን የገበያ ትስስር በገባው ውል መሠረት በአግባቡ እየሠራ ያለ ወይም ሠርቶ ያስረከበ
- ወደ ኢንዱስትሪ ዞን ለመግባት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ
- ከንግድና ልማት ባንኮች ለመበደር የሚያስችል የብድር ዋስትና ያዘጋጀ
- በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጪ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ የሆነ
- የምርትና አገልግሎት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ወቅታዊና የተሻሻለ አሠራር ተጠቃሚ የሆነ
- ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም የአግልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ 85% የአካባቢ ብክለት የማያስከትሉና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ
- ግዴታን ስለመወጣት
- የሚጠበቅበትን የ1 ዓመት ገቢ ግብር የከፈለ
- ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እድሳት ያካሄደ
- የተሠጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት የመለሰ
ወደ ታዳጊ መካከለኛ ኢንዱስትሪ የመሸጋገር ሂደት
እንዲህ ዓየነቱ ሽግግር ዘርፍ፣ ካፒታል እና ኢንተርፕራይዙ የፈጠረውን የሥራ ዕድል መሠረት ያደረገ ነው።
በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማራ ኢንተርፕራይዝ
- ካፒታሉ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ (በማስረጃ የተረጋገጠ)
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ30 ሰው በላይ
- የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ20 ሰው በላይ
በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማራ ኢንተርፕራይዝ
- ካፒታሉ ከ500 ሺህ ብር በላይ (በማስረጃ የተረጋገጠ)
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ20 ሰው በላይ
- የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከ15 ሰው በላይ