ወደ መብቃት ደረጃ ለማደግ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማራ ጥቃቅን/አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
- በሥራ ዕድል ፈጠራ
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል፡-
- ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ እስከ 5 ሰዎች የቀጠረ
- ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ 6 እስከ 15 ሰዎች የቀጠረ
- የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል፡-
- ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በዓመት ውስጥ እስከ 3 ሰዎች የቀጠረ
- ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በዓመት ውስጥ ከ3 እስከ 15 ሰዎች የቀጠረ
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል፡-
- በሃብት መጠን
- ጠቅላላ ሃብት ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከ75,001 እስከ 100,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
- ጠቅላላ ሃብት ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ500,001 እስከ 1,500,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
- በብድርም ሆነ በራሱ ገንዘብ ሥራ ለጀመረ፣ ካገኘው ሃብት ቢያንስ 50% ለቋሚ ንብረት ያዋለ
- ቋሚ ንብረት ኖሮት ለግብዓት የሚበደር፣ ብድሩን ሙሉ በሙሉ ለሥራ ያዋለ
- በብድርም ሆነ በራሱ ገንዘብ ሥራ ለጀመረ፣ ካገኘው ሃብት ቢያንስ 50% ለቋሚ ንብረት ያዋለ
- ቋሚ ንብረት ኖሮት ለግብዓት የሚበደር፣ ብድሩን ሙሉ በሙሉ ለሥራ ያዋለ
- የሃብት እና የእዳ መግለጫ (ኦዲት ሪፖርት) ህጋዊ እውቅና ባለው ኦዲተር ያረጋገጠ
- በትርፋማነት
- በ1 ዓመት ካደረገው ሽያጭ ቢያንስ 20% ትርፍ ያስመዘገበ
- ከትርፉ ላይ ለሥራ ማስፋፊያ ያዋለው ወይም የቆጠበው፣ ከተጣራ ሃብቱ ቢያንስ 30% የሆነ
- በገበያ መጠን
- የ1 ዓመት ሽያጩ፡-
- ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከ75,000 እስከ 100,000 ብር የሆነ
- ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ500,001 እስከ 1,500,000 ብር የሆነ
- እንደየ ንዑስ ዘርፉ፣ ተከታዩ መጠን ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የሆነ
- ኮንስትራክሽን – ቢያንስ 35%
- ብረታ ብረትና እንጨት – ቢያንስ 75%
- ሌሎች ንዑስ ዘርፎች – ቢያንስ 80%
- ለሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በንዑስ ኮንትራት በ1 ዓመት ቢያንስ 2 ጊዜ የገበያ ትስስር የፈጠረ
- ቢያንስ አምስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
- ለደረጃው በተዘጋጀ ኤግዚቢሽንና ባዛር ቢያንስ በዓመት ሦስቴ የተሳተፈ
- የ1 ዓመት ሽያጩ፡-
- በምርታማነት
- ካለው ሙሉ የማምረት አገልግሎት የመስጠት አቅም ቢያንስ 70% የተጠቀመ
- ለሚያመርታቸው ምርቶችና አገልግሎቶች ዘመናዊ የሥራ አመራርን የተከተለ የቁጥጥር ሥርዓት የዘረጋ
- ለገቢ ወይም ለወጪ ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችን ወይም ገቢ ምርቶችን የሚተካ፣ ወይም ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን ማምረት የቻለ
- ከኢንተርፕራይዙ አባላት ወይም ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ ቢያንስ 75% ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያላቸው
- በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት
- ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ያደረገና ስትራቴጂክ ዕቅድ ያለው
- የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ያዋለና ኦዲት ያስደረገ
- የማምረቻ ማዕከሉ አደረጃጀት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽሕናውን የጠበቀ
- የሠራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እና እንደ ንዑስ ዘርፉ ዓይነት የደህንነት መሣሪያዎች የተሟሉለት
- ሥራውን ሊያስፋፋ የሚያስችል በጽሑፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ያለው
- ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥም ሆነ በጋራ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል የንግድ ግንኙነት የፈጠረ
- በመንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም
- የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግባር ላይ አውሎ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣና የአሠራሩን ተሞክሮ ለሌሎች ማካፈል የሚችል
- ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ጋር በትብብርና በኩባንያ ውስጥ ስልጠና የሚሳተፍ
- ተደጋጋሚ የብድር ተጠቃሚ ሆኖ ያልተመለሰ ውዝፍ ብድር የሌለበት
- የመሥሪያ ቦታ ተጠቃሚ ከሆነ፡-
- የውል ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ
- የኪራይ ውዝፍ ዕዳ የሌለበት
- ከማዕከሉ ከመውጣቱ በፊት አስፈላጊውን የፋይናንስና የማምረቻ ቦታ ቅድመ ዝግጅት ያደረገ
- በመንግስት የሚሰጠውን የገበያ ትስስር በገባው ውል መሠረት በአግባቡ እየሠራ ያለ ወይም ሠርቶ ያስረከበ
- በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጪ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ የሆነ
- የምርትና አገልግሎት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ወቅታዊና የተሻሻለ አሠራር ተጠቃሚ የሆነ
- ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም የአግልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ 75% የአካባቢ ብክለት የማያስከትሉና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ
- ግዴታን ስለመወጣት
- የሚጠበቅበትን የ1 ዓመት ገቢ ግብር የከፈለ
- ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እድሳት ያካሄደ
- የተሠጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት የመለሰ-
በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማራ ጥቃቅን/አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
- በሥራ ዕድል ፈጠራ
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል፡-
- ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ እስከ 5 ሰዎች የቀጠረ
- ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ ከ 6 እስከ 15 ሰዎች የቀጠረ
- የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል፡-
- ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ እስከ 2 ሰዎች የቀጠረ
- ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ 2 እስከ 15 ሰዎች የቀጠረ
- የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል፡-
- በሃብት መጠን
- ጠቅላላ ሃብት ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከ40,001 እስከ 50,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
- ጠቅላላ ሃብት ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ50,001 እስከ 500,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
- በብድርም ሆነ በራሱ ገንዘብ ሥራ ለጀመረ፣ ካገኘው ሃብት ቢያንስ 20% ለቋሚ ንብረት ያዋለ
- ቋሚ ንብረት ኖሮት ለግብዓት የሚበደር፣ ብድሩን ሙሉ በሙሉ ለሥራ ያዋለ
- በትርፋማነት
- በ1 ዓመት ካደረገው ሽያጭ ቢያንስ 20% ትርፍ ያስመዘገበ
- ከትርፉ ላይ ለሥራ ማስፋፊያ ያዋለው ወይም የቆጠበው፣ ከተጣራ ሃብቱ ቢያንስ 20% የሆነ
- በገበያ መጠን
- የ1 ዓመት ሽያጩ፡-
- ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከ50,001 እስከ 75,000 ብር የሆነ
- ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ200,001 እስከ 750,000 ብር የሆነ
- ከሽያጩ ቢያንስ 85% ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የተገኘ
- ቢያንስ አምስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
- የ1 ዓመት ሽያጩ፡-
- በምርታማነት
- ካለው ሙሉ የማምረት አገልግሎት የመስጠት አቅም ቢያንስ 70% የተጠቀመ
- ለሚያመርታቸው ምርቶችና አገልግሎቶች ዘመናዊ የሥራ አመራርን የተከተለ የቁጥጥር ሥርዓት የዘረጋ
- ለገቢ ወይም ለወጪ ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችን ወይም ገቢ ምርቶችን የሚተካ፣ ወይም ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን ማምረት የቻለ
- ከኢንተርፕራይዙ አባላት ወይም ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ ቢያንስ 75% ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያላቸው
- በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት
- ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ያደረገና ስትራቴጂክ ዕቅድ ያለው
- የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ያዋለና ኦዲት ያስደረገ
- የማምረቻ ማዕከሉ አደረጃጀት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽሕናውን የጠበቀ
- የሠራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እና እንደ ንዑስ ዘርፉ ዓይነት የደህንነት መሣሪያዎች የተሟሉለት
- ሥራውን ሊያስፋፋ የሚያስችል በጽሑፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ያለው
- ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥም ሆነ በጋራ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል የንግድ ግንኙነት የፈጠረ
- በመንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም
- የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግባር ላይ አውሎ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣና የአሠራሩን ተሞክሮ ለሌሎች ማካፈል የሚችል
- ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ጋር በትብብርና በኩባንያ ውስጥ ስልጠና የሚሳተፍ
- ተደጋጋሚ የብድር ተጠቃሚ ሆኖ ያልተመለሰ ውዝፍ ብድር የሌለበት
- የመሥሪያ ቦታ ተጠቃሚ ከሆነ፡-
- የውል ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ
- የኪራይ ውዝፍ ዕዳ የሌለበት
- ከማዕከሉ ከመውጣቱ በፊት አስፈላጊውን የፋይናንስና የማምረቻ ቦታ ቅድመ ዝግጅት ያደረገ
- በመንግስት የሚሰጠውን የገበያ ትስስር በገባው ውል መሠረት በአግባቡ እየሠራ ያለ ወይም ሠርቶ ያስረከበ
- በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጪ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ የሆነ
- የምርትና አገልግሎት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ወቅታዊና የተሻሻለ አሠራር ተጠቃሚ የሆነ
- ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም የአግልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ 75% የአካባቢ ብክለት የማያስከትሉና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ
- ግዴታን ስለመወጣት
- የሚጠበቅበትን የ1 ዓመት ገቢ ግብር የከፈለ
- ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እድሳት ያካሄደ
- የተሠጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት የመለሰ