መነሻ / የምክር ጥግ

የምክር ጥግ

ተደራጅቶ አዲስ ቢዝነስ ለጀመረ ወይም ቢዝነሱን ለማስፋት ለሚፈልግ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ፣ በዚያ ሂደት ውስጥ አስቀድሞ ያለፈ ሰው ወይም በተለያዩ የሙያ መስኮች (የቢዝነስ አመራር ወይም ዕድገት አማካሪ፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ ማርኬቲንግ፣ ወዘተ) ልምድ ያለው ሰው የሚሰጠው ምክርና ድጋፍ ያለው ዋጋ ከፍተኛ ነው። በዚህ ገጽ ሥር፣ ከቢዝነስና ከቢዝነስ አመራር ወይም ዕድገት እንዲሁም በየሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ ማርኬቲንግ፣ ወዘተ ጋር በተያያዘ፣ በጎ ፈቃደኛ መካሪና ልምድ አካፋይ (ሜንተር) ሆነው ቢመዘገቡ፣ የእርስዎን ግብዓት የሚፈልጉ ብዙ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ሊጠቅሙ ይችላሉ። እንዲሁም ጥቃቅን ወይም አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ከቢዝነስና ከቢዝነስ አመራር ወይም ዕድገት ጋር የተያያዘ ልምድ ካለው ሰው ምክርና ክትትል ከፈለጉ፣ መመዝገብ ይችላሉ።