ምዝገባ

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ ሲያከናውኑ፣ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሥራ ላይ ባለው የንግድና ምዝገባ የዘርፎች አደረጃጀት መሠረት ይሆናል። ሆኖም ጥቃቅና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ይህንን አገልግሎት በ “አንድ ማዕከል” አገልግሎት ያገኛሉ።

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች “አንድ ማዕከል” አገልግሎት

እንደየአካባቢው ሁኔታ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ እና በከተማ ደረጃ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የ”አንድ ማዕከል” አገልግሎት ያገኛሉ። ኢንተርፕራይዞች በማዕከሎቹ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያገኛሉ፡-

  • በኅብረት ሥራ ማኅበር፣ በግል፣ በሽርክና፣ ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ማኅበር ወዘተ መደራጀት፣ መመዝገብና የምስክር ወረቀት ማግኘት
  • የግብር ከፋይነት ምዝገባ አገልግሎት ማግኘት
  • የንግድ ፈቃድ ማደስ፣ መለወጥና መሰረዝ
  • የሂሳብ አያያዝና ኦዲት አገልግሎት ማመቻቸት

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …