ታፍ ሌዘር የተመሠረተው በ 2004 ዓ.ም. በወይዘሮ ትዝታ አሰፋ እና በስድስት ሴት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቆዳ ውጤት የሆኑ ምርቶችን ያመርታል።
ተጨማሪልምድ እና ተሞክሮ
ብራይት ማኑፋክቸሪንግ
ብራይት ማኑፋክቸሪንግ የተመሠረተው በአቶ ሠለሞን መገርሳ እና በሁለት ጓደኞቻቸው በ2021 (እ.ኤ.አ.) ነው። ድርጅቱ የእንሰት ተክልን በመጠቀም ከግሉተን ነጻ (gluten free) የሆነ ስታርች እና የፋይበር ምርቶችን ያመርታል። እነዚህም ምርቶች ለተለያዩ ተጠቃሚ ደንበኞች፣ የግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች፣ ሱፐርማርኬቶች እና የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ያቀርባል። በቅርቡም ወደ ውጭ ሀገር ምርቱን ለመላክ (export ለማድረግ) አውሮፓ …
ተጨማሪሚካኤል፣ ነብዩ እና ጓደኞቻቸው የእንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሚካኤል ውድነህ እና በጓደኞቻቸው በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የብረት እና የእንጨት ምርቶችን የሚያመርት ድርጅት ነው።
ተጨማሪብሩክ እና የኔነሽ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ብሩክ ነጋሽ እና ጓደኛቸው በ2006 ዓ.ም. ሲሆን አጠቃላይ የግንባታ ሥራዎችን በጠቅላላ ተቋራጭነት እንዲሁም የሕንጻ ማጠናቀቅ (ፊኒሺንግ) ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪፍጹም፣ ሜላት እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ፍጹም ዘላለም እና ጓደኞቻቸው በ2013 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች በዋናነት የእንጨት ምርቶች ሲሆኑ በተጓዳኝ ደግሞ የብረት ሥራዎችንም ይሠራል።
ተጨማሪለፍቅር መላኩ ሕንጻ ፊኒሽኒግ ሥራ ተቋራጭ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ፍቅር መላኩ በ2003 ዓ.ም. ነበር። ተመሥርቶ በነበሩ አንዳንድ ሁኔታዎች ለተወሰነ ጊዜ ከቆመ በኋላ እንደገና በ2009 ዓ.ም. አንደ አዲስ ሥራ ቀጥሏል። ድርጅቱ አጠቃላይ የፊኒሽንግ ሥራዎች እና ተያያዥ የሆኑ የብረት ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪዓለም እና ተገኘወርቅ የሌዘር ምርቶች ማምረቻ
ዓለም እና ተገኘወርቅ የሌዘር ምርቶች ማምረቻ የኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በአቶ ተገኘወርቅ ጫንያለው በ2008 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የቆዳ ውጤቶችን በጥራት የሚያመርት ድርጅት ሲሆን በይበልጥ ደግሞ ጫማዎችን በስፋት እያመረተ የሚገኝ ድርጅት ነው።
ተጨማሪሄኖክ፣ በላይ እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሄኖክ ስብሃት እና ዘጠኝ መሥራች አባላት 2013 ዓ.ም. ነው። አጠቃላይ የእንጨት ውጤቶችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ተያያዥ የሆኑ የብረት ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪመአዛ የጽዳት ዕቃዎች
ኡቡንቱ ኤራ ኅ.የተ.የግ.ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ መአዛ ታምራት በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የንጽህና መጠበቂያ እና የጽዳት ዕቃዎችን በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማምረት ለገበያ ያቀርባል።
ተጨማሪወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ
ወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ ኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ ፍቅርተ ገብሬ እና ሁለት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም. ነው። የቤት ማስዋቢያ እቃዎች እንዲሁም ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የፈርኒቸር ሥራዎችን ከእንጨት ውጤቶች ጋር በማቀናጅት (በማመሳጠር) ያመርታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የወንድ እና የሴት ጌጣጌጥ ምርቶችን (ማጌጭያዎችን) ያመርታል።
ተጨማሪ