industry

ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዕድገት ደረጃ

ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዕድገት ደረጃ የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች

 1. በሥራ ዕድል ፈጠራ
  ሀ) በኢንዲስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዙን አባላት ጨምሮ 101 በላይ ሆኖ በአገግልሎት ዘርፍ ደግሞ ከ 31 በላይ መሆን አለበት።
  ለ)  በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ በዓመት ውስጥ በጊዜያዊነት የፈጠረው የሥራ ዕድል ከ 31 ሰዎች በላይ ሆኖ በአገግግሎት ዘርፍ ደግሞ ከ21 በላይ መሆን አለበት።
 2. በሃብት መጠን
  ሀ) ጠቅላላ የሃብት መጠን የተጠራ ሃብት እና እዳን የሚያካትት ከብር 20,000,000.00 በላይ መሆን አለበት፤
  ለ)  ኢንተርፕራይዙ በብድር ካገኘው ገንዘብ ለቋሚ ንብረት ያዋለው 70 በመቶ እና በላይ መሆን አለበት፤
  ሐ) የሃብትና የዕዳ መግለጫ ወይም የኦዲት ሪፖርት ህጋዊ እውቅና ባለው የሂሳብ አዋቄ የተረጋገጠ መሆን አለበት፤
 3. በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ የህብት መጠን
  ሀ) ጠቅላላ የሀብት መጠን የተጣራ ሃብት እና ዕዳን የሚያካትት ሆኖ ከብር 5,000,000.00 በላይ መሆን አለበት፤
  ለ) ኢንተርፕራይዙ በብድር ካገኘው ገንዘብ ለቋሚ ንብረት ያዋለው 50 በመቶ እና በላይ መሆን አለበት፤
  ሐ)  የሃብት የዕዳ መግለጫ ወይም የኦዲት ሪፖርት ህጋዊ እውቅና ባለው የሂሳብ አዋቂ ባለሙያ ወይም በኦዲት የተረጋገጠ መሆን አለበት።
 4. የሀብት መጠን
  በአገልግሎት ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ ወይም ኢንዱስትሪ ትርፋማ መሆኑ መታየት አለበት።
 5. የገበያ መጠን በኢንዱስትሪ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ
  ሀ) ከኢንተርፕራይዙ የ አንድ አመት የሽያጭ መጠን ውስጥ በኮንስትራክሽን ንዑስ ዘርፍ የተማሩ ቢያን 55 በመቶ በላይ በብረታ ብረት እና በእንጨት ንዑስ ዘርፍ የተሰማሩ ቢያንስ ከ80 በመቶ እና በተቀሩት ንዑሳን ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ከ90 በመቶ በላይ የተገኘው ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ መሆን አለበት፤
  ለ)  ኢንተርፕራይዙ ለሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች በንዑስ ኮንትራት ቢያስ 5 ጊዜ የፈጠር፤
  ሐ)  ኢንተርፕራይዙ ምርት ለማስተዋወቅ ቢያንስ አምስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
  መ)  ኢንተርፕራይዙ በደረጃው በተዘጋጀ ባዛር ቢያንስ በአንድ አመት ሁለት ጊዜ የተሳተፈ መሆን አለበት።
 6. በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ የሀብት መጠን
  ሀ) ኢንተርፕራይዙ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የተገኘው ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ መሆን አለበት፤
  ለ)  ኢንተርፕራይዙ ምርት ለማስተዋወቅ ቢያንስ አምስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
 7. ምርታማነት
  ሀ) ኢንተርፕራይዙ ወይም ኢንዱስትሪው ለሚያመርታቸው  ምርቶችና  አገልግልቶች  ዘመናዊ  የስራ  አመራርን  የተከተለ የጥራት  ቁጥጥር  ሥርዓት  የዘረጋ  መሆን  አለበት።
  ለ)  ለገቢ ወይም ለወጪ ምርቶች የሚውሉ  ግብዓቶችን  ወይም ገቢ  ምርቶችን  የሚተካ  ወይም  ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን  ማምረት  መቻል  አለበት።
  ሐ) ከኢንተርፕራይዙ  አባላት  እና  ወይም ቋሚ ሰራተኞች  ቢያንስ 90 በመቶ ከቴክኒክና  ሙያ  ትምህርትና  ስሌጠና ተቋማት  የሙያ  ብቃት  ምዘና  ማረጋገጫ  ሰርተፉኬት  መኖር  አለበት።
 8. በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት
  ሀ) ኢንተርፕራይዙ  ወይም  ኢንዱስትሪው  ዘመናዊ  የስራ  አመራር  ዘይቤ  ተግባራዊ  ያደረገና ስትራቴጂክ  ዕቅድ መኖር አለበት፣
  ለ)  ኢንተርፕራይዙ ወይም ኢንዱስትሪው ለተሰማራበት የምርት፣  የአገልግሎት ወይም ንግድ ሥራ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ማዋሌ እና ኦዲት ማስደረግ አለበት፣
  ሐ)  የኢንተርፕራይዙ ወይም ኢንደስትሪው አባላትን  እና  ሰራተኞችን  የስራ ደህንነት ለመጠበቅ  የሥራ ልብስ እና እንደ ንዑስ ዘርፈ ዓይነት የደህንነት መሣሪያዎች የተሟለ መሆን አለበት፣
  መ)  የኢንተርፕራይዙን ወይም ኢንዱስትሪውን ሥራ ሽግግር የሚያሳይ በጽሐፍ የተዘጋጀ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል መዘጋጀት አለበት፣
  ሠ) ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ወይም ኢንደስትሪዎች ጋር ስለ ቢዝነስ ሥራ ሃሳብ ለመለዋወጥም ይሁን የጋራ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን የሚያስችል የንግድ ግንኙነት መፍጠር አለበት፤
 9. በመንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም
  ሀ) ከፌደራልና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እና ከተለያዩ ኢንስቲቱቶችና ዩኒቨርስቲዎች  የሚሰጠውን  ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን  አገልግሎት ተግባር ላይ አውሎ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣና አሠራሩንና ሌሎች ተሞክሮውን ለማስተላለፍ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  ለ) ከኢንስቲቱቶች፣ ዩኒቨርስቲዎችና ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ጋር በትብብርና በኩባንያ ውስጥ ስልጠና የተሳተፇ መሆን አለበት፡፡
  ሐ) ብድር ተጠቃሚ ከሆነ ተደጋጋሚ የብድር ተጠቃሚ ሆኖ ያልተመለሰ ውዝፍ ብድር የሌለበት መሆን አለበት::
  መ) የማምረቻ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆነ የውል ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ መሆን አለበት::
  ሠ) በመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት የሚሰጠውን የገበያ ትስስር በገባው ውል በአግባቡ እየሰራ ያለ ወይም ሰርቶ ያስረከበ መሆን አለበት፡፡
  ረ)  ወደ ኢንዱስትሪ ክላስተር ወይም ፓርክ ለመግባት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀና ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
  ሰ) ከንግድና ከልማት ባንኮች ለመበደር የሚያስችል የብድር ዋስትና ያዘጋጀ መሆን አለበት፡፡
 10. በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
  ሀ) ኢንተርፕራይዙ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስሌጠና ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖልጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጪ  ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ መሆን አለበት፣
  ለ) የምርትና አገልግሎት ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ወቅታዊና የተሻሻለ  አሠራር  ተጠቃሚ መሆን አለበት፣
  ሐ) ኢንተርፕራይዙ ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ 90 በመቶ የአካባቢ ብክለት የማያስከትሉና ኢነርጂ ቆጣቢ መሆን አለበት፤
 11. የሥራ ቦታ ምልከታ እና ከሥራ ላይ ደህንነት አኳያ
  ሀ) የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ተጠቃሚ መሆን አለበት፣
  ለ)  የደህንነት አልባሳትና ቁሳቁስ መጠቀም አለበት፣
  ሐ) የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች ማዘጋጀት አለበት፣
  መ) የተደራጀ የቁሳቁሶች አቀማመጥ መኖር አለበት፣
  ሠ) በቂ አየር እና ብርሃን ያለው የማከማቻ ቦታ ያዘጋጀ መሆን አለበት።
 12. ግዴታን ስለመወጣት
  ሀ) ኢንተርፕራይዙ የሚጠበቅበትን ዓመታዊ የገቢ ግብር መክፈል አለበት፣
  ለ ) ኢንተርፕራይዙ ዓመታዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዕድሳት ማካሄድ አለበት፣
  ሐ) ኢንተርፕራይዙ የተሠጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርተፊኬት መመለስ አለበት።

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ምስረታ ወይም ጀማሪ

ጥቃቅን/አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለምን አስፈለጉ? ጥቃቅን/ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በተለገልጋዮች ፍላጎት መነሻነት፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለመሰማራት የሚፈልጉ …