መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ድጋፍ / ለኢንተርፕራይዞች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎች
enterprise-support

ለኢንተርፕራይዞች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎች

ይህ ጽሑፍ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን ዓላማውም ኢንተርፕራይዞች ማግኘት የሚችሉትን የድጋፍ ዓይነቶች በቀላሉ ተረድተው ተጠቃሚ ኢንዲሆኑ ለማድረግ ነው።

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

በታዳጊ ወይም መስፋፋት ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ

 1. በታዳጊ ደረጃ የሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ ተከታታይና ከሥራ ባህሪያቸው ጋር የሚጣጣም የብድር አቅርቦት ያመቻቻል
 2. ኢንተርኘራይዞቹ የወሰዱትን ብድር በአግባቡ ጥቅም ላይ እዲያውሉ መደገፍና የመልካም ተበዳሪነት ታሪክ እንዲኖራቸው ይደረጋል
 3. ኢንተርኘራይዞቹ ለተበዳሪነት የሚያበቃቸው የሥራ ዕቅድ (Business Plan) ዝግጅት ድጋፍ ያደርጋል
 1. የገበያ ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ የክህሎት ማበልጸጊያና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማመቻቸት
 2. በገበያ ላይ በቀጣይነት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሙያ ብቃት እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ ድጋፍ ይሰጣል
 3. በጥናት ላይ የተመሠረተ የሥራ አመራር ሥልጠና በመስጠት የኢንተርኘራይዞቹን የቢዝነስና ሥራ አመራር ብቃት በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ያደርጋል
 4. የምርትና አገልግሎት ጥራትና ምርታማነት ሥራ አመራር ወይም ካይዘን በኢንተርኘራይዞች እንዲተገበር ማስቻል
 5. የክልል ገበያን እንዲሁም የአካባቢ ገበያ ትስስር መፍጠርና የገበያ አቅም ማሳደጊያ ድጋፍ መስጠት
 6. የገበያ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ማድረግ
 7. ተወዳዳሪነትን ማሳደግ የሚያስችል የማሽነሪ ሊዝ ድጋፍ ማድረግ
 8. የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ከከፍተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር የማስተሳሰር ሥራ መሥራት
 9. ከመካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ተሞክሮ እንዲወስዱ ማድረግ
 1. የኢንተርኘራይዞቹን የሥራ ባህሪ መሠረት ያደረገ የመሥሪያና መሸጫ ማዕከላት ማቅረብ
 2. ኢንተርኘራይዞቹ ለሚጠቀሙበት የመሥሪያና መሸጫ ማዕከላት ተመጣጣኝ የአገልግሎት ኪራይ እንዲከፍሉ ማድረግ
 3. በመሥሪያና መሸጫ ማዕከላት ውስጥ ኢንተርኘራይዞቹ በራሳቸው ሊያሟሉ የማይችሏቸውን በጋራ መጠቀም እንዲችሉ የጋራ መገልገያ አገልግሎቶችን ማጠናከር
 1. ኢንተርኘራይዞቹ በሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ማዕቀፍ ውስጥ እንዲሠሩ  መደገፍ
 2. ኢንተርኘራይዞቹ በወቅቱ ግብር እንዲከፍሉ ማድረግ
 3. በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ አስገዳጅ ደረጃዎችን እንዲያሟሉ መደገፍ

በመብቃት ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ

 1. ቀጣይነት ያለው የጥራትና ምርታማነት ብቃት ማሳደጊያ ወይም ካይዘን ሥርዓትን መትከል
 2. ገበያን  የማስፋፋት ድጋፍ ማድረግ
 3. በገበያ ውስጥ ኢንተርኘራይዞቹ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አዳዲስ የምርት ልማት ሥራዎችን እንዲያካሂዱ ማመቻቸት
 4. ኢንተርኘራይዞቹ ለተሠማሩበት ዘርፍ የሚያስፈልገውን ዘመናዊ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸት
 5. በዋናነት የውጭ ገበያ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩ ድጋፍ ማድረግ
 6. ሥራቸውን ለማስፋፋት የብድር አገልግሎት ማመቻቸት
 7. ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማመቻቸት
 8. ከከፍተኛ ኢንድስትሪዎች ጋር ተሞክሮ እና የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ ማመቻቸት
 • ኢንተርኘራይዞቹ ወደ መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ሊያሸጋግራቸው የሚያስችላቸውን የማምረቻ መሣሪያ ዓይነቶች መለየትና በመሣሪያ ሊዝ ሥርዓት እንዲጠቀሙ ማመቻቸት
 • ያለውን የሥራ ባህሪና የማምረቻ ማዕከላትን መሠረት ያደረገ የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ድጋፍ ማድረግ እና በብዛት ማዕከላትን ማስፋፋት

ለመካከለኛ ኢንተርኘራይዞች በደረሱበት ዕድገት ደረጃ ይገጥሟቸዋል ተብሎ ለሚታሰቡ ዋና ዋና ችግሮች የሚሰጡ ድጋፎች

 1. ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ የሚሸጋገሩ ኢንተርኘራይዞችን ብዛትና ዓይነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀጣይ ዓመታት ለእነዚህ ኢንተርኘራይዞች በጠቅላላው ለኢንዱስትሪ መንደሮች ከሚከለለው ቦታ ከ10 እስከ 20 ፐርሰንት የሚሆነውን በዕቅድ እንዲያዝ ይደረጋል
 2. ከአነስተኛ ወደ መካካለኛ ለሚሸጋገሩ ኢንተርኘራይዞች በኢንዱስትሪ ዞኖች ውስጥ በሚዘጋጀው ቦታ ለመሠረተ ልማት ግንባታ የሚሆን በጀት በመመደብ የተሟላ መሠረተ ልማት እንዲኖር ያደርጋል
 3. ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ የሚሸጋገሩ ኢንተርኘራይዞች ከማምረቻ ማዕከላት የመውጫ ጊዜ ከመድረሱ አስቀድሞ በኢንዱስትሪ መንደሮች ለእያንዳንዱ ኢንተርኘራይዝ እንደ ሥራው ባህሪ አስቀድሞ ቦታ እንዲዘጋጅ ይደረጋል
 4. እንደ ኢንተርኘራይዞች የሥራ ባህሪ የማምረቻ ሕንጻ ወይም  ሼድ በተመጣጣኝ የኪራይ ዋጋ ማቅረብ ወይም ራሳቸው እንዲገነቡ ቦታ ማመቻቸት፣ ይህ ድጋፍ እስኪመቻችላቸው ድረስ በጊዜ ተገድቦ በነበሩበት ሼድ የማምረት ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል
 5. እንደ ኢንተርፕራይዞቹ የሥራ ባህሪና አቅም የሚሰጣቸው ቦታ ከ500 ካሜ እስከ 2000 ካሜ እንዲሆን ይደረጋል
 6. የከተማ አስተዳደሩ በመካከለኛ ወጪ በሚያስገነባቸው ክላስተር ማዕከላት በተመጣጣኝ ኪራይ እና በጊዜ ለተወሰነ ገብተው የሚያመርቱበትን ሁኔታ እንዲመቻች ይደረጋል
 1. ኢንተርኘራይዞች ለሥራ እንቅስቃሴያቸው ማስፋፊያ የሚፈልገውን ብድር የካፒታልና መሣሪያ አቅማቸውን ለማጎልበት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተዘጋጀው ልዩ የብድር ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል
 2.  ወደ መካከለኛ የተሸጋገሩ ኢንተርኘራይዞችን መረጃ በማጠናቀር የፋይናንስ ፍላጎታቸውን ይለያል
 3. አበዳሪ ባንኮች የሚጠይቁት የብድር ቅድመ ሁኔታ ለኢንተርኘራይዞች ምቹ እንዲሆን ከአካባቢ ባንኮች ጋር መወያየትና በቅንጅት ይሠራል
 4. ኢንተርኘራይዞችን የባንክ ብድር ለማግኘት እንዲችሉ የቢዝነስ ኘላን በማዘጋጀት ረገድ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ይሰጣል
 1. ኢንተርኘራይዞቹ በተሰማሩበት መስክ ከአቅም ጋር የሚመጣጠን ሥራዎችን በመለየት በስፋት ከመንግሥት ኘሮጀክቶች የገበያ እድል ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉበትን አሠራር ይዘረጋል
 2. ከነባር፣ መካከለኛና ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ጋር የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ በቂ አቅም ያላቸውን በመለየት የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈራረሙ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል
 3. ወቅታዊ የገበያ መረጃ የሚያገኙበትን አሠራር ይዘረጋል
 1. በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች በየዘርፉ ባሉ የፌደራል ኢንስቲትዩት የክህሎት ማሻሻያ ሥልጠና የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት
 2. ኢንተርኘራይዞቹ በራሳቸው አቅም ሊገዙአቸው ያልቻሉትን የማምረቻ መሣሪያዎች ከካፒታል እቃዎች ሊዝ ኩባንያ፣ ከልማት ባንክ በኪራይ ወይም በግዥ ሊገለገሉ እንዲችሉ ማመቻቸት
 3. በአዲስ አበባ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች እንዲሁም ከምርታማነት ማሻሻያ ተቋም ጋር ኢንተርፕራይዞቹ ትስስር እንዲፈጥሩ በማድረግ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያገኙ ማመቻቸት
 4. ኢንተርኘራይዞች ለሥራቸው የሚያገለግሉ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች በፌደራልደረጃ በተቋቋሙ ኢንስቲትዩቶችና በቴክኖሎጂ ፋካልቲዎች እንዲመነጩ ክትትል በማድረግ መካከለኛ ኢንተርኘራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ
 5. የኢንተርኘራይዞችን የሂሣብ መዝገብ አያያዝና የቴክኖሎጅ ሽግገር የተሟላ እንዲሆን ተከታታይነት ያለው ሥልጠናና ድጋፍ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት እንዲያገኙ ማመቻቸት
የግብዓት አቅርቦት ችግር መኖር ኢንተርኘራይዞች በገበያ ላይ ተወዳዳሪ መሆን እንዲይችሉ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ነው። ስለሆነም ችግሩን ለማቃለል
 1. በከተማው በየወረዳው የሚገኙ ኢንተርኘራይዞች በየሥራ መስካቸው ኅብረት እንዲፈጥሩና በየዘርፉ በማኅበር እንዲደራጁ ማድረግ
 2. በየወረዳው የተመሠረቱ መካከለኛ ኅብረት በአካባቢያቸው ከሚገኙ የዘርፍ ማህበራት ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ መድረክ ማመቻቸት
 3. በየጊዜው  ኢንተርኘራይዞቹ  የሚፈልጓቸውን የጥሬ ዕቃ ዓይነቶች ዝርዝር መረጃ መሰብሰብ
 4. በተሰበሰበው መረጃ መሠረት እንደ ፍላጎታቸው ጥቅል የጥሬ ዕቃ ግዢ ለመፈፀም የሚያስችል የኢንተርኘራይዞችና ግብዓት አቅራቢዎች የመግባቢያ ሰነድ ማዘጋጀት
 1. በቀላሉ ግብዓት ለማቅረብና ምርትን ወደገበያ ለማውጣት እንዲሁም የግንባታ ዕቃዎችን ለማቅረብ የሚያስችል የመንገድ አውታር ለኢንዱስትሪ በተከለሉት አካባቢዎች አስቀድሞ ማሟላት
 2. በኢንዱስትሪ መንደሮቹ ለግንባታና ለማምረቻ የሚሆን ኃይል ማመቻቸት
 3. በኢንዱስትሪ መንደሮቹ ለግንባታ፤ ለማምረቻና ለመጠጥ የሚሆን የውሀ አቅርቦት እንዲኖር ማመቻቸት
 4. ለገበያና ለመረጃ ተደራሽነት ምቹ የሆነ የኢንተርኔትና የስልክ መሠረተ ልማት እንዲዘረጋ ማመቻቸት

ይህንንም ይመልከቱ

ለኢንተርፕይዞች ማገገሚያና መቋቋሚያ ብድር

ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕይዞችን ማገገሚያና መቋቋሚያ ፕሮጀክት ይህ ፕሮጀክት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተርካርድ …