ፋይናንስ | ብድር

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች ምዝገባ ከፈፀሙ በኋላ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙባቸውን አማራጮች በዚህ ሥር ያገኛሉ።

ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ማኅበረ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ በመቆጠብ የቁጠባን ባሕል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት፣ በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ሥራ አመራር ሃሳብ አመንጪነት እና በሠራተኞች መሥራችነት ጥቅምት 5 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ። ግሬት! ለእድገት ጽኑ መሠረት!

ተጨማሪ

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር

credit-and-saving

ተደራሽ ማኅበረ ሰብ አቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር “ትንሽ ቆጥበው ትልቅ ይሁኑ” የሚል መሪ ቃል ይዞ የተመሠረተ ተቋም ነው።

ተጨማሪ

ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በብድር ሊያገኙ ነው

አዋሽ ባንክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። ባንኩ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (ለአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት) ለማበደር ካቀደው በጀት ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ብድር ተጠቃሚ ከሚሆኑ ዘጠኝ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር ባለፈው ሐሙስ ሐምሌ 21 ቀን …

ተጨማሪ

ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም

sheger-mfi-logo

ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በብዙሃን የግል ባለሃብቶች እና በግል ኩባንያዎች የተቋቋመና በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ፣ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተሞክሮና እውቀት ባካበቱ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ነው። በአሁኑ ወቅት ቅርንጫፎቹን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በሆነችው ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) እና በሌሎች በክልሉ በሚገኙ ከተሞች በማስፋፋት የኅብረተ ሰቡን …

ተጨማሪ

አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.

agar-microfinance

አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. መጋቢት 9 ቀን፣ 1996 ዓ.ም.  ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ አግኝቶ የባንክ የፋይናንስ  አገልግሎት ለማያገኙ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች የቁጠባና የብድር አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው። ተቋሙ ከተመሠረተ ከ17 ዓመታት በላይ በሥራው ላይ የቆየ ሲሆን አጥጋቢ የሥራ ልምድ ከማካበቱም በላይ በአሁኑ ወቅት ቅርጫፎቹን ወደ ሃያ …

ተጨማሪ

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ማኅበር አዋጅ መሠረት በቁጥር 147/1998 ሲሆን ሕጋዊ ሰብእናውን  ከአራዳ ክፍለ ከተማ የኅብረት ሥራ ማኅበር ማደራጃ ቢሮ እና ከንግድ ሚኒስቴር በጥር 2005 ዓ.ም. ፍቃድ አግኝቶ በሥራ ላይ ይገኛል። አሚጎስ በቀዳሚነት የሚንቀሳቀሰው የአባላት መደበኛ ቁጠባ እና አክሲዮን በመሰብሰብ የተሻለ የብድር አገልግሎት በማቅረብ …

ተጨማሪ

አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም

አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአዋጅ ቁጥር 40/1988 ዓ.ም. መሠረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት በስድስት የአክሲዮን ባለቤቶች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለመስጠት እ.አ.አ ጥር 27 ቀን፣ 2000 ዓ.ም. በከተማው ያለውን ሥራ አጥነት ለመቅረፍና ድህነትን ለመቀነስ ዓላማ አድርጎ የተቋቋመ ተቋም ነው። በአሁን ሰዓት በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 626/2009 እየሠራ የሚገኝ እና …

ተጨማሪ

መክሊት የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ.

meklit-logo

መክሊት የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዋጅ ቁጥር 40/96 ከዚያም ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 626/2009 መሠረት በከተማና በገጠር ለሚኖሩ ምርታማ ዜጎች በተለይም የባንክ አገልግሎት ዕድል ላላገኙ ሴቶች እና ወጣቶች የብድር፤ የቁጠባና አነስተኛ የመድን ዋስትና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ሲሆን ላለፉት 19 ዓመታት አገልግሎቱን በጥራትና በብቃት እያቀረበ የሚገኝ …

ተጨማሪ

ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ለሥራ ተነሻሽነት ያላቸው ዜጎች በተለይም የባንክ አገልግሎት ዕድል ለተነፈጉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት የተቋቋመ ተቋም ነው። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ …

ተጨማሪ

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም

harbu-mfi

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በ2005 ዓ.ም. በፋሲሊቴተር ፎር ቼንጅ (መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም) ድጋፍ አማካኝነት የተቋቋመ ተቋም ነው። ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የዕሴት ሰንሰለት ልማት እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽነት በመደገፍ የግብርና ምርታማነትን እና የግብርና ግብይትን ለማሳደግ ያለመ ነው። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው …

ተጨማሪ