መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ድጋፍ / የመስሪያ ቦታዎች ድጋፍ
shed-addisababa-mse

የመስሪያ ቦታዎች ድጋፍ

መንግስት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከሚሰጣቸው ድጋፎች አንዱ፣ በራሱ (በመንግስት) በጀት ህንጻ፣ ወርክ ሾፕ እና ሼዶችን በመገንባት ለዕድገት ተኮር ዘርፎች በዝቅተኛ የኪራይ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ነው።

የመስሪያ ቦታዎቹ የሚከተሉት መልኮች ሊኖራቸው ይችላል፡-

 • ማምረቻ ህንጻ
 • ወርክ ሾፖች
 • ሼዶች (ማምረቻ)
 • መሸጫ ሕንፃዎች፣ ተለጣፊ ሱቆች፣ መደብሮች፣ ኮንደሚኒየም ሱቆች እና ሼዶች

የመስሪያ ቦታዎች ዓይነትና የሚሰጡት አገልግሎት

በማምረቻ ህንጻ የሚመረቱ የምርት አይነቶች፡-

 1. ልብስ ስፌት ስራ
 2. ሸማ ሥራ
 3. ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ሥራዎች
 4. ጥልፍ ሥራ
 5. ሹራብ ስራ
 6. ልዩ የፈጠራ ሥራዎች
 7. ህትመትና የወረቀት ስራዎች

በወርክ ሾፖች የሚመረቱ የምርት ዓይነቶች፡-

 1. የእንጨት ስራዎች
 2. ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ስራዎች
 3. ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ማምረት ስራ
 4. የሽመና ሥራ
 5. የሹራብ ሥራ
 6. የልብስ ስፌት፤ ዲዛይንና የጥልፍ ሥራ፤

በሼዶች የሚመረቱ የምርት ዓይነቶች፡-

 1. የኮንስትራክሽን ግብዓት ምርት
 2. የእንጨት ስራዎች
 3. ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ስራዎች
 4. የከተማ ግብርና ስራዎች ማለትም የወተት ከብት እርባታና ከብት ማድለብ፣ በግና ፍየል ማርባትና ማድለብ፣ ዶሮ እርባታ፣ እንጉዳይ ማምረት
 5. የእንስሳት መኖ ማቀነባበር
 6. የአግሮ ፕሮሰሲንግ ስራዎች
 7. የደረቅ ምግብና የባልትና ውጤቶች ምርት
 8. ፕላስቲክ፣ ብረታ ብረት እና ወረቀት መልሶ መጠቀም
 9. የዕደ ጥበብ ስራዎች ወይም በእጅ የሚመረቱ ምርቶች
 10. ሳሙናና ዲተርጀንት ማምረት
 11. ከረሜላ ማምረት
 12. ቀለም እና ቫርኒሽ ማምረት
 13. የህትመትና ወረቀት ስራዎች

በመሸጫ ሕንፃዎች፣ ተለጣፊ ሱቆች፣ መደብሮች፣ በኮንደሚኒየም ሱቆች እና ሼዶች ውስጥ የሚገቡ የምርትና አገልግሎት ዓይነቶች፡-

 1. የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች
 2. የቆዳ ውጤቶች
 3. የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ውጤቶች
 4. የባልትና ውጤቶች
 5. ካፌና ሬስቶራንት
 6. የዕደ ጥበብ ውጤቶች
 7. ሳሙናና ዲተርጀንት ውጤቶች
 8. የህትመት፣ ማስታወቂያና የወረቀት ስራዎች
 9. የኤሌክትሮኒክስና ሶፍት ዌር ልማት፣ የጥገና ስራዎችና የጽሕፈት አገልግሎት
 10. የእንስሳት ተዋፅኦ
 11. የውበት ሳሎን አገልግሎት
 12. አትክልትና ፍራፍሬ
 13. የአግሮ ኘሮሰሲንግ ውጤቶች
 14. የባህላዊ ዕደ ጥበብና ጌጣጌጥ ሥራ ውጤቶች
 15. ለጥቃቅንና አነስተኛ የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃ አቅርቦት
 16. ፕላስቲክና የፕላስቲክ ውጤቶች

ለተጠቃሚዎች የሚሰጡ የመስሪያ ቦታዎች ስፋት መጠን

በማምረቻ ህንፃ የሚሰጥ የቦታ ስፋት መጠን፤

 1. ለልብስ ስፌትና ለቆዳና ቆዳ ውጤቶች 6 ካሬ ሜትር በሰው ሆኖ ለጨርቅ መቅደጃ፤ ለመተኮሻ ሥራዎች ለጋራ መገልገያ የሚሆን 12 ካሬ ሜትር ቦታ በወለሉ ላይ የሚዘጋጅ ሆኖ የጋራ መጠቀሚያው በእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ የኪራይ ውል ላይ ተካቶ ይከፈላል።
 2. ለሸማ ሥራ 6 ካሬ ሜትር፣ ለጥልፍ ሥራ 4 ካሬ ሜትር፣ ለጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርት ለግብዓትነት የሚውሉ ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች 5 ካሬ ሜትር በሰው ይሰጣል።
 3. ለካፌ እና ሬስቶራንት 32 ከሬ ሜትር ለ5 ሰው እና ከዚያ በላይ ላለው ኢንተርፕራይዝ የሚሰጥ ይሆናል።

በማምረቻ ወርክ ሾፕ የሚሰጥ የቦታ ስፋት መጠን፡-

 1. በአዲስ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ለሚመጡ ስራ ፈላጊዎች የአባላት ብዛታቸው 10 ለሆኑ የስራ እቅዳቸው አዋጪነት ታይቶ ግማሹ 240 ካሬ ሜትር ተለክቶ የሚሰጥ ይሆናል።
 2. በአዲስ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ለሚመጡ ስራ ፈላጊዎች የአባል ብዛት 20 /ሃያ/ ከሆነ ሙሉ ወርክሾፕ 480 ካሬ ሜትር የስራ እቅዳቸው አዋጪነት ታይቶ በክፍለ ከተማው በኩል እየተወሰነ እንዲተላለፍ መደረግ አለበት።
 3. ሰላሳ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ስራ ፈላጊዎች ቋሚ የስራ ዕድል ፈጥሮ ለሚመጣ የግል ኢንተርፕራይዝ ለፈጠረው ቋሚ የስራ ዕድል ለአንድ ዓመት ተከታታይ ወራት ለገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ደመወዝ የከፈለበት ፔይሮል፣ የንግድ ስራ ዕቅድ ፣ ማሰልጠኛ ማዕከል ለመሆን እና ልምድ ለማካፈል የግዴታ ውል ለመግባት ፈቃደኛ ለሆነ የግል ኢንተርፕራይዝ ሙሉ ወርክሾፕ 480 ካሬ ሜትር በቢሮው ማኔጅመንት ኮሚቴ ተወስኖ ሊተላለፍ ይችላል።

shed-addisababa-sme-2

በማምረቻ ሼድ ለሚመረቱ ምርቶች የሚሰጥ የቦታ ስፋት፡-

 1. ለእንጨትና ብረታ ብረት፣ ቀለምና ቫርኒሽ፣ ሚስማር ስራ፣ ለብሎኬት፤ የድንጋይ ማስዋብ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ፣ ለመልሶ መጠቀም፣ለሳሙናና ዲተርጀንት  ስራዎች፣ ለህትመት ስራዎች 120 ካሬ ሜትር ለ5 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 2. ለፕሪካስት ምርት ማምረት 240 ካሬ ሜትር 5 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 3. የደረቅ ምግብና የባልትና ውጤቶች፣ ለአግሮፕሮሰሲንግ ስራዎች፣ ከረሜላ ማምረት 120 ካሬ ሜትር ለ5 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 4. ለባህላዊ ዕደ-ጥበብና ጌጣጌጥ ሥራዎች ወይም የቀንድና የሸክላ ስራ፤ ቀርከሀ፤ ስጋጃ፤ የከበሩ ድንጋዮችና የብር፣ የነሐስ ጌጣጌጥ ስራ እና የአሻንጉሊት ስራዎች 120 ካሬ ሜትር ለ5 እና ከዚያ በላይ አባል ላለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 5. ለወተት ከብት እርባታና ለከብት ማድለብ 240 ካሬ ሜትር ለ5 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 6. ለበግና ፍየል ማድለብና እርባታ፣ ዶሮ እርባታ፣ እንጉዳይ ማምረትና መኖ ማቀነባበሪያ 120 ካሬ ሜትር ለ5 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 7. ከአእምሯዊ ንብረት ተቋም ዕውቅና ተሰጥቷአቸው ልዩ የፈጠራ ስራ ይዘው ለሚቀርቡ ኢንተርፕራይዞች በሚያቀርቡት የንግድ ስራ ዕቅድ መሠረት ቋሚ የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ በማረጋገጥ በአንዱ የፈጠራ ስራ ብቻ በቢሮው ማኔጅመንት ተገምግሞ ውሳኔ ሲያገኝ  ሊተላለፍ ይችላል።

በመሸጫ ህንጻ የሚሰጥ የቦታ ስፋት፡-

 1. ለአትክልትና ፍራፍሬ ሽያጭ፣ ሶፍት ዌር ልማትና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራዎች 6 ካሬ ሜትር በሰው ይሰጣል።
 2. ለእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች 32 ካሬ ሜትር ለ3  እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 3. ለቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ለጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ለአግሮ ኘሮሰሲንግ ውጤቶች፣ የደረቅ ምግብና የባልትና ውጤቶች፣ ለዕደ ጥበብ ውጤቶች፣ ሳሙናና  ዲተርጀንት ምርት እና ለማስታወቂያና ህትመት ስራዎች 4 ካሬ ሜትር በሰው ይሰጣል።
 4. የውበት ሳሎን አገልግሎት 20 ካሬ ሜትር ለ3 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 5. ለኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ለካፌና ሬስቶራንት አገልግሎት 32 ካሬ ሜትር ለ5 ሰው እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 6. ለእንስሳት ተዋጽኦ መሸጫ 18 ካሬ ሜትር ለ3 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።

working-space-addisababa-mse

ተለጣፊ ሱቅ፣ ኮንቴነር፣ መደብርና ኮንደሚኒየም ንግድ ቤቶች ላይ የሚሰጥ የቦታ ስፋት፡-

 1. በመደብር ላይ የሚጠቀም ኢንተርፕራይዝ 4 ካሬ ሜትር በሰው ይሰጣል።
 2. ኮንቴነር እና ተለጣፊ ሱቅ ላይ የሚጠቀም ኢንተርፕራይዝ 2 ካሬ ሜትር በሰው ይሰጣል።
 3. የኮንደሚኒየም ንግድ ቤቶች ላይ የሚጠቀም ኢንተርፕራይዝ ለ5 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ይሰጣል።
 4. የፈጠራ ስራ ያላቸው ለሌሎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ በልዩ ሁኔታ በቢሮው ማኔጅመንት ውሳኔ ሲሰጥ ከዚህ ቁጥር ያነሰ አባል ቢኖራቸውም እንዲሰጣቸው ሊያደርግ ይችላል።

የመስሪያ ቦታ ለማግኘት ማሟላት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

በማምረቻ ህንጻ፣ ወርክ ሾፕ፣ በመሸጫ ህንጻና ሼድ የሚሰጠው የቦታ ስፋት እንደተጠበቀ ሆኖ የመስሪያ ቦታ ማስፋፊያ የሚደረግለት ኢንተርፕራይዝ በድጋፍ ሰጪ ስራ ክፍል የሚከተሉት መስፈርቶችን ማሟላቱ ሲረጋገጥ የሚሰጥ ይሆናል፡-

 1. የተዘጋጀው የንግድ ስራ እቅድ የሚፈጥረው ተጨማሪ የስራ ዕድል ዕቅድ አዋጪነቱና ተግባራዊነቱ ሲረጋገጥ፣
 2. በገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የአንድ ዓመት የቋሚ ሰራተኛ ደመወዝ መክፈያ ፔሮል መኖሩ ሲረጋገጥ፤
 3. ከሚመለከተው ተቋም የሚያስገባው አዲስ የመስሪያ ማሽን የሚይዘው የቦታ ስፋት መጠን የሚገልጽ ማስረጃ ሲቀርብ፤
 4. የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
 5. ማስፋፊያ የመስጠት ውሳኔው በወረዳው ጽ/ቤት የፕሮሰስ ከውንስል የድጋፍ ውሳኔ ሀሳብ ሲያቀርብ በክፍለ ከተማ ፕሮሰስ ካውንስል እየተወሰነ እንዲተላለፍ በማድረግ ለቢሮ ሪፖርት ይላካል።
 6. የያዘው መስሪያ ቦታ ከ5 ዓመት በታች የተጠቀመ መሆኑ ሲረጋገጥ

ይህንንም ይመልከቱ

enterprise-support

ለኢንተርፕራይዞች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎች

ይህ ጽሑፍ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን ዓላማውም ኢንተርፕራይዞች ማግኘት የሚችሉትን …