መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ሙሉጌታ ሰማኸኝ በሽር የኅትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

ሙሉጌታ ሰማኸኝ በሽር የኅትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሙሉጌታ ሰማኸኝ በ2009 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኅትመት እና የማስታወቂያ ሥራዎችን ይሠራል።


ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች

  • ብሮሹሮች
  • ፖስተሮች
  • ቢል ቦርዶች
  • ቢዝነስ ካርድ
  • ላይትቦክስ እና ሌሎች የኅትመት ሥራዎች
  • የማስታወሻ ደብተሮች

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ዋጋ በከፊሉ

  • ባነር በካሬ በ150 ብር ይሠራል
  • ቢልቦርድ ከሆነ ደግሞ የሚሠራው ሥራ ላይ የሚኖረውን የብረት የገበያ ዋጋ በመጨመር ይሠራል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ሙሉጌታ ድርጅቱን ከመመሥረታቸው በፊት ፎቶ ቤት ተቀጥረው ወደ አራት ወር ገደማ ሠርተዋል። በዚህ ጊዜም የኅትመት ሥራ ጥሩ እንደሆነ ስለተረዱ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሙያ በመማር ቤታቸው በግል ቀለል ያሉ ሥራዎች (ለምሳሌ ቢዝነስ ካርድ የመሳሰሉ ሥራዎችን) በመሥራት ነበር የጀመሩት። ቀስ በቀስ ሥራው እያደገ ሲመጣ የሥራ ቦታ በመከራየት ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራው ገብተዋል።

ድርጅቱ በአሁን ሰዓት ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ሲሆን፤ ያሸነፋቸውንም ጨረታዎች በብቃት አጠናቅቆ ያስረክባል። በዚህ ዓመት ብቻ አርባ ስድስት የሚጠጉ ጨረታዎችን ማሸነፍ ችሏል። ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ብቻ በነበረው የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር ምክንያት ሠርቶ ማስረከብ ሳይችል ቀርቷል።

ድርጅቱ ካጠናቀቃቸው ሥራዎች መካከል፦ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሥራ፣ የገቢዎች ሥራ እንዲሁም ብዙ ጤና ጣቢያዎች ላይ ሥራዎችን ሠርቷል።

ድርጅት ሲመሠረት በአምስት ሺህ ብር ካፒታል ሲሆን፣ አሁን ለዐሥር ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። የካፒታል መጠኑም ወደ አራት መቶ ሺህ ብር ማድረስ ችሏል። ይህም አቅም የሚመጡ ማናቸውም ዓይነት የኅትመት ሥራዎችን በሚገባ እና በብቃት መወጣት እንዲችል አድርጎታል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት እንቅስቃሴ ቀንሶ ነበር፤ ቢሆንም ለሠራተኞችም ሥራ ባይኖርም ደመወዝ ሲከፍሉ ነበር። ለዚህም ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የመዝገብ ሥራ ሠራተኞች በፈረቃ እየገቡ እንዲሠሩ በማድረግ ነበር የኮቪድን ጊዜ ያሳለፉት።

ምክር እና እቅድ

አቶ ሙሉጌታ የጨረታ አገልግሎቱ ላይ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል “በፊት ጨረታውን ያወጡ መሥሪያ ቤቶች(ድርጅቶች) ስም (Company Name) ኮፒ ማድረግ ስለማይቻል በመጻፍ ነበር ‘search’ እናደርግ የነበረው፤ አሁን ግን ኮፒ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል። ይህ ደግሞ በጣም ጥሩና ሥራችንን በከፍተኛ ሁኔታ ያቀለለ ነው።”

አሁን ወደ ኅትመት ሥራ የሚገቡ ሰዎች የገበያው ሁኔታ ማለት የጥሬ እቃ መጥፋት በኪሳራ ራሱ እንዳይሠራ  አድርጓል። የእቃ መጥፋት በጣም አስቸጋሪ ነው። ሥራው እንደታሰበው እንዳይሠራ አድርጓል፤ ትርፋማም ለመሆን አስቸጋሪ ነው። ለምሳሌ የወረቀት ዋጋ በሦስት እጥፍ ጨምሯል። አስቸጋሪ ነገሮች ስለበዙ አዲስ የሚገቡ ሰዎች ጠንካራ እና ታጋሽ እንዲሁም ምንም ቢመጣ አልፈው የሚሠሩ መሆን አለባቸው።

ድርጅቱ ወደ ፊት ከኅትመት ሥራው በተጨማሪ የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት እቅድ አለው። ለምሳሌ እንደ ፖስታ ማሸጊያ ማምረት እንዲሁም ደግሞ ወረቀት የማምረት እቅድ አላቸው። በቅርብ ጊዜ እቅድ ደግሞ የጎደሉ ማሽኖችን ለሟሟላት ከአዲስ ካፒታል ጋር በመሆን አዳዲስ እና ዘመናዊ ማሽኖችን ለማስገባት እየሠራ ይገኛል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ሀሌታው ሀ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ድርጅት የተመሠረተው በአቶ ዮናታን ታደሰ እና ሦስት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኅትመት …