መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ማኅበር አዋጅ መሠረት በቁጥር 147/1998 ሲሆን ሕጋዊ ሰብእናውን  ከአራዳ ክፍለ ከተማ የኅብረት ሥራ ማኅበር ማደራጃ ቢሮ እና ከንግድ ሚኒስቴር በጥር 2005 ዓ.ም. ፍቃድ አግኝቶ በሥራ ላይ ይገኛል። አሚጎስ በቀዳሚነት የሚንቀሳቀሰው የአባላት መደበኛ ቁጠባ እና አክሲዮን በመሰብሰብ የተሻለ የብድር አገልግሎት በማቅረብ የተሳለጡ የማህበራዊ ግንኙነቶች እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በአባላትና በማህበሩ እንዲኖሩ ማድረግ ነው።

በአሁኑ ሰዓት አሚጎስ ከ1700 በላይ አባላት ሲኖሩት ወደ 70 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ሀብት አለው። በብድር መጠን እስከ 120 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ለ700 አባላት እስከ አሁን ያቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ብር 60 ሚሊዮን  ከ300 በላይ አባል ተበዳሪዎች ጋር በሥራ ላይ ይገኛል። የአባልነት ጥቅም ከፍ ለማድረግ ደግሞ በ650 ሺህ ብር ደግሞ በ5 የተመረጡ ባንኮች አክሲዮን ገዝቶአል።

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

በአባላቱ ቁጥር አንድ ተመራጭ የሆነ የገንዘብ አገልግሎት ሰጪ ማኅበር መፍጠር ነው።

ተልዕኮ

ጥራት ያለው የገንዘብና ኤሌክትሮኒክ-ገንዘብ (e-finance) አገልግሎት በማቅረብ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሥራዎች በመሥራት የአባላትን ኑሮ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ ነው።

ዓላማ

የአባላትን አቅም መሠረት ያደረገ መደበኛ ተቀማጭ በመሰብሰብ ለአባላት ተደራሽ፣ አዋጭ፣ ምቹ እና ቀልጣፋ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት አባላትን የተሻለ መተዳደሪያ እንዲኖራቸው ማገዝ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል
  • አባላት በተናጠል በመሥራት ሊወጡዋቸው ያልቻሉትን ችግሮች በጋራ መፍታት
  • አባላት ያላቸውን ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት በማቀናጀት የተሻለ ውጤት ማግኘት
  • በአባላት ዘንድ በራስ መተማመንን ማጎልበት
  • አነስተኛ የአገልግሎት ዋጋ በማቅረብ አባላት ምርታቸው ወይም አገልግሎታቸው የተሻለ የገበያ ዋጋ አንዲያገኝ ማድረግ
  • በአባላት ዘንድ ገንዘብ የመቆጠብና የመበደር ባህል ጎልብቶ ኢንቨስትመትን ማስፋፋት
  • አባላት አትራፊ በሆኑ የንግድ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ እንዲሁም የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ መርዳት
  • ለአባላት የብድር የሕይወት ማህበራዊ መድን ዋስትና መስጠት
  • በአባላቱም ሆነ በአካባቢ የሚገኝ ኅብረተ ሰብ ማኅበራዊ ጉዳይ ውስጥ ተሳታፊ መሆን

ተግባር

  • ለአባላት ገንዘብ ማበደር እና ከነወለዱ መሰብሰብ
  • አባላት ተበድረው አዋጭ በሆነ የሥራ ዘርፍ እንዲሰማሩ የምክርና ሥልጠና አገልግሎት መስጠት
  • ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ማፍራትና ማስተዳደር
  • የአካባቢ ልማት ላይ መሳተፍ
  • ስለ አባላትና ማኅበሩ እድገት ጥናት እና ምርምር ማካሄድ
  • ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ተመሳሳይ ተግባራት ማከናወን

ዕሴቶች

አሚጎስ የሚከተሉት ዕሴቶች አሉት
  • ብቃት ያለው አመራር
  • ለጋራ ዓላማ በኅብረት መሥራት
  • አርቆ ለውጤት ማቀድ
  • ተጠያቂነት
  • መተሳሰብ
  • ታማኝነት እና አንድነት ናቸው።

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • መደበኛ ቁጠባ
  • የፍቃደኝነት ቁጠባ
  • የልጆች / ታዳጊዎች ቁጠባ
  • የጊዜ ገደብ ቁጠባ
  • የትምህርት ቁጠባ
  • የቢዝነስ ቁጠባ
  • የቤት ቁጠባ
  • የመኪና ቁጠባ
  • እና ሌሎች ለተለያየ ዓላማ የሚውሉ የቁጠባ ዓይነቶች
  • የግል ብድር
  • የቢዝነስ ብድር
  • የመኪና ብድር
  • የትምህርት ብድር
  • የቤት ብድር
  • እና ሌሎች ለተለያየ ዓላማ የሚውሉ የብድር አይነቶች
  • የአጭር ጊዜ ብድር፦ ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር
  • የመካከለኛ ጊዜ ብድር፦ ከአንድ ዓመት እስከ ሦስት ዓመት
  • የረዥም ጊዜ ብድር፦ እስከ ሰባት ዓመት
  • ተቋሙ ከግንቦት 8 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የተስተካከለ እና ያልዘገየ ተቀማጭ ላለው አባል ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር (ብር 2,200,000) የነበረውን የብድር ጣሪያ ወደ ሶስት ሚሊዮን ብር (ብር 3,000,000) አሳድጓል።
  • ከዘጠኝ ፕርሰንት እስከ አሥራ ዘጠኝ ፕርሰንት
  • የአባል ቁጠባ
  • የራስ የፍቃደኝነት ቁጠባ
  • የሌላ ሰው የደመወዝ ዋስትና
  • የባንኮች የሼር ሰርተፍኬት
  • የመኪና ዋስትና
  • የቤት ዋስትና
  1. መልካም ባሕሪ እና የተስተካከለ ቁጠባ ያለው
  2. መልካም የብድር ታሪክ ያለው
  3. እንደ ብድሩ ዓይነት ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች ይኖራሉ
አንድ አባል በድርጅቱ አባል ከሆነ በኋላ ማድረግ የሚጠበቅበት ነገሮች
  1. ያለማቋረጥ መቆጠብ
  2. ለዓላማ መበደር
  3. ተጠቅሞ፣ አትርፎ በስምምነት ጊዜው መመለስ
የአሚጎስ አባል ለመሆን ከታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት ያስፈልጋል።
  1. እድሜ ዐሥራ ስምንት አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ
  2. የመመዝገቢያ ፎርም መሙላት
  3. ትንሹን መነሻ የአክሲዮን መጠን 1000 ብር ግዢ መክፈል
  4. ለልጆች ቁጠባ መነሻ ብር 100 መክፈል
  5. ሁለት 3*4 መጠን ያላቸው ፎቶግራፎች
  6. የመታወቂያ ኮፒ/ መንጃ ፈቃድ/ ፓስፖርት
  • በአጭር ጊዜ ከሁለት ሳምንት ጀምሮ ብድር የሚያቀርብ መሆኑ
  • በአንጻራዊነት ከፍ ያለ ብድር እስከ 2.2 ሚሊዮን ብር የሚሠጥ መሆኑ
  • ረዘም ላለ ጊዜ (እስከ 7 ዓመት) የብድር ጊዜ መስጠቱ
  • የተሻለ ወለድ ማሰቡ(ለታዳጊዎች)
  • ብድሩ ወርሃዊ ቅናሽ መኖሩና ሲዘጋም ቀሪው ወለድ ሳይከፈል ብድሩን መዝጋትና ተጨማሪ ብድር መውሰድ መቻሉ
  • በተቀማጭ ላይ የሚሰላ የብድር ብዜቱ ከፍ ያለ መሆኑ
  • ለተለያዩ አላማ የሚውል ብድር ማቅረቡ
  • ከፍ ያለ ዓመታዊ ትርፍ ለአባላቶች ማከፋፈል መቻሉ
  • በሰራተኞች ላይ የጓደኝነታዊ አቀራረብ መኖሩ
  • በማህበሩ አባላት የተቋቋሙ ሪል እስቴት የአክሲዮን እና የቤት ባለቤት እንዲሆኑ እድል መኖሩ እንዲሁም ሌሎችም

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር አድራሻ

ከአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ ፊት ለፊት ብሩክ ሕንጻ 3ኛ እና 5ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።

ስልክ

  • 0111 26 76 57
  • 0930 08 22 30
  • 0930 08 68 30

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …