መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / እቴጌ ዳቦ እና ብስኩት

እቴጌ ዳቦ እና ብስኩት

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሳሙኤል በለጠ፣ በሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ መሥራች አባላት በ2010 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች ምግብ እና መጠጥ ሲሆኑ በአሁን ጊዜ በዳቦ፣ ኩኪስ እና ጨው ምርቶች ላይ በስፋት እየሠራ ይገኛል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች በተለያየ መጠን እና ዋጋ ለገበያ ያቀርባል፤ የምርቶቹ ዓይነትና ዋጋቸው ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል።

የዳቦ ምርቶች

 • ስላይስ ዳቦ፣ ኖርማል ዳቦ እና ድፎ ዳቦ ናቸው
 • ከዚህ በተጨማሪ ደንበኛ በሚፈልገው መጠን ምርቱን ያመርታል
 • የዳቦ ዋጋ፦ ኖርማል ዳቦ ሶስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም፤ ትልቁ ስላይስ ዳቦ ሃያ ብር

ድርጅቱ የሚያመርታቸው የኩኪስ ምርቶች በሁለት የተከፈሉ ሲሆን እነሱም ኖርማል ኩኪስ እና እስፔሻል ኩኪስ ናቸው ዋጋቸው ደግሞ እንደሚከተለው ነው።

 • ኖርማል ኩኪስ፦ ከአርባ ሰባት ብር እስከ ዘጠና ብር ድረስ
 • ስፔሻል ኩኪስ፦ ከመቶ ሃያ ብር እስከ መቶ ስልሳ ብር ድረስ ለገበያ ያቀርባል።

የጨው ምርቶች

 • አንድ ኪሎ ግራም ጨው፦ ሃያ ብር
 • ስምንት መቶ ግራም ጨው፦ አሥራ ሰባት ብር
 • አምስት መቶ ግራም ጨው፦ አሥራ አራት ብር

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ሳሙኤል ይህን ድርጅት ከመመሥረታቸው በፊት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ሠርተዋል። ለምሳሌ ለሆቴሎች የእንስሳት ተዋፅኦ አቅራቢ በመሆን ሠርተዋል። በሥራው በነበረው አለመግባባት ያንን ሥራ በመተው የዳይፐር እና ሞዴስ ምርት በሃገራችን ላይ ለማምረት በማሰብ ጥናት ሲጀምሩ የነበራቸው ካፒታል በቂ አልነበረም። ስለዚህ በዚህ ካፒታል ምን ብንሠራ ያዋጣናል የሚለው በደንብ ካጠኑ በኋላ የዳቦ ሥራ ጥሩ አማራጭ እንደሆነ በማየት የዳቦን ሥራ ጀመሩ።

የድርጅቱ አመሠራረት ሂደት

 • አባላቱ የዳቦ ሥራ ለመሥራት ከወሰኑ በኋላ ወደ መንግሥት በመሄድ የሥራ ቦታ ተቀበሉ።
 • በመቀጠል ደግሞ አዲስ ካፒታል በመሄድ ያላቸውን ቦታ በማሳየት የሚፈልጉትን ማሽን ዋጋ ዐሥር ፕርሰንት በመቆጠብ ማሽኑን አስገቡ።
 • ከዛም በኋላ ወደ አዲስ ብድር እና ቁጠባ በመሄድ ለሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ በመበደር ወደ ሥራ ገቡ።

ድርጅቱ ሥራ ሲጀምር በአንድ ቀን የነበረው የማምረት አቅም ከአንድ ሺህ እስከ ሁለት ሺህ ዳቦ ሲሆን አሁን የድርጅቱ የማምረት አቅም በቀን ወደ አስር ሺህ ዳቦ አድጓል። በተጨማሪም ያለው የሰው ኃይል ከሰባት ሠራተኞች ወደ ዐሥራ ሁለት ሠራተኞች ከፍብሏል።

ድርጅቱ ምርቱን ከተጠቃሚዎች በተጨማሪ ለሁለት ትምህርት ቤቶች በየቀኑ ወደ ስድስት ሺህ የሚጠጋ ዳቦ ያቀርባል፤ በተጨማሪ ለጴጥሮስ ሆስፒታል እና ስፖርት አካዳሚ በየቀኑ ምርቱን እያቀረበ ይገኛል። ከዚህ የበለጠ የመሥራት አቅም አለው ሥራ ቢመጣም በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ይሠራል።

የድርጅቱ መሥራች አባላት ልምድ ያካበቱት አንድ ራሳቸው በፊት ቤተሰቦቻቸው የዳቦ ሥራ ይሠሩ ነበር ከቤተሰብ በመማር፤ በመቀጠል ደግሞ ሥልጠናዎችን በመውሰድ እንዲሁም ከጓደኞቻቸው ጋር ሻይ ቡና ሲሉ በመነጋገር እና ሃሳብ በመቀያየር ነው። እንዲሁም ድርጅቱ በዐሥራ አምስት ቀን ወይም በወር ስለተሠራው ሥራ መሻሻል ስላለበት ነገር ምን መሻሻል አለበት ምን ቢስተካከል ጥሩ ነው የሚሉትን ነገሮች በመነጋገር ራሱን ያሳድጋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ሥራ ቀንሶ ነበር። አቶ ሳሙኤል የቤት ኪራይ እና የማሽን ኪራይ የጊዜ ገደብ እረፍት በመጠየቅ፤ እንዲሁም ሠራተኞችን ከራሳቸው ኪስ በመደጎም ነው ያሳለፉት።

ድርጅቱ ከኮቪድ በተጨማሪ በጣም ያስቸገረው ነገር የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ነው። በጣም አስቸጋሪ እና ምሬት ውስጥ የሚከት ነው፤ በዚህ ምክንያት ራሱ ለመዝጋት የደረሰበት ሁኔታዎችም ነበሩ ምክንያቱም ሥራ የሚሠራው በኤሌክትሪክ ነው። ይህ ነገር መፈታት የሚችልበት ሁኔታ ቢፈጠር ጥሩ ነው ብለዋል።

ምክር እና እቅድ

“አዲስ ቢዝነስ የሚጀመር ሰው ሲያማክር ሰዎች አሁን እኮ ሥራ የለም በጣም ቀንሷል እኛ ራሱ ልንዘጋ ነው የሚሉ ይበዛሉ። እነዚህ ሰዎች አላወቁትም እንጂ በዚህ የሥራ ዘርፍ እጥረት አለ እያሉት ነው። ስለዚህ ማንም ሰው ምንም ሥራ መሥራት ቢፈልግ እንደ አቅሙ መሥራት የሚፈልገውን የሥራ ዘርፍ ዞር ዞር ብሎ አይቶ ምን ብሠራ ያዋጣኛል? ምን መሥራት እችላለሁ? ብሎ አጥንቶ ቢጀምር ጥሩ ነው። ላማክር ቢል ራሱ የሚያማክር ሰው ብዙም ስለሌለ። ስለለዚህ ገንዘብ አለኝ የለኝም? አውቀት አለኝ የለኝም? እውቀት አለኝ ገንዘብ የለኝም? ገንዘብ አለኝ እውቀት የለኝም? ገንዘብም እውቀትም አለኝ? የሚሉትን ነጥቦች አይቶ ቢጀምር ጥሩ ነው።  ስለ ገበያ ጥናት ሜክሲኮ አካባቢ ሥልጠና የሚሰጥ ድርጅት አለ፤ እዛ በመሄድ የአንድ  ወር ወይም የሦስት ወር ስልጠና በመውሰድ አስፈላጊውን ልምድ እና ተሞክሮ ማካበት ይቻላል” ይላሉ የድርጅቱ መሥራች።

ማንም ሰው ቢዝነስ ኖረውም አልኖረውም ጥሩ ስነ-ምግባር ሊኖረው ይገባል። ሌላው ከሠራተኛ ጋር እኩል ከፍ ዝቅ ብሎ መሥራት መቻል አለበት። ከሠራተኞች ጋር ጥሩ ስነ-ምግባር የሚያሳይ ከሆነ እነሱም ሲመለከቱ ፀባያቸው እንደሱ ይሆናል። ጠንካራ እና ትጋት ያላቸው ሠራተኞች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።

የወደፊት እቅዳቸው በፊት ያሰቡትን የዳይፐር ሥራ ቢጀምሩ በጣም ደስተኛ ናቸው፤ በመቀጠል ደግሞ የታሸጉ ምግቦችን ማምረት ለመጀመር እቅድ አላቸው።

ድርጅቱ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት ካለፈው ዓመት ጀምሮ የሚጠቀም ሲሆን በዚህ ዓመት ካለፈው በይበልጥ እየተጠቀመ ይገኛል።  በቅርቡ ዘውዲቱ ሆስፒታል በጨው ጨረታ አሸንፏል። በዳቦም አሸንፎ ነበር ግን በስህተት ነው ጨረታው የወጣው በሚል የዳቦው ጨረታ ተሰርዟል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ። 

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …