መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / አስቴር ከበደ ኅትመት እና ማስታወቂያ እንዲሁም ተያያዥ ሥራዎች

አስቴር ከበደ ኅትመት እና ማስታወቂያ እንዲሁም ተያያዥ ሥራዎች

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አዲስ አንለይ የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ በዋናነት የሚሠራው የሌብል ኅትመት ሥራዎችን ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይ የኅትመት ሥራዎችን ይሠራል።

ድርጅቱ የሚሰጣቸው የኅትመት አገልግሎቶች

  • የተለያዩ ብሮሸሮች
  • ካላንደር እና የካላንደር ላይ ኅትመት
  • ደረሰኞች
  • መጽሔቶች
  • በራሪ ወረቀቶች
  • ማስታወሻ ደብተሮች
  • የማዳበሪያ ላይ ኅትመት
  • አጀንዳዎች
  • በባልትና ዘርፍ ፌስታሎች ላይ የሽሮ፣ በርበሬ እና ሌሎችም የምስል ላይ የኅትመት አገልግሎት መስጠት
  • እስክርቢቶ፣ ኮፍያ፣ ቲሸርት እና ሌሎችም እቃዎች ላይ የኅትመት አገልግሎት
  • መስታወት እና መኪና ላይ ዘመናዊ (3D/ሶስት ማእዘን/) ማስታወቂያ መሥራት
  • ላይት ቦክስ፣ አቅጣጫ ጠቋሚዎች እና
  • የሌብል ሥራዎችን በሻምፖ፣ የምግብ ዘይት እና ሌሎች እቃዎች ላይ የሌብሊንግ አገልግሎት ይሠጣል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ አዲስ የኅትመት ሥራ በልጅነታቸው ከቤተሰባቸው ጋር የመሥራት አጋጣሚ ስለነበረ እዛ ይሠሩ ነበር። ይህም ከገንዘብ ይልቅ ሥራውን እንዲወዱት አድርጓቸዋል፤ ምክንያቱ ደግሞ ሁልጊዜ አዳዲስ ሥራ ስለሚመጣ እና ይህ ደግሞ አዳዲስ ነገሮችን እንዲማሩ እና የተለያዩ ነገሮችን እንዲሞክሩ ስለሚያደርጋቸው ነው። በዚህ ሂደት ሌሎች ነገሮችን መማር አስችሏቸዋል። ሁለተኛው ደግሞ የሠሩትን ሥራ ውጤት ሲያዩ ይበልጥ ይደሰቱ ነበር። ስለሆነም ከቤተሰብ ጋር የነበራቸውን ልምድ ኅትመት ትምህርት ጋር በመቀላቀል ሥራቸውን በመቀጠል በኅትመት ሥራ የዐሥር ዓመት የሥራ ልምድ ማዳበር ችለዋል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በሁለት መንገድ በመክፈል ነው፤ አስቸኳይ እና ኖርማል። አስቸኳይ ሥራ ሲመጣ ሦስት ቀን ወይም አራት ቀን የሚፈጅ ሥራ አስፈላጊውን የሰው ኅይል በመቅጠር በአንድ ቀን ይጠናቀቃል። ከዚህ ጋር ዐብሮ በኅትመት ሥራ ላይ ያልተቀረፈ የነበረ እና አሁንም ያለ ችግር የመብራት መቆራረጥ እንደሆነ የድርጅቱ መሥራች ጠቅሰዋል። ይህም አንዳንዴ ከደንበኛ ቅሬታ እንደሚያመጣ ጠቅሰዋል።

ድርጅቱ አገልግሎቱን ካቀረበላቸው ተቋማት ጥቂቶቹ

  • ሶራ ሻምፖ እና ኮንዲሽነር
  • አብሮ ሂል ማኑፋክቸሪንግ
  • ሸሙ ሳሙና
  • ጊዮን በረኪና
  • ረጲ ሳሙና

ድርጅቱ የተመሠረተው በሃምሳ ሺሕ ብር ካፒታል ሲሆን አሁን ድርጅቱ የካፒታል አቅሙን ወደ ዘጠኝ መቶ ሺሕ ብር ማሳደግ ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ ለአምስት ቋሚ ዜጎች እና ለዐሥር ጊዜያዊ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። ለዚህም እድገት ተጠቃሽ የሆኑ ነገሮች ታጋሽ መሆን፣ አዳማጭ ማለት ደንበኛ ምን እንደሚፈልግ በደንብ መረዳት እና ምንም አይነት ነገር ቢል ታግሶ ማሳለፍ፤ ይህ ማለት ደግሞ ከደንበኞች ጋር ጥሩ እና ጤናማ የሆነ ግንኙነት መፍጠር ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለማንኛውም ድርጅት እድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።

ድርጅቱ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ እና በማሸነፍ በሚገባ ሥራውን አጠናቅቆ ዐምስት ለሚደርሱ ድርጅቶች አስረክቧል። አሁን ደግሞ ማርች ስምንት (March 8) ትምህርት ቤት (ቦሌ ጃፓን አካባቢ የሚገኝ) ጨረታ አሸንፎ እየሠራ ይገኛል። ሌሎችም ገና ያልተከፈቱ ጨረታዎችም ውጤት በመጠበቅ ላይ ይገኛል።

አቶ አዲስ ምንም ዓይነት ሥራ ለማስኬድ አራት መሠረታዊ ነገሮች እንዳሉ ተናግረዋል። እነሱም የምርቱ ጥራት (quality)፣ ዋጋ፣ የማድረሻ ጊዜ እና የሰዎች ፍላጎት ማወቅ በጣም ወሳኝ ነገር እንደሆነ ጠቅሰዋል። እነዚህን ነገሮች ማወቅ ለአንድ ቢዝነስ ማደግ ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።

ድርጅቱ ምርቱን በቴሌግራም እና ፌስቡክ እንዲሁም ሰው በሰው ያስተዋውቃል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል። ከዚህም ጋር አያይዘው የድርጅቱ መሥራች ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም ከወጣቶች እንዲሁም ጨረታ መጠቀም ደግሞ በእድሜ ጠና ካሉ ሰዎች ጋር ሥራን መሥራት እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ድርጅቱ በኮቪድ ጊዜ በጣም ከባድ ሁኔታዎችን ነበር ያሳለፈው። ይህም ፋብሪካዎች ሥራ አቁመው ስለነበር እቃ እንደ ልብ አይገኝም። በዚያን ወቅት የድርጅቱ ሠራተኞች የተለያዩ ሥራዎችን ጎን ለጎን በመሥራት እና በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ የማገገሚያ ብድርም በመውሰድ ቢዝነሱን በመደገፍ ነው የኮሮና ጊዜን ያሳለፉት።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ አሁን ከሁለት ባንኮች ጋር አብሮ ለመሥራት ሂደቱን እየጨረሰ ይገኛል። በዚህም የኅትመት ሥራውን አስፍቶ ለመሥራት እና በኅትመት ትልቅ ፋብሪካ በመክፈት በኅትመቱ ዘርፍ ተጽእኖ የሚፈጥር እና ታዋቂ ድርጅት የመሆን እቅድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ ከውጭ የሚመጡ ግን ሀገር ውስጥ መሠራት የሚችሉ እቃዎችን የማምረት እቅድ አለው። ለምሳሌ የውሃ ላስቲክ፣ እነዚህን ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት ብዙ የሥራ እድል ለመፍጠር እቅድ አለው።

“አዲስ ወደ ሥራው የሚገቡ ሰዎች ፍቅር ሊኖራቸው ይገባል። ቀጥሎ ደግሞ ትዕግስት እና ዘወትር የሥራ ቦታ ላይ መገኘት አስፈላጊ ነው። ይህም ችግሮች እንዳይፈጠሩ ያደርጋል። ችግሮች ከተፈጠሩ እንዳንድ ችግሮች ኪሳራ ውስጥ ሊከትቱ ስለሚችሉ፣ በተቻለ መጠን ሥራ ቦታ መገኘት ባለመገኘት ይፈጠር የነበረውን ችግር መቅረፍ እንዲችል ያድርጋል።” ስለዚህ ሥራ ቦታ መገኘት አስፈላጊ ነው እንደሆነ አቶ አዲስ ጠቅሰዋል።

አቶ አዲስ ስለ 2merkato.com የጨረታ አገልግሎት የሚከተለውን ብለዋል “ጥሩ ነው፤ በፊት ከነበረው በጣም ተሻሽሏል። ድሮ እኔ ቤተሰብ ጋር ስሠራ በኢሜይል ብቻ ነበር ጨረታ የሚደርሰን። አሁን ግን በቴሌግራም፣ በአፕልኬሽን እና በዌብም እንደልብ ጨረታ መፈለግ እንድንችል አድርጎናል። ይህ ደግሞ ከነበረው የሆነ እርምጃ እንደተጓዘ ያሳያል። ጥሩ ነው እኔ በጣም ተስማምቶኛል፤ ወድጄዋለሁ ብለዋል።”

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …