መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ኔዘርላንድስ ከኢትዮጵያ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር ሆነች

ኔዘርላንድስ ከኢትዮጵያ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር ሆነች

የ2012 በጀት ዓመት የወጪ ንግድ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ኔዘርላንድስ ቀዳሚ ሀገር ሆናለች ተባለ፡፡

አበባ፣ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የኤሌክትሪክ ውጤቶች፣ ጫማ፣ ቆዳ፣ ማርና ሰም፣ የቅባት እህሎች፣ የአልኮል መጠጦች፣ ጫት፣ ሻይ፣ ብረትና የመሳሰሉትን ከኢትዮጵያ በመቀበል 320,162.35 የአሜሪካን ዶላር በማስግኘት ቀዳሚ ሀገር ሆናለች፡፡

export-chart

ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቡና ጫማ፣ አበባ፣ የቆዳ ውጤቶችን፣ የቅባት እህሎችን እና ሌሎች ኢትዮጵያ ወደ ውጪ የምትልካቸውም ምርቶች በመቀበል አሜሪካ በሁለተኛነት ስትቀመጥ 295,809.17 የአሜሪካን ዶላር ማስገኘት ችላለች፡፡

ሶማሊያ 291,855.37 የአሜሪካን ዶላር ፣ ሳውዲ አረቢያ 214,652.57፣ ጀርመን 174,283.18 የአሜሪካን ዶላር በማስገኘት እንደ ቅደም ተከተላቸው ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …