አዋጭ ለአነስተኛ የንግድ ሥራ እስከ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ድረስ የሚያበድር ሲሆን ለንግድ መኪና ደግሞ እስከ ብር 2አዋጭ ለአነስተኛ የንግድ ሥራ እስከ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ድረስ የሚያበድር ሲሆን ለንግድ መኪና ደግሞ እስከ ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን) ድረስ ያበድራል።
ለመበደር ምን ማድረግ አለብኝ?
ለአነስተኛ ንግድ ሥራ ብድር አባል ሆኖ ቢያንስ ለ6 (ስድስት) ወራት በተከታታይ መቆጠብ ይኖርበታል። የሚበደረውን ገንዘብ መጠን 25% (አንድ አራተኛ) መቆጠብ አለበት።
የንግድ መኪና ለመግዛት ለሚሰጥ ብድር አባል ሆኖ ቢያንስ ለ 6 (ስድስት) ወራት በተከታታይ መቆጠብ ይኖርበታል ። የሚበደረውን ገንዘብ መጠን 25% (ሃያ አምስት ፕርሰንት) መቆጠብ አለበት።
አዋጭ በነኝህ ዋስትናዎች ለአነስተኛ ንግድ እንዲሁም ለንግድ መኪና ያበድራል:- በቁጠባ ዋስትና፣ በደመወዝ ዋስትና እና በአባል ዋስትና፣ በንብረት ዋስትና (ለየመኪና እና የቤት ብድር የሚገዛው ንብረት ራሱ ዋስትና ይሆናል)
የአዋጭ የዋና መሥሪያ ቤት፣ የቅርንጫፎች አድራሻ እና ስልክ ቁጥሮች
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ዋና መሥሪያ ቤት | አዲስ አበባ፣ አዋሬ አጋር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 11 557 97 98 |
ዋና መሥሪያ ቤት | አዲስ አበባ፣ አዋሬ አጋር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 11 557 88 89 |
ዋና መሥሪያ ቤት | አዲስ አበባ፣ አዋሬ አጋር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 11 557 98 99 |
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
አብይ ቅርንጫፍ | ሜክሲኮ ህብረት ባንክ ዋና መ/ቤት | +251 11 126 05 06 |
ሥላሴ ቅርንጫፍ | ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ | +251 111 26 01 92 |
ስታዲዮም ቅርንጫፍ | የሓ ሲቲ ሴንተር 1ኛ ፎቅ | +251 115 58 25 55 |
ስድስትኪሎ ቅርንጫፍ | ሊደርሺፕ ሕንፃ ምድር ላይ | +251 118 68 55 98 |
ልደታ ቅርንጫፍ | ኤ አይ ኤ የገበያ ማዕከል ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 115 30 30 98 |
ሰዓሊተ ምህረት ቅርንጫፍ | ድራር ሞል 1ኛ ፎቅ | +251 116 73 2011 |
ጀሞ ቅርንጫፍ | ኤክስፕረስ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ | +251 113 69 86 83 |
አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ | ጃምቦ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ | +251 111 54 74 40 |
ቦሌ ቅርንጫፍ | ቦሌ መድኃኒዓለም ሸገር ህንፃ ፊት ለፊት አስረስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ | +251 116 67 19 23 |
ቃሊቲ ቅርንጫፍ | ቃሊቲ ቶታል ካፍደም ህንፃ 2ኛ ፎቅ | +251114715955 |
መገናኛ ቅርንጫፍ | መሰረት ደፋር ሕንፃ ምድር | +251 116 68 66 53 |
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ | ቱሪስት ሰፈር ፣ ሚና ቤና ሕንፃ 1ኛ ፎቅ | +251 118 12 42 42 |
ጫንጮ ቅርንጫፍ | አዳም ሕንፃ ምድር ላይ | +251 118 12 43 44 |
ሰበታ ቅርንጫፍ | ሳምቡሳ ቤት አካባቢ ኦፍታና ህንፃ ፊትለፊት | +251 113 38 45 23 |
ሆለታ ቅርንጫፍ | ቀልቤሳ ሆቴል አጠገብ ሃና ፋርማሲ ያለበት ህንፃ 1ኛ ፎቅ | +251 112 61 07 77 |
አዳማ ቅርንጫፍ | ዋርካ ፊት ለፊት ኪዳነ ምህረት ሥጋ ቤት አጠገበ ኤ.ኤች.ዋይ ሆቴል 2ኛ ፎቅ | +251 222 12 00 88/89 |
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ሐዋሳ ቅርንጫፍ | አሮጌው መናኸሪያ ትዕግስት ሆቴል አጠገብ 1ኛ ፎቅ | +251 462 12 24/26 |
ጠቃሚ መረጃዎች ስለ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የሕብረት ሥራ ማኅበር
ራዕይ
በ2030 ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኀብረት ሥራ ማኀበር ሆኖ ማየትተልዕኮ
አባላት በማስተባበር ተገቢውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በፍላጎት ላይ የተመሠረተ በሀገራችን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ላይ አስተዋፅኦ በማበርከት የተሻለ የቁጠባ፣ ብድር እና ሌሎች የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ የኑሮ ደረጃቸውን ማሻሻል።ዓላማ
- ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም በመፍጠር ባንክ ነክ አገልግሎት ለአባላት በመስጠት የገቢ መጠናቸውን ማሳደግ እና የደህነት መጠንን መቀነስ
- የተለየ እገዛ የሚፈልጉ ሴቶችን እና ወጣቶችን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን በማበረታታት በገቢ ማስገና ሥራ ላይ ተሰማርተው ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ማበረታታት እና ድጋፍ ማድረግ
- በሀገራችን መንግሥት ባስቀመጠው የልማት ዕቅዶች ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ
- ለአባላት፣ አመራር፣ አቅጥር ሠራተኛ እና ለህብረተሰቡ ተከታታይ ሥልጠና እና ትምህርት በመስጠት በኅብረት ሥራ ማህበሩ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ማሳደግ
- ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለአባላት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የአገልግሎቱ ተደራሽነት ማስፋት
ተ.ቁ. | የብድር ዓይነት | የብድር መጠን በብር እስከ | ብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በመቶኛ (%) | ብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በብር | ብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠንና ጊዜ በተከታታይ | የብድር ወለድ መጠን በመቶኛ (%) | የብድር መመለሻ ጊዜ እና ገደብ |
---|---|---|---|---|---|---|---|
1 | መደበኛ ብድር - ለማኅበራዊ ጉዳይ | 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ) | 25% | 150,000 (መቶ ሃምሳ ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 13.5% | 3 ዓመት |
2 | መደበኛ ብድር - ለአነስተኛ ንግድ | 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) | 25% | 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 13.5% | 3 ዓመት |
3 | ለቤት መኪና ብድር | 1,500,000 (አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን) | 25% | 375,000 (ሦስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 14.5% | 5 ዓመት |
4 | ለንግድ መኪና ብድር | 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን) | 25% | 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 14.5% | 5 ዓመት |
5 | ለቤት ብድር መያዣ መሥሪያ ማደሻ | 3,000,000 (ሦስት ሚሊዮን) | 25% | 750,000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 15.5% | 10 ዓመት |
- በቁጠባ ዋስትና
- በደመወዝ ዋስትና እና በአባል ዋስትና
- በንብረት ዋስትና የሚሰጥ ብድር
- የመኪና ብድር እና የቤት ብድር የሚገዛው ንብረት ራሱ ዋስትና ይሆናል።
- ማንኛውም ብድር የሚሰጠው የተበዳሪው የመክፈል አቅም ያገናዘበና ባቀረበው ዋስትና መጠን ብቻ ነው።
- የባንክ ወይም የኢንሹራንስ አክሲዮን
- የማኅበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 500 (አምስት መቶ) ወይም ከ30 ቀናት ገቢ ውስጥ 10% ሲሆን ይህን ቁጠባ ሳያቋርጥ በየወሩ መቆጠብ ይኖርበታል፣
- እያንዳንዱ አባል ከመነሻ የቁጠባ መጠን በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል።
- አንድ አባል የቆጠበውን መደበኛ ቁጠባ ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ይወስዳል። ነገር ግን ተጨማሪ/የፍላጎት ቁጠባውን አስገዳጅ በሆነ ጊዜ ወጪ አድርጎ መጠቀም ይችላል።
የቁጠባ አገልግሎት
- መደበኛ ቁጠባ
- የፍላጎት ቁጠባ
- የልጆች ቁጠባ
- የቤት ቁጠባ
- የመኪና ቁጠባ
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ
- በተመጣጣኝ ወለድ የብድር አገልግሎት መስጠት
- አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
- የትምህርት፣ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት
የብድር አገልግሎት
- መደበኛ ብድር
- የንግድ ሥራ ማስጀመሪያ እና ማስፋፊያ ብድር
- የቤት መግዣ፣ መስሪያና ማደሻ ብድር
- ለንግድ አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ ብድር
- ለግል አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ ብድር
በተጨማሪ ደግሞ
- አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
- የትምህርት፣ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት ናቸው
- የአዋጭ በሕብረት ሥራ ማኅበሩ የሥራ ክልል ነዋሪ የሆነና የነዋሪነት ማረጋገጫ ያለው
- ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
- የሕብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በመሆን በኅብረት ሠርቶ በኅብረት ለማደግ ዓላማ ያለው
- በሕብረት ሥራ ማኅበሩ ደንብና መመሪያ ተገዢ ለመሆን ፈቃደኛ የሆነ/ነች
- በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
- የታደሰ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- አንድ አመልካች አባል እንዲሆን ሲፈቀድለት የመመዝገቢያ ለአንድ ጊዜ ብቻ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የተወሰነውን የገንዘብ መጠን ይከፍላል።
- ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ በስንብት ወቅት ለአባላት ተመላሽ አይሆንም።
- የአባሉ ቁጠባ እና እጣ መጠን
- የኅብረት ሥራ ማህበር አባል የሆነ ለዋስትናነት
- ለዋስትናነት የቀረበ የቋሚ ቅጥር ሰራተኛ ደመወዝ ህጋዊ ደብዳቤ
- የንብረት ዋስትና ካርታ ወይም ሊብሬ
- የንብረት እግድ አግባብ ካለው አካል ጋር የቀረበ ማረጋገጫ
- በህጋዊ አካል የቀረበ የአክሲዮን ሰነድ ለዋስትናነት
- ያላገባ ወይም ያገባ ስለመሆኑ የሚገልጽ የጋብቻ ሰርተፍኬት
- የተበዳሪው እና የተበዳሪ ባለቤት፣ ዋስ የሆነ ግለሰብ እና የሚስት/ የባል የታደሰ የቀበሌነት መታወቂያ
- በተበዳሪ የተፈረመ ገቢያቸውን የሚገልጽ ዝርዝር መግለጫ
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ቁጥር እና የዘመኑ ግብር የተከፈከ ማረጋገጫ
- የንግድ እንቅስቃሴያቸውን የሚገልጽ የንግድ ሥራ እቅድ ወይም መግለጫ
- የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1,000.00 ሲሆን አንድ አባል መግዛት ያለበት ዝቅተኛው የዕጣ መጠን ሁለት ነው።
- አንድ አባል በጠቅላላ ጉባዔ ተወካይ አባላት እንዲሸጥ ከተወሰነው የዕጣ መጠን ከ10 በመቶ በላይ ድርሻ ሊኖረው አይችልም።
- በሕ/ሥ/ማኅበሩ የዕጣ እና ቁጠባ ምጥጥን ሥራ ይከናወናል
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አዋጭ በሚያዘጋጀው ብሮሹር እና በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።