መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በ2000 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቶ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት በመስጠት የገጠሩንና የከተማውን ማኅበረ ሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በመሥራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።

እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

የጊዜ ገደብ ቁጠባ

ይህ የቁጠባ ዓይነት ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኝ ሲሆን ከብር 5,000 ጀምሮ በድርጅቱ ቆጥበው ለ6ወር እና ከዚያ በላይ በውል ካስቀመጡ በዓመት ከ10% እስከ 14% ወለድ ያገኛሉ።

ልዩ የልጆች ትምህርት ቁጠባ

ይህ የቁጠባ ዓይነት ወላጆች ልጆቻቸውን ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩበት እና ሥራ ፈጥረው ራሳቸውን የሚያስችሉበት ሲሆን ውል ገብተው በየወሩ ሲቆጥቡ 10% ወለድ የሚያስገኝ ነው።

መደበኛ ቁጠባ

ይህ ቁጠባ ደንበኞች ከሚያገኙት ገቢ አቅማቸው በፈቀደ መጠን በድርጅቱ ሲቆጥቡ 8% ወለድ የሚያስገኝ ሲሆን ቁጠባቸውንም በፈለጉት ጊዜ ማውጣት ይችላሉ።

የሳጥን ቁጠባ

ይህ ቁጠባ ደንበኞች ከሚያገኙት ገቢ በቁጠባ ሳጥን ውስጥ ባጠራቀሙት ቁጠባ መጠን በዓመት 8% ወለድ ያገኛሉ። ቁጠባቸውን በፈለጉት ጊዜ ማውጣት ይችላሉ።

የግብርና የቡድን ብድር

ይህ ብድር ለአርሶ አደሮች የግብርና ግብዓት መግዣ በቡድን ዋስትና የሚሰጥ ብድር ሲሆን መጠኑም ከብር2,000 እስከ 15,000 ነው።

የንግድ ሥራ የግል ብድር

ይህ የብድር ዓይነት ንግድ ፈቃድ ላላቸው ነጋዴዎች በቤት፣ በመኪና፣ በባንክ አክሲዮን ወይም በደመወዝ ዋስትና የሚሰጥ ነው። የብድር መጠኑም ከብር 20,000 እስከ 280,000 ነው።

የንግድ ሥራ የቡድን ብድር

ይህ የብድር ዓይነት የንብረት ዋስትና ማቅረብ የማይችሉ እና በአነስተኛ የንግድ ሥራ የሚተዳደሩ የከተማው ቋሚ ነዋሪዎች በቡድን ተደራጅተው የእርስ በርስ የጠለፋ ዋስ በመሆን ሲቀርቡ የሚሰጥ ነው። የብድር መጠኑም ከብር 2,000 እስከ 30,000 ነው።

የሠራተኛ ብድር

ይህ የብድር ዓይነት ለቋሚ የመንግሥት ወይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ሕጋዊ ድርጅት ሠራተኞች መሥርያ ቤታቸው ለተበዳሪው እና ለዋስ በሚጽፍላቸው የደብዳቤ ዋስትና የሚሰጥ ነው። የብድር መጠኑም ከብር 4,000 እስከ 100,000 ነው።

የግብርና ሥራ የግል ብድር

ይህ የብድር ዓይነት ለታታሪና ሞዴል አርሶ አደሮች በመሬታቸው የባለቤትነት ይዞታ የመጠቀም መብት ዋስትና የሚሰጥ ነው። የብድር መጠኑም ከብር 20,000 እስከ 50,000 ነው።

የሶላር ኢነርጂ ብድር

ይህ የብድር ዓይነት የመክፈል አቅም ያላቸው ሰዎች የመብራትና ቴሌቪዥን ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰጥ ነው። የብድር መጠኑም ከብር 4,000 እስከ 30,000 ነው።

እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. አድራሻ እና ስልክ

ዋና መሥርያ ቤት

አዲስ አበባ፣ ጀርመን አደባባይ፣ መካነኢየሱስ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር

    • +251 11 3206451
    • +251 11 3206452
    • +251 11 3206453

Email

eshetmfi@gmail.com

P.O. Box

23923 ኮድ 1000፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በአካል በመሄድ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …