መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ

ውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ

ውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ የተመሠረተው በ 2011 ዓ.ም በአቶ ካሊድ አብዲ እና ሁለት መሥራች አባላት ነው። ውብ ፊኒሺንግ አጠቃላይ የፊኒሽንግ ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ነው። ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት አቶ ካሊድ ከጓደኞቻቸው ጋር ለሦስት አመት በትውውቅ (በሰው በሰው) ሥራውን ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ ተደራጅተን በሙሉ አቅም ብንሠራ ደግሞ የተሻለ ተጠቃሚ እንሆናለን በማለት ነበር ድርጅቱን የመሠረቱት።

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች

  • የሴራሚክ ሥራዎች
  • የአሉሚኒየም ሥራዎች
  • የቤቶች እድሳት
  • የኮንቴክስትራ የውጭ ቀለም ቅብ
  • የግራናይት የውጭ ቀለም ቅብ
  • የኳርትዝ ቀለም ቅብ
  • የውስጣዊ ዲኮር ቀለም ቅቦች
  • የዳሞስ ኮራቶ የጣልያን ቀለም ቅብ
  • ዲኮሮች
  • ፍሬም ቦርዶች እና ፓርቲሽን ሥራዎችን ይሠራል።

ማስተዋወቅ እና መስፋፋት

ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት መሥራቾቹ  በተለያየ የሥራ ዘርፍ ተሠማርተው ሲሠሩ ነበር። ለምሳሌ በሹፍርና ሙያ፣ በሴልስ እና ማርኬቲንግ ሥራዎችን ሲሠሩ ቆይተዋል። ወደ ፊኒሺንግ የሥራ ዘርፍ የገቡትም ምክንያት ሴልስ ሥራ ሲሠሩበት የነበረው ድርጅት የፊኒሺንግ እና ኮንስትራክሽን ሥራዎች የሚሠራ ድርጅት ስለነበረ በሂደትም ሥራውን እና ሙያውን በደንብ ከተማሩ በኋላ በዘርፉ ጥሩ የሥራ እድል አለ እንዲሁም የሀገራችን ገበያ ወደ ኮንስትራክሽን ሥራ ስለሚያተኩር በራሳችን ብንሠራ ይበልጥ ውጤታማ እንሆናለን ብለው በማሰብ ነው በራሳችው ሥራውን የጀመሩት። ድርጅቱ በሦስት መሥራች አባላት ተመሥርቶ በአሁኑ ጊዜ ከአስራ አምስት እስከ ሃያ ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በዋናነት በሰው በሰው ሲሆን በመቀጠልም ማስታወቂያዎችን የገበያ ትስስር ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚያመቻቸው በkefta.merkato.com፣ ፌስቡክ እና የመሳሰሉ ሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም ነው። እንዲሁም ጨረታዎችን በከፍታ በኩል በመከታተል  ከመቶ በላይ ሳይቶችን በአዲስ አበባ፣ ወራቤ፣ ጎንደር፣ ደብረ ዘይት እና ሀረር በጥራት እና ቃል በገባው የጊዜ ገደብ መሰረት አስረክቧል።

የድርጅቱ መሥራቾች አዳዲስ ፈጠራዎች በመጠቀም ከሀገር ውጭ የሚሠሩ ሥራዎች ወደ ሀገራቸው በማምጣት ጥሩ የአሠራር እና የአካሄድ አይነቶች በመጠቀም አዳዲስ ነገሮችን በመጨመር ጥሩ ውጤት በማምጣት ተሳክቶላቸዋል። ለዚህም ማሳያ የተበላሸ ወይም አቤቱታ የቀረበበት ሳይት ምንም የለም።  ሳይቶች በማጠናቀም አቅሙ በፊት አንድ ሳይት የነበረው አሁን ሠላሳ ሳይቶችን ማጠናቀቅ ይችላል። እንዲሁም ሲመሠረት ከነበረው መነሻ ካፒታል መቶ ሀያ ሺህ ብር አሁን ብዙ የሥራ ማሽኖችን በማሟላት አንድ ሚሊዮን ብር ካፒታል ደርሶአል ።

ውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ ሲጀመር ብዙ መሰናክሎች የነበሩ ሲሆን ለምሳሌ ሥራ (ሳይት) ማግኘት ከባድ ነበር። የገንዘብ እና የጥሬ እቃ እጥረት እንዲሁም የዋጋ አለመረጋጋት በጣም አስቸጋሪ ነገሮች ነበሩ። ለምሳሌ አንድ ሥራ ለመሥራት የሚወጣው ዋጋ እቃው ለመግዛት ወጪ ሲደረግ ይጨምራል ይህ ደግሞ ከደንበኛ ጋር ያጋጫል፣ ኪሳራ ያስከትላል፤ ነገር ግን የሚቀጥለው ይሻላል እያልን እየተማርንበት ከቤትም ከራሳችን ኪስ በማምጣት አልፈነዋል ይላሉ አቶ ካሊድ። ሌላው ችግር ደግሞ ሰው ቃል የገባውን ገንዘብ በተገቢው ጊዜ አለመክፈል፣ መቀነስ እና ብሎም መከልል ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው። ነገር ግን የዓላማ ጽናት፣ የማደግ እና የመለወጥ ዓላማ ድርጅቱ ውስጥ ስላለ ለእነ አቶ ካሊድም ያለው አማራጭ መቀጠል እና መቀጠል ስለነበር ነው ድርጅቱ ውጤታማ ሊሆን የቻለው። ድርጅቱ በአሁን ሰዓት ምንም አይነት የአቅም ችግር የለበትም ማንኛውንም ሥራ ማከናወን ይችላል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ ድርጅቱ ላይ ተፀዕኖ ነበረው፤ ምክንያቱም ሰው ቤቱ እንዲኬድበት አይፈልግም አብዛኛው ሰው ገቢው ቀንሶ ስለነበር ገንዘብ የሚያወጣበትን ነገር አይፈልግም ነበር። የሚሠሩ ሳይቶች ቀንሰው ነበር፤ የሚታደሱ የሚኖሪያ ቤቶች ምንም አልነበሩም። ቢሆንመ በወረርሽኙ ወቅት ድርጅቱ ቀድሞ የያዛቸው ሥራዎች ስለነበሩ ብዙም አንደሌሎች ድርጅቶች አልተጎዳም።

ምክር እና እቅድ

አዲስ ሰዎች ወደ ፊኒሺንግ ሥራ ሲገቡ ሥራውን ማወቅ አለባቸው፣ ካላወቁ ስለሥራው ትክክለኛ እውቀት ስለማይኖራቸው ሥራውን ያበላሹታል ይህ ደግሞ የገንዘብ፣ የንብረት፣ የሥራ እና የጊዜ ብክነትን ያመጣል በተጨማሪም ደንበኛው ያበሳጫል። ይህ ማለት ሌላ ሥራ አያገኙም ማለት ነው ስለዚህ ሥራውን በሚገባ ማወቅ ወሳኝ ነገር ነው።

ድርጅቱ ወደ ፊት በሚቀጥሉ አምስት አመታት ትልቅ የፊኒሽኒግ ድርጅት ለመሆን እና ኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ በመግባት እንዲሁም በፊኒሽንግ ዘርፍ ትልቅ ብዙ ሥራዎችን የሚሠራ እና ብዙ ዲፓርትመንቶች ያሉት ትልቅ ድርጅት ለመሆን አቅድ አለው።

ድርጅቱ አቶ ዘሩባቤል ሽለሺ በሥራ፣ እውቀት እና በድርጅቱ ምሥረታ ላይ እና ሙያውን ስላስተማሯቸው የድርጅቱ መሥራች አባላቶች አመስግነዋል።

ስለ ውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ የበለጠ መረጃ ለማግኘት https://www.2merkato.com/directory/34632-wib-finshing-solutions ይመልከቱ ።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …