መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / 2merkato ሥራችንን ያለንበት ቦታ ድረስ ያመጣልናል – ቢዝነስ ሕትመት እና ማስታወቂያ

2merkato ሥራችንን ያለንበት ቦታ ድረስ ያመጣልናል – ቢዝነስ ሕትመት እና ማስታወቂያ

ቢዝነስ ማስታወቂያ የተመሠረተው በ2004 ዓ.ም ሲሆን፣ የተመሠረተውም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ቢሆነኝ ዘመነ ነበር። ድርጅቱ ሲመሠረት ሥራው ብዙም አስቸጋሪ አልነበረም። ቢዝነስ ማስታወቂያ የሰባት ዓመት ጊዜ ያስቆጠረ ቢሆንም በጥሩ ሁኔታ መንቀሳቀስ የጀመረው ግን በ2009 ዓ.ም ነው።

ምሥረታና ዕድገት

የድርጅቱ መሥራች የሆኑት አቶ ቢሆነኝ ወደ ሕትመት ሥራ ከመግባታቸው በፊት ኢንጂነር የመሆን ህልም ነበራቸው። ነገር ግን የዩኒቨርስቲ ተማሪ እያሉ በተፈጠረው አጋጣሚ የኢንጂነሪንግ ትምህርታቸውን በመተው ወደ ሕትመት ሙያ ሊገቡ ችለዋል። አቶ ቢሆነኝ ወደ ሕትመት ሙያ እንዴት ሊገቡ እንደቻሉ ሲናገሩም የዩኒቨርስቲ ተማሪ እያሉ አንድ ጓደኛቸው ስለ ሕትመት ሥራ ሲነግራቸው ለምን በትርፍ ጊዜ አልሞክረውም ብለው የጀመሩት። እንደጀመሩም ለዐሥራ አምስት ቀናት ከሠሩ በኋላ የነበረው የሥራው አሠራር ከደንበኛ ጋር የሚያጋጭ ስለነበረ ሥራውን ለማቆም ተገደዱ። በሠሩበት በአሥራ አምስት ቀናት የሥራ ጊዜ ውስጥ ሥራውን ስለወደዱት እና ሥራው በየቀኑ አዲስ ስለሆነ እንዲሁም ከተለያዩ ሰዎች ጋር ስለሚያገናኝ በራሳቸው መንገድ ከደንበኛ ጋር በማያጋጭ መልኩ ለመሥራት ወሰኑ።

አቶ ቢሆነኝ ተቀጥረው ሲሠሩበት የነበረውን ሥራቸውን ካቆሙ በኋላ በሰላሳ አምስት ብር እና በፊት ሲሠሩበት ከነበረው ቦታ በተሰጣቸው የቢዝንስ ካርድ ቢዝነስ ማስታወቂያን ሊመሠርቱ ችለዋል። ሥራውንም ሲጀምሩ የሕትመት ሥራ በመፈልግ ሥራ ሲያገኙም ወደ ባለሙያ ጋር በመውሰድ (outsource) በማድረግ ይሠሩ እንደነበር ያስታውሳሉ። በመቀጠል ደግሞ የ ‘አርከበ ሱቅ’ በማግኝት እዛም ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። በዚህም ጥሩ እንቅስቃሴ እንደነበር አቶ ቢሆነኝ ገልጸዋል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

የድርጅቱ መሥራች በሕትመት ሥራው ትንሽ እንደቆዩ የሕትመት ሥራውን ትንሽ ቆም በማድረግ የግብርና ሥራ በአፋር ክልል ጅምረው የነበረ ቢሆንም በነበረው አለመረጋጋት 2007 ዓ.ም ሥራውን ትተው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ ምንም ግዜ ሳያባክኑ በፊት ሲሰሩበት ወደ ነበረው የሕትመት ሥራ ከአዲስ ካፒታል ብድር በመበደር የሥራ ቦታ በመከራየት እና ማሽን በመግዛት ሥራውን አንደ አዲስ ጀምረዋል። የተበደሩትንም ብድር በአንድ አመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ብድሩን በመመለስ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ማሽኖችን ሊገዙ ችለዋል። ቢዝነስ ማስታወቂያ ሥራውን ለማስፋፋት ከአዲስ ካፒታል አስር ሚሊዮን ብር ለመበደር በስምምነት ላይ ይገኛል። በአሁን ጊዜም ለአሥራ ሁለት ሰራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር እና ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚጠጋ ካፒታል በመያዝ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ቢዝነስ ማስታወቂያ በቀን አንድ ሺህ ካሬ ሜትር ማስታወቂያ የመሥራት አቅም አለው።

የሚሠራቸው ሥራዎች

  • ዲጂታል ማስታወቂያ
  • ባነሮች
  • ስቲከሮች
  • ሜሾች
  • ቲሸርቶች
  • የወረቀት አጠቃላይ ሥራዎች
  • ዲጂታል ህትመት ሥራዎች
  • ማህተሞች በተመጣጣኝ ዋጋ ያመርታል።

ቢዝነስ ማስታወቂያ ለዚህ የእድገት ደረጃ ለመድረስ የወረዳው የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ድጋፍ የራሱ የሆነ አስተዋጽዖ አለው፤ ለምሳሌ የድጋፍ ደብዳቤ በመፃፍ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር እና በየጊዜው በመከታተል እንዲሁም የብድር አገልግሎት በማመቻቸት ትልቁን ቦታ እንደሚይዝ ይገልጻሉ። የራሳቸውም አስተዋጽዖ ቀላል አልነበረም፤ ለምሳሌ ሙያውን በትግል ነበር ሊገነዘቡ የቻሉት ምክያቱም በጊዜው ሙያውን የሚያውቁ ሰዎችም ለማስተማር ፈቃደኛ አልነበሩም። ይህ ደግሞ አቶ ቢሆነኝን በይበልጥ እንዲተጉ አድርጓቸዋል። ይህም እየሠሩ ላፕቶፕ ኮምፒውተር በመግዛት ዩቲዩብ ቪዲዮዎችን በማየት እራሳቸውን በማሳደግ አዚህ ደረጃ ሊደርሱ ችለዋል።

ቢዝነስ ማስታወቂያ የሚጠቀመው ትልቁ የድርጅቱ ማስፋፊያ የ2merkato የጨረታ አገልግሎት ነው። ሥራችንን ያለንበት ቦታ ድረስ ያመጣልናል ይላሉ አቶ ቢሆነኝ። እያንዳንዱን መረጃ ሳትንቀሳቀስ ጋዜጣ ሄደህ ሳታነብ ሁሉም መረጃ እጅህ ላይ ይመጣልሃል። ሳትንቀሳቀስ ሥራ መሥራት ትችላለህ። ለአቶ ቢሆነኝ ግብዓት ማለት ኢንፎርሜሽን ነው፤ ግብዓት ከሌለህ ሥራ መስራት አትችልም 2merkato ደግሞ ይህንን አቅሎልናል። ከዚህም በላይ ሐረር፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር የመሥራት እድሉም ነበረ። ትልልቅ ድርጅቶች  ሲሆኑ በ2merkato.com በኩል በመጫረት እንጠቀማለን” ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ቢሆነኝ የ 2merkato.com የጨረታ አገልግሎት አራት አመት ተጠቃሚ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ድርጅቱ በተለያዩ መንገዶች አገልግሎቱን ያስተዋውቃል፤ ለምሳሌ በብሮሹሮች፣ ባነሮች፣ ባዛሮች፣ ቢዝነስ ካርዶች እና እራሱ ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ሲሰቀሉ እና በተለያየ ቦታ ሲለጠፉ እዛ ላይም ሥራው ይተዋወቃል።

 

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ የነበረው ጥሩም መጥፎ ተፅዕኖ ነበረው፤ ምክንያቱም ኮቪድ መጋቢት አራት ቀን 2012 ዓ.ም. ነው የገባው። ማኅበረሰቡ ስለኮቪድ የሚኖረውን ንቃተ ኅሊና ለማሳደግ በሚታተሙ ሕትመቶች ምክንያት ለአንድ ወር ያህል ሃያ አራት ሰዓት ያለምንም እረፍት ነበር ሥራ የነበረው። የነበረውን የሥራ ጫና ለመቀነስ ጊዜያዊ ሠራተኞችም ተጨምረው ነበር፤ ነገር ግን ሥራው ሲጠናቀቅ ሌላ ምንም ዓይነት ሥራ ባለመኖሩ አምስት ሠራተኞችን ቀንሶ ሊቀጥል ችሎአል።

ምክር እና እቅድ

ወደ ሕትመት ሥራ ለሚገቡ ሰዎች ሙያውን ማክበር ቀጥሎ ደግሞ ደንበኛን ማክበር ዋናው እና ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። “ደንበኛ የፈለገውን ነገር ቢያደርግ የራሱ ስህተት ቢሆን እራሱ እስከ መጨረሻው ደረስ ማስረዳት ነው እንጂ ደንበኛን መናቅ አያስፈልግም ድርጅቱን የሚያንቀሳቅሰው ደንበኛ ስለሆነ” ይላሉ አቶ ቢሆነኝ።

ቢዝነስ ማስታወቂያ ወደ ፊት በአራት እና በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በተቻለ መጠን ማሽን በመጨመር ብዙ ሥራ ለመሥራት አቅዷል። የሚገዛቸውን (የሚሰበስባቸውን) ማሽኖች በመጠቀም አሁን ካለበት ደረጃ በሠራተኛ፣ በማሽን እና በካፒታል ሶስት አጥፍ ለመጨመር አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …