መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / “በከፍታ ፓኬጅ ተጠቅመናል”- መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

“በከፍታ ፓኬጅ ተጠቅመናል”- መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተመሠረተው በአቶ መንግሥቱ አባተ በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራዎች በዋናነት እንዲሁም የተለያዩ የአበባ ማስቀመጫ እቃዎችን በተለያየ መጠን እና ዲዛይን በተጨማሪም የህጻናት መጫወቻዎችን በጥራት ያመርታል።

ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል

  • የመንገድ እና የአስፋልት ሥራ
  • የድልድይ ሥራ
  • የቀለም ሥራ
  • የጂፕሰም ሥራ
  • የዲኮር ሥራ እንዲሁም
  • የአበባ ማስቀመጫ እቃዎችን በጥራት ያመርታል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ መንግሥቱ ወደ ኮንስትራክሽን ሥራ ከመግባታቸው በፊት በጋራዥ ሥራ ውስጥ ለዐሥራ አምስት አመት ሲሠሩ ቆይተዋል። በዚህም ሥራ ላይ እያሉ ዛሚ ኤ ፍ ኤም 90.7 በጣም ይከታተሉ ነበር፤ እናም በሬድዮ ሰዎች እየደወሉ ከችግራቸው ወጥተው እንዴት እንዳደጉ ይሰሙ ነበር። በዚህ አጋጣሚ እሳቸውም የኮንስትራክሽን ሥራ ይወዱ ስለነበር ለምን አልጀምርም ብለው የጋራዥ ሥራ እየሠሩ ትምህርታቸውን ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ ወደ ኮንስትራክሽን ሥራ ከአናጢ ጀምሮ እስከ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ሊመሠርቱ ችለዋል።

የድርጅቱ መሥራች አንድን ሥራ ለማሳደግ ትልቁ መሣርያ ወሳኝነት እና ቁርጠኝነት ነው ይላሉ፤ ይህንንም በተጨባጭ ሁኔታ ጋራዥ ተቀጥሮ ከመሥራት እስከ የራሳቸውን ጋራዥ እስከመክፈት በተግባር ያዩት ነገር እንደሆነ ጠቅሰዋል። ድርጅቱ ሲመሠረት ካፒታሉ ዐሥራ አምስት ሺህ ነበር፤  አሁን ላይ የሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ካፒታል ማፍራት ችሏል።

ድርጅቱ የፊኒሽኒንግ ሥራዎችን በቤተል እና ብሥራተ ቅ/ ገብርኤል አካባቢ ሠርቷል። እንዲሁም የቤዝመንት ሥራዎችንም እየሠራ ይገኛል።ይህ ድርጅት አንድ ባለ አምስት ኮንዶሚኒየም ሕንጻ ለማጠናቀቅ ከሁለት ወር እስከ ሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ጨርሶ የማስረከብ አቅም አለው። ድርጅቱ ሲጀመር በሦስት አባላት ሲሆን አሁን ላይ ግን ሁለት መሥራች አባላት ብቻ ናቸው ያሉት። ለአራት ቋሚ ሠራተኞች እና  ዐሥራ አንድ ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል ፈጥሮ ይገኛል። መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በፊንሺንግ ሥራ የሦስት አመት የሥራ ልምድ አለው። ይህ ድርጅት ውጤታማ ሊሆን የቻለው በተመረጡ ጊዜዎች ስብሰባ ያካሂዳል ይህም ሠራተኛው ከድርጅቱ ምን እንደሚፈልግ ጠንቅቆ እንዲያውቅ ያደርጋል፤ ድርጅቱም ደግሞ ሠራተኞቹ ምን እንደሚያስፈልጋቸው ከራሳቸው ይሰማል የሚያስፈልጋቸውን ያዘጋጃል ሠራተኞችም የሚጠበቅባቸውን ሥራ ያለ ግፊት እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ ከመጣ ጀመሮ ምንም ሥራ ድርጅቱ አልሠራም፤ በተጨማሪም ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የነበረው አለመረጋጋት ከባድ  ተፀዕኖ ነበረው። ይህም ክ/ከተማ፣ ወረዳ፣ ኮንስትራክሽን ቢሮም ምንም አይነት ሥራ እንዳይኖር ተፅዕኖ አሳድሮ ነበር። አቶ መንግሥቱ ሥራ ሲጠፋ በራሳቸው የፈጠራ ሥራ በመጠቀም የአበባ መትከያ ፋይበር ግላስ እየሠሩ መሸጥ ጀምረዋል። ያ ጥሩ ውጤት ሲያመጣ በመቀጠልም ለትምሕርት ቤቶች፣ ለህጻናት መዝናኛ የሚሆኑ መጫወቻዎችን እየሠሩ ለገበያ በማቅረብ የኮቪድን ጊዜ አልፈዋል።

2merkato.com የቀረበላቸውን  ከፍታ የጨረታና የገበያ ትስስር ማግኛ አገልግሎት ወደውታል። የገበያ ትስስሩን (የማስታወቂያውን ሥራ) ስለወደዱት ነው አንድ አመት በነፃ ተጠቅመው አሁን ደግሞ በከፍታ ፓኬጅ ለኢንተርፕራይዞች በቅናሽ የቀረበውን ፓኬጅ በክፍያ እየተጠቀሙ ያሉት። በዚህም ሁለት ጨረታዎችን አሸንፈዋል። አንዱን ጨረታ ፊርማ ኤንቭሎፕ ላይ አልተፈረመም ተብሎ በዛች ስህተት ለሁለተኛ ሲሰጥ በዚህም ትልቅ ተሞክሮ እንዳገኙ የድርጅቱ መሥራች ገልፅዋል። ሁለተኛውን ደግሞ የአንድ ትምሕርት ቤት እድሳት አሸንፈው በጥራት በመሥራት አስረክበዋል። እንዲሁም ሥራቸውን በጥራት እና በጊዜ ስላጠናቀቁ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በሰው በሰው ነው ምክንያቱም በኮንስትራክሽን ሥራ ትልቅ ድርጅት ካልሆነ ማስታወቂያ መሥራት ትልቅ አቅም ይፈልጋል። ይህንንም አቅልሎ በመሥራት 2merkato.com የመጀመርያ ነው ሲሉ የድርጅቱ መሥራች ተናግረዋል።

ምክር

አዲስ ለሚጀምሩ ምክር

  1. ብዙ ጊዜ አዲስ ጀማሪዎችን ትኩረታቸው ገንዘብ ላይ ነው፤ ይህ ደግሞ ትክክል አደለም ሥራ ላይ ነው መሆን ያለበት።
  2. ሥራ ላይ በአግባቡ ያለመገኘት (የብልጣብልጥንተ ጸባይ)  ተገቢ አይደለም። አባላቱ እኩል መሥራት እኩል መካፈል አለባቸው።
  3. ድርጅቱን ሲመሠርቱ ሳይበዙ ቢሆን (ቢበዛ አምስት አባላት ቢሆኑ) ጥሩ ነው፤ ይህም ቁጥር ሲጨምር የሚፈጠሩ ችግሮችን ያስቀራል፦ ለምሳሌ አለመደማመጥ እና ጥሩ የጋራ ተጠቃሚነትን ያግዳል።

አዲስ ጀማሪዎች ወደ ኮንስትራክሽን ሥራ ሲገቡ አንዱና ዋነኛው ነገር ሥራን በጊዜ  ማስረከብ ነው፤ ይህንን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል። ይህም ማለት ዛሬ ማለቅ የሚችል ሥራ አለማሳደር ተጨማሪ ሠራተኛ ቀጥሮም ቢሆን ሠርቶ ማጠናቀቅ በጣም አስፈላጊ ነው – አሠሪው ደስተኛ ይሆናል ይህ ደግሞ ሌላ ሥራ ይመጣል ማለት ነው። መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅትም ውጤታማ የሆነው ለዚህ ነው፤ ይዋል ይደር የሚባል ሥራ የለውም። ቀጥሎ ደግሞ ሠራተኛውን ማክበር፣ የሠራተኛ መተዳደሪያ ደንብ እና ዲሲፒሊን መኖር ለአንድ  ድርጅት ግዴታ እና መብት ነው። ይህም ሥራ በሚገባ እንዲከናወን ይጠቅማል።

አቶ መንግሥቱ “ሰዎች የራሳቸውን ሥራ ቢሠሩ በቂ ክፍያ ማግኘት ይችላሉ፣ በሚፈልጉት የእድገት ደረጃ ማደግ ይችላሉ እንዲሁም የሞራል ልዕልና ይኖራል በተጨማሪም ለሌሎች የሥራ እድል መፍጠር ያስችላ” ብለው ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

በከፍታ ላይ ያለውን ይድርጅቱን ፕሮፋይል በመመልከት የበለጠ መረጃ ማግኘት ይቻላል። በዚህ ሊንክ ይመልከቱ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …