መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / “በደንብ የሚያውቁትን ስራ መሥራት ለውጤታማነት ቁልፍ ነው”

“በደንብ የሚያውቁትን ስራ መሥራት ለውጤታማነት ቁልፍ ነው”

ሳሙዔል ሰማኸኝ (ሳሚ ማተሚያ ድርጅት)

ሳሚ ሕትመት እና ተያያዥ ሥራዎች የተመሰረተው በ 2011 ዓ.ም ሲሆን፣ የተመሠረተውም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ሳሙኤል ሰማኸኝ ነበር። ድርጅቱ ሲመሰረት ሥራው ብዙም አስቸጋሪ እንዳልነበረ አቶ ሳሙዔል ይናገራል።

የድርጅቱ መስራች የሆነው አቶ ሳሙዔል ወደ ሕትመት ሥራ ከመግባቱ በፊት በአይቲ (IT) ሥራ አራት ዓመት ሲሠራ እንደቆየ ያስረዳል። ወደ ሕትመት ሥራ እንዴት ሊገባ እንደቻለ ሲናገርም መነሻው ጓደኞቹ የሕትመት ሥራ ይሠሩ የነበረ መሆኑ እና እነርሱን ማየቴ ነው ይላል። ከጓደኞቹ ጋር አብሮ የሕትመት ሥራ ሲራ ከቆየ በኋላ፣ ያገኘው የሥራ ልምድ እና ከተማረው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ጋር ተዳምሮ ሥራውን ብዙም ሳይቸገር እንዲገነዘበው አስቻለው። ለሆነም የራሱን የሕትመት ሥራ ሲጀምር ያለ ምንም ችግር እንድሠራ አስችሎኛል ይላል።

አቶ ሳሙኤል ድርጅቱን ሲመሰርት የነበረው መነሻ ካፒታል አንድ ሚሊዮን ብር ነበር። ድርጅቱ ሥራውን ሲጀምር የነበሩት 10 ደንበኞች ሲሆኑ፣ በሁለት ዓመት ውስጥ ከመቶ በላይ ደርሰዋል። አቶ ሳሙኤል ጠንክሮ በመሥራቱ ሥራውን በጀመረ በአንድ ዓመቱ ቁጥር ሁለት ቅርንጫፍ ጀሞ ሊከፍት ችሏል። በአሁኑ ወቅት ከአስር በላይ ሠራተኞች በድርጅቱ ውስጥ ይሠራሉ። ሳሚ ማተሚያ ከምስረታው አንሥቶ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ የሆኑ ሥራዎችን አጠናቋል።

ሳሚ ማተሚያ ብዙ ዓይነት ሥራዎችን ሳይመርጥ በጥራት እንደሚሠራ ይሠራል። ላይት ቦክስ፣  የማይካ ማስታወቂያ፣ የፎም ማስታወቂይ፣ ባነር፣ ስቲከር፣ ሜሽ፣  ሮልአፕ ባነር፣ ብሮሸር፣ ደረሰኝ፣ ማህተም፣ የደረት ባጅ፣ መታወቂያ፣ የኩባያ ህትመት፣ የኮፍያ ህትመት፣ መጽሔት፣ የሰርግ ካርድ፣ የሐዘን ካርድ፣ ቢዝነስ ካርድ፣ ብሮሸር፣ ፍላየር እና ሌሎችም አጠቃላይ የህትመት ሥራዎችን ይሰራል።

 

 

 

 

 

 

በተጨማሪም ክሪስታል ጄት 7000 (Crystaljet 7000) የሚባል ከዘመኑ ጋር ተራማጅ ዘመናዊ የህትመት ማሽን እንደገዛ አቶ ሳሙኤል ይናገራል። “ብዙ ቦታ ያለው ማሽን ሞዴል 4000 (Crystaljet 4000) የሚባለው ነው። የእኛ ዓይነቱ ሞዴል 7000አዲስ አበባ ላይ ከአስር አይበልጥም። ይህኛው ሞዴል ሥራችንን በብዛት እና በጥራት ጊዜ ቆጥበን እንድንሠራ አስችሎናል”  ይላል።

አቶ ሳሙዔል የከፍታ አገልግሎትን በመጠቀም ከተለያዩ ትልልቅ ድርጅቶች ጀምሮ እስከ ትንንሽ ድርጅቶች ድረስ የሥራ ትስስር እንደ ተፈጠረለት ጠቅሶአል። ለዚህ ደግሞ በከፍታ አማካኝነት 2merkato.com ላይ የሚገኙ በመላ ኢትዮጵያ የሚወጡ ጨረታዎች ስለሚደርሱት ብዙ ሥራ የማግኝት ዕድል ተፈጥሮልኛል ይላል አቶ ሳሙዔል። በከፍታ አገልግሎት በኩል ባገኘው ዕድል ከከፍተኛ ተቋማት ጋር አብሮ ከመሥራቱም ባሻገር ከአዲስ አበባ እስከ ድሬዳዋ ድረስ የመሥራት አጋጣሚ አግኝቷል። “ያለማጋነን ከፍታ / 2mrekato.com ለሥራችን ዋና የሥራ ምንጭ ነው” ይላል አቶ ሳሙዔል።

“አዳዲስ ጨረታዎች በየቀኑ ይደርሱናል፣ ለሥራችን ብቻ የምንፈልገውን ጨረታ መርጦ ነው የሚያመጣው ይህ ደሞ ሌላ የማይመለከተንን ጨረታ በማየት ጊዜ እንዳናጠፋ በጣም አግዞናል። ለብዙ ጓደኞቼን እንዲጠቀሙ ጋብዜአቸዋለሁ።”

ለዚህ ደረጃ ምን እንዳደረሰው አቶ ሳሙኤል ሲናገር፣ “ከአስር በላይ ሠራተኞች አሉ፤ እነሱ ደስተኛ ሆነው ሲሠሩ ሥራው ውጤታማ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ በተቻለኝ መጠን እነሱ ደስተኛ ሆነው ሥራውን እንዲሠሩ እሞክራለሁ። ደስተኛ ሠራተኛ ሲኖር ሥራውም ውጤታማ ይሆናል” ይላል።

የወደፊት እቅዳቸውን ሲናገሩ በስድስት ወር ውስጥ 3ኛ ቅርንጫፍ መሐል ከተማ መክፈት አስባለሁ ብለዋል። ትልቁ ዓላማቸው ጥሬ ዕቃዎችን በቀጥታ በማስመጣት አገር ውስጥ የማይሠሩ ሥራዎችን መሥራት እንደሆነ ያስረዳሉ። ለምሳሌ ቻይና እና ዱባይ የሚሠሩ ሥራዎችን በተመጣጣኝ ጥራት በአገር ቤት ለመሥራት ያስባሉ፤ ይህንን ለማሳካትም አምስት ዓመት ያህል ሊፈጅ እንደሚችል ይገምታሉ።

ኮቪድ በድርጅቻቸው ላይ የነበረው ተፅእኖ  አንድ ወር ሠራተኛ ቀርቶ ሥራ ለማቋረጥ ተገደው ነበር። ቢዝነሱ ላይ መጠነኛ ተጽዕኖ ቢኖረውም አከራያቸው የ50% የኪራይ ቅናሽ አድርገውላቸው የነበረ መሆኑ ያንን ጊዜ ያለ ብዙ ጫና እንዲያልፉ እንደረዳቸው አቶ ሳሙዔል ገልፅዋል።

አቶ ሳሙዔል በሕትመት ዘርፍም ሆነ በሌላ ሥራ አዲስ ለተሰማራ ሰው ምን እንደሚመክሩ ሲጠየቁ፣ በቅድሚያ ለሥራው ፍላጎት መኖር እና ሥራውን በደንብ ማወቅ ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። በመቀጠል በተለይ የህትመት ሥራ በባህሪው ብዙ ካፒታል የሚጠይቅም ስላልሆነ ፍላጎቱ ካለ ሥራውን በደንብ ለማወቅ የ6 ወር ጊዜ ይበቃል ይላሉ።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …