መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / የእንጨት ሥራ -ሶሊና ሶፋ የቤት እና የቢሮ እቃዎች አምራች

የእንጨት ሥራ -ሶሊና ሶፋ የቤት እና የቢሮ እቃዎች አምራች

ሶሊና ሶፋ የቤት እና የቢሮ እቃዎች አምራች የተመሰረተው በ2001 ዓ.ም በአቶ አብይ ወልደሐና እና በአምስት መሥራች አባላት ነው። በ2001 ዓ.ም ቢመሰረትም ምርት በጥሩ ሁኔታ ማምረት የጀመረው ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ነው። በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ እና አንጋፋ ሶፋ አምራች ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ በሦስት ቅርንጫፎች በጎተራ፣ ጉርድ ሾላ እና መካኒሳ  እንዲሁም አንድ ቅርንጫፍ በደሴ የማሳያ ሱቆች አሉት።

shebelle-solina

 

ሶሊና ሶፋ ከሚያመርታቸው ምርቶች

adey-abeba

  • ሶፋዎች
  • ቁም ሳጥንኖች
  • አልጋዎች
  • የቢሮ እና የቤት እቃዎች
  • አሁን ደሞ በቅርብ ሶሊና ሆምስ ፈርኒቸር በሚል አጠቃላይ የቤት እቃ፦ አልጋ፣ አንሶላ፣ ትራስ፣ ቴሌቪዥን፣ የኪችን ካቢኔት በጥራት ያቀርባል።

 

 

soli-solina

 

ምሥረታ፣ ዕድገት እና ማስተዋወቅ

ድርጅቱ አሁን በደረሰበት የማምረት አቅም በቀን ዐሥራ አንድ ሶፋዎች ማምረት ይችላል። ሁሉም በሶሊና ሶፋ የሚመረቱ ሶፋዎች በሥራ አስኪያጁ በአቶ ጥላሁን ወንድም በአቶ አብይ ወልደ ሀና የዲዛየን ንድፍ ችሎታ የኢትዮጵያውያንን የአኗኗር ዘይቤ ባገናዘቡ መልኩ ነው የሚነደፉት። ሶሊና ሶፋ እንደ ደንበኞች ፍላጎትና አቅም በተመጣጣኝ የሽያጭ ዋጋ ከስምንት ሺህ ብር ጀምሮ እስከ መቶ ሺህ ብር  ሶፋዎችን በጥራት ለተጠቃሚ ያቀርባሉ። ሶሊና ሶፋ ከመመስረቱ በፊት የአቶ ጥላሁን ወንድም አቶ አብይ በእንጨት ሥራ ለዐሥር ዓመት ተቀጥረው ሲሠሩ እንደ ነበር ገልጸዋል። በመቀጠለም  ከዐሥር ዓመት የሥራ ልምድ እና በራስ የመተማመን ስሜት ተደምሮ ከአምስት መስራች አባላት ጋር ሶሊና ሶፋ ሊመሰረት ችሏል። ቀስ በቀስ እያደገ እየሰፋ በአምስት መስራች አባላት የተጀመረው ድርጅት አሁን ላይ 69 ለሚደርሱ ሠራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ምርት የሚመረትበት የሥራ ቦታ

ሶሊና ሶፋ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ አሁን ላለበት ደረጃ እስኪደርስ ግን ችግሮች አልነበሩም ማለት አይደለም፤ ገኖ የወጣ ትልቅ ችግር ባይኖርም ሊያጋጠሙ የሚችሉ ችግሮችን በተረጋጋ አእምሮ በማጤንና በማጥናት ችግሮቹ ሊፈቱ ችለዋል። በአሁን ጊዜ ሶሊና ሶፋ ትልቅ ችግር የሆነበት የመሥሪያ ቦታ ማነስ ነው፡፡ ይህንንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ወደ መፍትኄ ለመድረስ እየሠራ ይገኛል።  ሶሊና ሶፋ አሁን የደረሰበት ደረጃ ሊደርስ የቻለው በድፍረት ጠንክሮ በመሥራቱ እና ሁሉም ሠራተኞች ያላቸው የሥራ ፍቅር ነው።

ሶሊና ሶፋ ምርትን ማስተዋወቅ ለአንድ ቢዝነስ ወሳኝ የማደጊያ መንገድ እንደሆነ ያውቃል ስለሆነም በተለያዩ መንገዶች ምርቱን ያስተዋቅቃል ከሚያስተዋውቅባቸውም መንገዶች ውስጥ

  • በቴሌቪዝን (ቃና፣ ፋና)
  • በሬድዮ (በሰይፉ ፕሮግራም ላይ)
  • የተለያዩ ቲሸርቶች፣ የእጅ ፌስታሎች፣ ባነሮች፣ ብሮሸሮች እና የመሳሰሉትን በመጠቀም ሥራውን ያስተዋውቃል።

አቶ ጥላሁን ሥራ በሚሰራበት ጊዜ ሊኖር የሚገባው ግንኙነት የአሠሪና ሠራተኛ ሳይሆን የአባት እና የልጅ ወይም የታላቅ እና የታናሽ ቤተሰባዊ የሥራ ግንኙነት መኖር የላቀ ጠቀሜታ አሰገኝቶለታል ይላሉ። እንዲሁም ለታታሪና ውጤታማ ሠራተኖች በተለያየ መልኩ የማበረታቻ ሽልማቶችን በማዘጋጀት መሸለም ለውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል።

ድርጅቱ ወደ ፊት የቦታ ችግር መፍትኄ እንድሚያገኝ ጽኑ እምነት ያለው ሲሆን የሥራ እድል በማስፋፋት ረገድ በመቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ሐረር እንዲሁም ኤክስፖርት በማድረግ ለአገራችን የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት  ረገድ አስመራ ቅርንጫፎችን  የመክፈት እቅድ አለው።

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮሮና ወረርሽኝ የነበረው ተፅዕኖ ከባድ ነበር ምርት፤ በግማሽ ቀንሶ እንደነበር ለዚህም ሶሊና ሶፋ እንደመፍትሔ የወሰደው ሠራተኞችን በግማሽ  በፈረቃ እንዲገቡ በማድረግ የሚያስፈልግውን ጥንቃቄ በመጠቀም በቀን ዓሥራ አንድ ሶፋ ይመረት የነበረውን ወደ አምስት በመቀነስ ያንን ፈታኝ ጊዜ ሊያልፉት ችለዋል።

ማስፋፋት እና ምክር

“ሶሊና ሶፋ ለሚያመርተው ምርት ከምንም በላይ ለጥራት ቅድሚያ ይሰጣል አንድ ምርት ለማምረት የሚፈለገው ጥሬ እቃ ካልቀረበ ወይም ከጎደለ ለሥራው የሚፈልገው ጥሬ እቃ እስከሚመጣ ደረስ ይዘገያል እንጂ ሥራው ቶሎ እንዲሠራ ተብሎ ጥራቱን ቀንሰን አንሠራም።  ይህም ከፍተኛ የደንበኛ እርካታ በማስገኘት ለእድገቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል። ሰዎች ሶሊና ሶፋን ከሚዲያው ይልቅ በሰው በሰው ያውቁታል። ይህም ሥራችን በጣም ጥራት ስላለው እንድ ደንበኛ ጥሩ ነገር ከሰጠነው ነገ ሰው ይዞ መምጣቱ ስለማይቀር ነው” ይላሉ አቶ ጥላሁን።

“ሥራን አለመናቅ አና ምንም አይነት ሥራ ቢሆን የወደፊቱን ትልቅነት እያሰቡ መሥራት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ፈርኒቸር ቤት ለመክፈት የሚያስብ ሰው መጀመሪያ ከትንሽ ሥራ እንደ እቃ ማንሳት ማቀበል፣ ከዛ መዶሻ መያዝ ከዚያም ትንሽ ገንዘብ አጠራቅሞ እንድ ማሽን መግዛት ከዛ ሁለት እያለ ማደግ ነው። ቅድም እንዳልኩት የሥራው ብቃት ሲኖረው ሥራውን መጀመር ይችላል። ዋናው ነገር ግን ድፍረት እና ታጋሽ መሆን በጣም ያስፈልጋል” ሲሉ አቶ ጥላሁን ይመክራሉ።

አሁን ባለው የገበያ ሁኔታ በ’ከፍታ’ በኩል የሚሰጠውን የ2merkato የመረጃ አገልግሎት በቴሌግራም እንደሚጠቀሙ  ገልፀዋል፤ ወደፊት የብረታ በረት አሉሚኒየም ሥራ የመጀመር ሀሳቡ ስላለ የ2merkato ጨረታ አገልግሎት ለመጠቀም አቅደዋል ።

አዲስ ሥራ ለሚጀምሩ ሰዎች ያስተላለፉት መልክት፦ በመጀመሪያ የሚሰሩትን ሥራ ማወቅ፣ ሥራን ማክበር፣  ስራን በሚገባ ማጤንና ማውቅ ሶስተኛ ወድ ስራ ለመግባት ድፍረት መኖር ያስፈልጋል። እነዚህ ዋና ዋና ነገሮች ናቸው ሲሉ አቶ ጥላሁን ይመክራሉ።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …