መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ዜድቲኢ አልሙኒየም እና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሥራ

ዜድቲኢ አልሙኒየም እና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዘላለም እና በጓደኛቸው መሥራች አባልነተ በ2011 ዓ.ም. ነው። የሚሠራቸው ሥራዎች አጠቃላይ የአሉሚኒየም ሥራዎች፣ የማማከር፣ አጠቃላይ የኢንቲሪየር ዲዛይን (የቤት ውስጥ ስነ ውበት)፣ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ይሠራል። የድርጅቱ መሥራቾች በዘርፎቹ ከሰባት ዓመት በላይ የሥራ ልምድ አዳብረዋል።

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች

 • የአሉሚኒየም በር እና መስኮት ሥራ እንዲሁም የማማከር አገልግሎት
 • የአሉሚኒየም ፓርቲሽን ሥራ
 • የስካይ ላይት ሥራ
 • የአሉሚኒየም ሃንድ ድሪል ሥራዎች
 • የኬሪንግ ሥራ (የቤት ማስዋብ ሥራዎችን በአሉሚኒየም እና በእንጨት አጣምሮ የመሥራት ሥራ)
 • የውስጣዊ ቤተ ውበት ሥራዎች ደግሞ
 • የቤት ማስዋብ ሥራ
 • የዲኮር ሥራ
 • የቤት ውስጥ ፈርኒቸር ማስዋብ ሥራ እንዲሁም
 • የጋርደን ማስዋብ (ማሳመር) ሥራዎችን በጥራት ይሠራል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

የድርጅቱ መሥራቾች ይህን ድርጅት ከመመሥረታቸው በፊት በዘርፉ ተቀጥረው ሦስት ዓመት ሠርተዋል። አቶ ዘላለም ወደ አሉሚኒየም ሥራ ከመግባታቸው በፊት በተማሩበት የኮንስትራክሽን ሙያ ለሦስት ወር ከሠሩ በኋላ የሚያዋጣው አሉሚኒየም ሥራ እንደሆነ በመረዳት ወደ አሉሚኒየም ሥራ ተቀላቅለዋል።

ድርጅቱ ሲመሠረተ የነበረው መነሻ ካፒታል ሁለት መቶ ሺህ ብር ሲሆን አሁን የድርጅቱ የካፒታል መጠን ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ደርሷል። በተጨማሪም ለዐሥራ አንድ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በሰው በሰው (word of mouth) ነው። በተጨማሪም የድርጅቱ ሠራተኞች ሥራዎችን በሚሠሩበት ጊዜ ወይም በሌላ ቦታ ምንም አይነት የሥራ እድል አያልፉም ሁሉንም አጋጣሚ በመጠቀም ሥራዎች ያገኛሉ። ይህ ማለት ከኮንትራክተሮች፣ ሥራውን የሚያሠራው ሰው እንዲሁም ሥራው የሚሠራበት አካባቢ የሚገኙ ሠራተኞችን በማናገር በመተዋወቅ ብዙ ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ። እንዲሁም የኮንትራት ሥራዎች በመውሰድ እና ሥራውን ለመሥራት አቅሙ ላላቸው ሰዎች ሥራውን በመስጠት እንዲሠራ ያደርጋሉ። በመጨረሻ ደግሞ ቴክኖሎጂን መጠቀም ለምሳሌ ሥራ ለማግኘት አዳዲስ እና ቀላል አሠራሮችን ለማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። በከፍታ አገልግሎት ጨረታዎችን እና የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን ዋጋ እየተከታተሉ እና ሥራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ድርጅቱ ያጠናቀቃቸው ሥራዎች እንደሚከተለው ናቸው

 • ቦሌ አዲላ ሪል  እስቴት ባለ ዐሥር ፎቅ ሕንጻ
 • ሜሪዲያን አካባቢ አሁን እየሠራ የሚገኘው ሪል እስቴት ሕንጻ
 • አንዲ ኮንስትራክሽን ወሎ ሰፈር ሁለት ሳይቶች በጥራት ሠርቶ አጠቆ አስረክቧል
 • ካክሰስ፣ ፕሮ ሎግ፣ ላይፍ ኢን ዘወርድ፣ ኤቢቢ፣ አፍሪካ ዴቭሎፕመንት ባንክ ጋር ሥራዎች ሥራዎች ሠርቷል።

ድርጅቱ አሁን የሚሠራቸው ሥራዎች ዋጋ በካሬ ከስምንት ሺህ ብር እስከ ዐሥር ሺህ ብር ነው። ይህም አንደ ሥራው አይነት እና ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጀው ጥሬ እቃ ታሳቢ በማድረግ።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ በድርጅቱ ላይ የነበረው ተፅዕኖ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ምንም ሥራ አልነበረም፤ የማርኬቲንግ ሥራ ደግሞ ወጥቶ አንደ ልብ ለመሥራት አስቸጋሪ ስለነበር የነበረውን አማራጭ ሰው የማይበዛባቸውን ሥራዎች በማጠናቀቅ ነበር ያሳለፉት።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ ወደ ፊት በተሻለ ሁኔታ የመሥራት አቅሙን በማስፋት ትልቅ ድርጅት ለመሆን የመሥራት እቅድ አለው።

አቶ ዘላለም አንድ ቢዝነስ ያለው ሰው ምን ዓይነት የቢዝነስ ስነ ምግባር ሊኖረው እንድሚገባ ሲናገሩ፦ “ሰዓት ማክበር አለበት እና ደግሞ ለሥራው እራሱ ምሳሌ ሆኖ መታየት አለበት። ሠራተኞች የሚያዩትን ስለሆነ የሚሠሩት ሥራውን በሚገባ አክብሮ መሥራት የሚችል ሰው መሆን አለበት” ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

እንደ ተጨማሪ ደግሞ የሚከተለውን ሀሳብ አክለዋል “አንድ ድርጅት የንግድ ስም (trade name) ሲኖረው ሥራ ለመሥራት በጣም የተሻለ ይሆናል፤ ምክንያቱም አሁን በጥቃቅን እና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ዝቅ አድርጎ የማየት ነገር አለ። ስለዚህ ድርጅቶች የተለመደውን የጥቃቅን እና አንስተኛ ስያሜ በየንግድ ስም (trade name) በመቀየር የተሻለ ሥራ መሥራት ይችላል። ሌሎችም እንዲህ ቢያደርጉ ጥሩ ነው” ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …