መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ የከተማ ግብርና መስፋፋት የሚቻሉባቸው መንገዶች ላይ ከባለሙያዎች ጋር መከሩ

የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ የከተማ ግብርና መስፋፋት የሚቻሉባቸው መንገዶች ላይ ከባለሙያዎች ጋር መከሩ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው በትናንትናው ዕለት እንዳሰፈሩት፣ ከከተማ ግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም በዘርፉ ተሰማርተው ውጤታማ ሥራዎችን ከሠሩ ግለሰቦች ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ከንቲባው፣ “በየቅጥር ጊቢያችንና በጠባብ መኖሪያዎች ላይ ጭምር እንዴት የከተማ ግብርና መተግበር እንደሚቻል ተወያይተናል” ሲሉ አሳውቀዋል።

“በከተማችን የሚገኙ ወንዞችን የፍሰት መስመር ተከትለን ነዋሪዎቻችንን ወደ ከተማ ግብርና ስርአት ማስገባት እንደምችል ተግባብተናል። በቅርብ ጊዜ ውስጥም የሚታይ ውጤት እንደሚመዘገብ እምነቴ የፀና ነው። በከተማ ግብርና ከተማችንን እንመግባለን!” – ሲሉም ኢንጅነር ታከለ ኡማ ደምድመዋል።

ምንጭ፡- https://twitter.com/TakeleUma

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …