ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አብዲ ድሪባ 2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ አጠቃላይ የቆዳ ምርቶች እንደ ጫማ፣ ጃኬት እና ቦርሳዎችን ሲሆን፣ እንዲሁም ለቆዳ ሥራ የሚውል ጥሬ እቃ ያቀርባል።
ድርጅቱ የሚያቀርባቸው ምርቶች አሁን ላይ ያለው ዋጋ በጥቂቱ
- የሴት ጃኬቶች ከ 2500 ብር እስከ 2700 ብር ድረስ ለግል ተጠቃሚዎች ለጅምላ ደግሞ ከ2300 ብር ያቀርባል።
- የወንድ ጃኬቶች ከ 2800 ብር ጀምሮ እስከ 3500 ድረስ ለጅምላ ተጠቃሚዎች ደግሞ ከ2700 ብር ጀምሮ ያቀርባል።
- የወንድ የኪስ ቦርሳዎች 350 ብር ያቀርባል።
- ሳይድ ባግ 2200 ብር ያቀርባል።
- የሴቶች ቦርሳ ከ1400 ብር እስከ 2000 ብር ድረስያቀርባል።
ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት
አቶ አብዲ ወደ ቆዳ ሥራ የገቡት የተማሩት በዚሁ ዘርፍ ስለነበር ነው። እንዲሁም ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲወጡ በሌላ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ለስድስት ወር መሥራት ችለዋል። በዚህም ምክንያት ስለቆዳ ሥራ የነበራቸው እውቀት በጣም ሊሰፋ እንደ ቻለ እና እሳቸው አንድ ማሽን በመግዛት ሥራውን እንደጀመሩ ገልጸዋል።
የድርጅቱ መሥራች ለትንሽ ጊዜ እንደ ሠሩ የቤት ኪራይ ዋጋ ሲወደድ፣ የእቃዎችም ዋጋ ሲጨምር እና ነገሮች መክበድ ሲጀምሩ ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን አብረን ብንደራጅ እና ከመንግሥት ሼድ ማግኘት እንችላለን፤ ሌሎች ድጋፎችም ስለሚኖሩ እኛ ደግሞ ሥራችን በደንብ መሥራች እንችላለን ብለው ተደራጁ። በመቀጠልም ሥራቸውን እየሠሩ ቀስ በቀስ የምርት ጥራት እና ብዛት መጨመር ችላለዋል።
ድርጅቱ አሁን ላይ በደንብ አተኩሮ እየሠራ የሚገኘው በጃኬት እና ቦርሳ ላይ ሲሆን የጫማ ሥራ ለጊዜ በጥሬ እቃ አቅርቦት መጓተት ምክንያት ቆሟል። ድርጅቱ አሁን ባሉት ዐሥር ማሽኖች እና ሦስት ቋሚ ሠራተኞች የሚመጣን ማንኛውንም ሥራ ተቀብሎ የመሥራት አቅም አለው። ካስፈለገ ደግሞ ከዐሥር በላይ የሚሆኑ ዜጎችን በጊዜያዊነት በመቅጠር መሥራት ይችላል።
ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በተለያዩ መንገዶች በመጠቀም ሲሆን እነዚህም የቴሌግራም ቻናል በመጠቀም ምርቱን በማስተዋወቅ፣ በኤግዚቢሽን እና ባዛሮች ላይ በመሳተፍ፣ እንዲሁም 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ባዘጋጀው የከፍታ ፓኬጅን በመጠቀም ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ እና በሰው በሰው የሚመጡ ሥራዎችን በመሥራት እና ለሱቆች በማስረክብ ነው።
ድርጅቱ የነገው ባዛር ላይ ሁለት ጊዜ የመሳተፍ ዕድል የነበረው ሲሆን ተሞክሮአቸውን እንዲህ ሲሉ አካፍለዋል። “የነገው ባዛር በጣም ጥሩ ነው ምንም ጥያቄ የለውም፤ ከጎብኚዎች ውስጥ የውጭ ዜጎች አሉ። በመጀመሪያ ጊዜ ምን ዓይነት ምርት እንደሚፈልጉ ማወቂያ ነበር፤ ሁለተኛ ጊዜ ላይ የሚፈልጉትን ምርቶች በጥራት በማምረት ለማቅረብ ችለናል። ሌላው ጥሩ ነገር ስለ ምርቱ አስተያየት በቀጥታ ይሠጣሉ፤ ይህ ደግሞ ምርታችንን ካለው የጥራት ደረጃ ይበልጥ እንድናሳድግ እና በነበረው ምላሽ መሠረት ጥሩ እንደሆነ ተረድተን ኤክስፖርት የማድረግ ሃሳቡ እንዲመጣልን አድርጎናል” ሲሉ የድርጅቱ መሥራች ተናግረዋል።
ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ ለሦስት ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ እንዲሁም ብድር በማግኘት ማሽኖችን ጨምሯል። በተጨማሪ ማቴሪያሎችን ገዝቶ በማስቀመጥ ምንም ዓይነት ሥራ ሲመጣ የማቴሪያል እጥረት ሳይኖር ሥራው በማቴሪያል እጥረት ሳይጓተት በተባለው ጊዜ መጠናቀቅ እንዲችል አድርጓል። በዚህም ሁለት ጨረታዎችን በማሽነፍ በጥራት ሠርቶ ማስረከብ ችሏል።
የኮቪድ ተፅዕኖ
በኮሮና ጊዜ ሥራ ቀንሶ ነበር። ሠራተኞችም ወደ ትወልድ ቦታቸው ሄደው ነበር። የነበረው ሁኔታ ትንሽ ቀዝቅዝ ሲል ማስክ ማምረት ጀምረው ነበር፤ ብዙም ሳይሠሩበት የሰርጂካል ማስክ ገበያውን ሞላው። አንዳንድ ሥራዎች በሰው በሰው ሲመጡ የመሥራት ዕድሉ ነበር፤ እነዚህን ነገሮች በማድረግ ነው ያሳለፈው።
ምክር እና እቅድ
ድርጅቱ ወደ ፊት አሁን ያለውን ለባለሱቆች ምርት ሲያስረክብ በክፍያ መቆየት ምክንያት ያለውን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት የራሱን የማሳያ ሱቅ ለመክፈት ዕቀድ ይዟል። እንዲሁም ከአዲስ ካፒታል ጋር የጀመረውን የማስፋፍያ ሥራ አጠናቆ ምርቱን በብዛት ለማምረት እና የውጭ ገበያ ላይ በመሳተፍ ምርቶቹን በማስተዋወቅ ኤክስፖርት እያደረገ ራሱንም ሀገሩንም ለመጥቀም እቅድ አለው።
“አዲስ ወደ ሥራ የሚገቡ ሰዎች ለሚሠሩት ሥራ ፍላጎት ሊኖራቸው ይገባል። ሥራውን ሲሠሩ ሄዶ ሄዶ ምንም ነገር ላይገኝ ይችላል፤ የታሰበው ቦታ ላይ በግማሽም በሩብም ላይደርስ ይችላል። ፍላጎት ካለ ግን ተስፋ ሳይቆርጡ በመሥራት በዚህ በዚህ ምክንያት ነው ያልተሳካልኝ የሚለውን በማወቅ እና በማስተካከል መቀጠል ይችላል። በሥራ ላይ እንዳንድ ነገሮችን ያልፋሉ ብሎ ማሳለፍ እና ተስፋ ሳይቆርጡ መሥራት አስፈላጊ ነው” ብለው ምክራቸውን መክረዋል።
እንደ ተጨማሪ ኤቨንቶች ሲኖሩ በከፍታ በኩል መረጃው ማየት እና ማግኘት የሚቻልበትን መንገድ በቴሌግራም ቻናል ላይ ልክ እንደ የነገው ባዛር መረጃውን ብታደርሱን መልካም ነው ብለዋል።
የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ።