መነሻ / የቢዝነስ ዜና / በኮቪድ-19 ለተጎዱ ኢንተርፕራይዞች የሚውል 207 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

በኮቪድ-19 ለተጎዱ ኢንተርፕራይዞች የሚውል 207 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

ዛሬ በገንዘብ ሚኒሰቴር በተደረገ የፊርማ ስነ-ሰርዓት ላይ በኢትዮጰያ መንግስት እና በዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ። ከዚህ ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው።

የ200 ሚሊዮን ዶላሩ ድጋፍ ዒላማ ያደረገው በተለይ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ ተጎድተው፣ ነገር ግን ቢደገፉ በሥራቸው አዋጭ ሆነው ለመቀጠልና በንግድ ውስጥ ሊቆዩ ለሚችሉ ኢንተርፕራይዞች እንደሆነ ተገልጿል።

የ500 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በሀገሪቱ ውስጥ ለሚከናወኑ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ተደራሽነት ከማሳደግ ባሻገር የግሉ ዘርፍ ካፒታል ተሳትፎን እና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን ለማምጣት የሚያስችል አከባቢን ለመፍጠር የሚያስችል ነው። ከዚህ ስምምነት ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ የሚውለው የግሉ ዘርፍ በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ እና አቅርቦት ተሳትፎ እንዲኖረው ለማስቻል ነው።

የመጨረሻው የ207 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ፣ ብሎም የበሽታው መከላከያ ክትባቶችን ውጤታማ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲዳረስ ለማድረግ የሚውል የፋይናንስ ድጋፍ ነው።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ኦስማን ዲዮን ተፈራርመውታል።

የስምምነቱ የተፈረመው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ከበደ፣ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ  ዶ/ር ፍሬሕይወት ወልደሃና፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው፣ የፌዴራል አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፊያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በተገኙበት ነው።


ምንጭ ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር ድረ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …