መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / ፋይናንስ | ብድር / አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ.
gears

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ.

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር ዓላማ አድርጎ የተነሳው በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ ዕውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክንያት መሥራት ላልቻሉ ኢንተርፕራይዞች የተወሰነ የጊዜ ገደብና ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጦ የካፒታል ዕቃን በማቅረብ (በሟሟላት) የፋይናንስ እጥረታቸውን መቅረፍ ነው። 

በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የሊዝ የፋይናንስ ስርዓት የካፒታል ዕቃዎች ኪራይ አገልግሎት ሂደት ተጠቃሚ በመሆን የካፒታል እቃ ባለቤት መሆን ይቻላል። መሟላት ያለባቸውን መመዘኛዎች (መስፈርቶች) ይዞ በመቅረብ እና በመዝገብ አገልግሎቱን ተጠቅሞ ሥራን ለማሳደግ እና የተሻለ ገቢን ለማግኘት ያስችላል።

ኩባንያው በአሁን ሰዓት ለሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በየክፍለ ከተሞች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን በመክፈት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ. ማን ነው?

ምሥረታ

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሌሎች የከተማው የልማት ተቋማት ጋር በመሆን በ2006 ዓ.ም. የተቋቋመ የካፒታል ዕቃ አቅራቢ ተቋም ነው። በዋናነት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በጥናት መሠረት የማምረቻ መሣሪያዎችን ገዝቶ በማቅረብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት ዓላማው ነው። ኩባንያው ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ለቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች፣ ለሴት ሥራ ፈጣሪዎች፣ ለተመረጡ ስኬታማ የንግድ ተቋማት ዕሴት የሚጨምርና ተደራሽ የሆነ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ መደገፍ ላይ ትኩረት አድርጎ በመንቀሳቀስ ውጤታማ የካፒታል ዕቃ አቅርቦት ስርዓት የመገንባትን ተልእኮ በመወጣት ላይ ይገኛል።

የኩባንያው ራዕይ

በ2025 (እ.ኤ.አ) ቀጣይነቱና አስተማማኝነቱን ያረጋገጠ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ሞዴል የሆነ የካፒታል እቃ ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ መሆን 

የኩባንያው ተልዕኮ

እውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ወይም ለመደራጀት ፍላጎት ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክንያት ሥራቸውን ማስፋት ላልቻሉ ኢንተርፕራይዞች ቀጣይ እና አስተማማኝነት ያለው የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት ነው።

  • የዱቤ ግዥ ኪራይ
  • የፋይናንሽያል ኪራይ
  • የምክር አገልግሎት መስጠት
የካፒታል ዕቃ ኪራይ ማለት በፋይናንስ ኪራይ ወይም በዱቤ ግዥ ኪራይ ዘዴዎች መለዋወጫን ጨምሮ ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የካፒታል እቃዎች ፋይናንስ አቅርቦት ስርዓት ነው።
  • የሥራ ሁኔታውን (የቢዝነሱን አዋጭነት) እና የመክፈል አቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት የመሣሪያ ኪራይ ክፍያ ማጠናቀቂያ የቆይታ ጊዜ ከ 3-8 ዓመታት ነው።
  • ኩባንያው ለአንድ ኢንተርፕራይዝ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት የኩባንያው ካፒታል 2.5 ሚሊዮን ብር ድረስ የሚያወጡ የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ ያቀርባል።
  • ከእቃ ግዢ በኋላ አዲስ ለተቋቋመ የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ እስከ 6 ወራት፣ ለነባር ኢንተርፕራይዝ ደግሞ እስከ 4 ወር የሚደርስ የእፎይታ ጊዜ ይሰጣል።
  • ሕጋዊ የንግድ ሥራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ
  • ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ዕቃ ኪራይ ለሚጠይቁ ደንበኞች የተጠና ቢዝነስ እቅድ እና ከግማሽ ሚሊዮን ብር በታች ለሚጠይቁ በአግባቡ ተሞልቶ በሁሉም ገጾች የኢንተርፕራይዙ ማህተም የሚያርፍበት ከኩባንያው የሚቀርብ ቢዝነስ ፕላን እና የማሽን መጠየቂያ ቅጽ
  • እንዲገዙላቸው የሚፈልጓቸው ማሽኖች ዝርዝር
  • የመሣሪያውን ዋጋ ዐሥራ አምስት በመቶ ወይም በላይ ቅድሚያ ለመክፈል የተዘጋጀ
  • የተጠየቁት ማሽኖች ለመትከል በቂና መሠረተ ልማቱ የተሟላ ቦታ
  • የመሥሪያ ቦታው የመንግሥት ሼድ ከሆነ የኪራይ ውል፣ የግል ቦታ ከሆነ የካርታ ኮፒ፣ የግለሰብ የኪራይ ቦታ ከሆነ በውልና ማስረጃ የጸደቀ የኪራይ ውል ኮፒ፣ የሥራ አስኪያጅ 2 ጉርድ ፎቶ
  • የግል ኢንተርፕራይዝ ወይም ማኅበር (ኅ.የተ.የግ.ማ) ከሆነ የአባላት የጋብቻ ስርቲፊኬት ወይም ያላገባ ማስረጃ ኮፒ
  • ማኅበር (ኅ.የተ.የግ.ማ) ከሆነ የመመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ 2 ኮፒ
  • የኢንተርፕራይዙ አባላት በሙያው የሠለጠኑበት እና ብቃታቸው የተመዘነበት የምስክር ወረቀት (ሲኦሲ) ወይም ከታወቀ ማምረቻ ድርጅት የሙያ ልምድ ማስረጃ ኮፒ
  • የብድር ታሪክ ደብዳቤ ከወረዳቸው የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም እንዲሁም ከሌላ ፋይናንስ ተቋም ካለም ማቅረብ
  • በመንግሥት ሼድ ውስጥ ከሆኑ ከክፍለ ከተማ የመሥሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ወይም ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ውልና የማሽን ይሰጣቸው ድጋፍ
  • በአግባቡ ተሞልቶ በሁሉም ገጾች የኢንተርፕራይዙ ማህተም የሚያርፍበት ከኩባንያው የሚቀርብ ቢዝነስ ፕላን እና የማሽን መጠየቂያ ቅጽ
  • ከውጭ ሃገር ሚገቡ ምርቶችን ለሚተኩ እና ወደ ውጭ አገር ለሚላኩ ምርቶችን ለሚያመርቱ ልዩ ትኩረት ይሰጣል።
  • በክላስተር ማዕከላት በመሰባሰብና በመሥራት ላይ ላሉ ኢንተርፕራይዞች፣ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሴቶች፣ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ክፍሎች፣ ለቴክኒክና ሙያ እና ለዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ወጣቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል።
  • በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳ፣ ብረታብረት፣ እንጨት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ምርት፣ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች፣ ኮንስትራክሽን ግብዓት ምርቶች፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በመልሶ መጠቀምና ሌሎች የማምረቻ የሥራ መስኮች የተጠቃሚዎችን ጥያቄ መሠረት በማድረግ አገልግሎት ይሰጣል።
  • ከኢንተርፕራይዞች ምንም ዓይነት ዋስትና (ማስያዣ) ሳይጠይቅ የማምረቻ መሣሪያውን ዋጋ 15-35% ብቻ በመክፈልና (በሴት/ሴቶች ለሚንቀሳቀስ ኢንተፕራይዝ 10% ብቻ በመክፈል) 15-35% የባለቤትነት መብት በመያዝ መሣሪያውን ወስደው መጠቀም ያስችላል።
  • የመሣሪያ ኪራይ ዋጋ ክፍያ ተመን በዓመታዊ ተቀናሽ ስሌት ሆኖ በዓመት በማኑፍክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽንና የግብርና ከሆነ 14% ሲሆን ለሌሎች የሥራ ዘርፍ 15% ነው።
  • አገልግሎትን ያለ ምንም የዋስትና መያዣ ማግኘት መቻሉ
  • የሚቀርቡ ማምረቻ መሣሪያዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ መደረጋቸው
  • በየወሩ አነስተኛ ክፍያ በመፈፀም የማሽን ባለቤት መሆን ማስቻሉ
  • ተከራይ የካፒታል ዕቃውን በኪራይ በማግኘቱ ያለውን ካፒታል ለሥራ ማስኬጃ የሚያውለው ስለሆነ ለካፒታል ቁጠባ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ
  • የተከራዮችን የንግድ እንቅስቃሴ፣ የመክፈል አቅም ሁኔታ ፍላጎት መሰረት ያደረገ የክፍያ መጠንና የክፍያ ጊዜ ስምምነት ማድረግ የሚያችል መሆኑ
  • እንደ ጥሬ ገንዘብ ለሌላ ላልተፈለገ ዓላማ የማይውል መሆኑ
  • ተከራዩ የጥሬ ገንዘብ ፍሰቱን በዕቅድ እንዲመራ ማስቻሉ
የአዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ የዋና መሥሪያ ቤት እና በየክፍለ ከተሞቹ ያሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አድራሻ
ቅርንጫፍአድራሻስልክ ቁጥር
ዋና መሥሪያ ቤትቸርችል ጎዳና፣ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ. ሕንጻ፣ 5ኛ ፎቅ011 12 62 411/ 011 12 63 514
አቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ አንደኛ ፎቅ011 872 13 62
የካ ቅርንጫፍየክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ ምድር ቤት 011 872 07 06
ቦሌ ቅርንጫፍየክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ ምድር ቤት 011 872 15 90
ጉለሌ ቅርንጫፍየክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ ምድር ቤት 011 872 16 10
ኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍየክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ አራተኛ ፎቅ011 872 37 52
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍየቀድሞ ሴፍዌይ ሱፐር ማርኬት ሕንጻ011 872 35 96
አዲስ ከተማ ቅርንጫፍየክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ አራተኛ ፎቅ 011 872 04 07
አራዳ ቅርንጫፍየክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ ሶስተኛ ፎቅ011 126 42 33
ቂርቆስ ቅርንጫፍየክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንጻ፣ ሶስተኛ ፎቅ 011 558 45 58
ልደታ ቅርንጫፍጎማ ቁጠባ የቀድሞ ልደታ ክፍለ ከተማ ሕንጻ 0913 37 59 48
ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ አራተኛ ፎቅ 0911 44 22 25

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …