መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር
addis-raiffeisen-logo

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ2003 ዓ.ም. በኅብረት ሥራ ሠራተኞችና ባለሙያዎች የተቋቋመ የኅብረት ሥራ የፋይናንስ ተቋም ነው። የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የኅብረት ሥራ ባለሙያዎችና ሠራተኞችን በአባልነት በማቀፍ በዚህ ዘርፍ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከት የተቋቋመ ማኅበር ነው። ስሙን የወሰደው ከ Friedrich Wilhelm Raiffeisen ሲሆን፤ ራፋይሰን በ19ኛው ምዕት ዓመት የኖሩ፣ በዜግነት ጀርመናዊ የነበሩ፣ የመጀመሪያውን የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማኅበር ያስጀመሩ የፋይናንስ የኅብረት ሥራ አባት ናቸው።

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

የአባላት ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ሞዴል የኅብረት ሥራ የፋይናንስ ተቋም ሆኖ መገኘት ነው።

ዓላማ

 • መላውን የኅብረት ሥራ ቤተሰብ በአባልነት በማሰባሰብ ተደራሽ መሆን
 • በተለያየ ስልት ቁጠባ በማሰባሰብ በተመጣጠነ ወለድ የብድር አገልግሎት መስጠት
 • ብድርን መሠረት ያደረገ የህይወት መድን አገልግሎት መስጠት
 • ለአባላት ሥልጠና እና የምከር አገልግሎት መስጠት
 • በማኅበራዊ አገልግሎት ተሳታፊ መሆን

ተልዕኮ

መላውን የኅብረት ሥራ ቤተሰብ በአባልነት በመመዝገብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ባንክ ነክ የፋይናንስ አገልግሎት ለአባላት መስጠት ነው።

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

 • መደበኛ ቁጠባ - 7% ወለድ ያስገኛል
 • የፈቃደኝነት ቁጠባ - 7% ወለድ ያስገኛል
 • የቁርጠኝነት ቁጠባ - 7% ወለድ ያስገኛል
 • የጊዜ ገደብ ቁጠባ - 8% ወለድ (ከዚያ በላይ እንደተቀማጩ መጠን በስምምነት የሚወሰን ይሆናል)
 • የአደራ ገንዘብ ማስተዳደር-  7% ወለድ ያስገኛል

ብድር

 • የሚበደረው ላይ 13.5% ወለድ ይኖረዋል
 • የተቀማጩን (የቆጠበውን) አራት እጥፍ መበደር ይቻላል
 • ለቤት ልማት፣ ለሕክምናና ለትምህርት ቅድሚያ ይሰጣል

የብድር የህይወት መድህን

 • የተበደረው ገንዘብ 1.5% ይቆረጣል
 • ተበዳሪ አባል ቢሞት ለቀሪው ብድር ሙሉ ሽፋን በመስጠት ዕዳውን መዝጋት
 • የኅብረት ሥራ ቅጥር ሠራተኛ፤ ባለሙያ ወይም ቤተሰብ የሆነ
 • የኅብረት ሥራ መርሖችንና ዕሴቶችን የተቀበለ
 • በመደበኛነት ከገቢው 5% ወይም ብር 300.00 እና ከዚያ በላይ መቆጠብ የሚችል
 • የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1000.00 ሆኖ አምስት ዕጣዎችን መግዛት የሚችል (4 - ዕጣዎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚያበቃ)
 • የመመዝገቢያ ብር 200 መክፈል የሚችል
 • የግ ክልከላ የሌለበት
 • የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነ

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር አድራሻ

 • አዲስ አበባ ካዛንቺስ ቶታል አጠገብ በአዲስ አበባ የቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ዩኒየን ጽሕፈት ቤት ግቢ ውስጥ
 • 011 833 3582
 • 011 833 3580
 • 0920 322502
 • 0911 241081

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …