መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ሙስጠፋ ጀማል ብረታ ብረት

ሙስጠፋ ጀማል ብረታ ብረት

ሙስጠፋ ጀማል ብረታ ብረት ድርጅት በአቶ ሙስጠፋ ጀማል ባላቤትነት የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው የተመሠረተው። ድርጅቱ በዋናነት የፍሬንች በሮችን የሚሠራ ሲሆን በተጨማሪም አጠቃላይ የብረታ ብረት ሥራዎችን ይሠራል።

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች

  • የአልጋ ሥራ
  • አጠቃላይ የብረት ሱቅ ሥራዎች
  • አጠቃላይ ከብረት ጋር ተያያዥ የሆኑ የቢሮ ሥራዎች
  • የመስታወት እና የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
  • ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ተጣጣፊ በሮች
  • በብረት ተዋቅረው የሚሠሩ ቤቶች እና መጋዘኖችን

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ሙስጠፋ ወደ ብረታ ብረት ዘርፍ ለመግባት የአንድ ዓመት ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ ነው ወደ ሥራው የገቡት። ድርጅቱን ከመመሥረታቸው በፊት ተያያዥ የፈጠራ ሥራዎችን ሲሠሩ ቆይተዋል፤ እነዚህም የፈጠራ ውጤቶች የተለያየ ዲዛይን ያላቸው የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን በራሳቸው ፈጠራ በማምረት ለገበያ ያቀርቡ ነበር። በፈጠራ ሥራም ሰርተፍኬት አላቸው። በምድጃው ሥራ ሁለት ዓመት ተኩል ከሠሩ በኋላ  የተወሰኑ መሠረታዊ እቃዎች በመግዛት በ2008 ዓ.ም ወደ ብረታ ብረት ሥራ ተሠማርተዋል። ወደ ብረታ ብረት ሥራ ሲገቡ ሥራው ቀሏቸው ነበር ምክንያቱም የፈጠራ ሥራ ሲሠሩ ስለነበር የተሠራ ሥራን አይቶ መሥራት አልከበዳቸውም። አቶ ሙስጠፋ በብረታ ብረት ሥራ የአምስት ዓመት የሥራ ልምድ አካብተዋል።

ድርጅቱ ለአንድ ቋሚ ሠራተኛ እና አምስት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል ፈጥሮ እየሠራ ይገኛል። ድርጅቱ ሥራ ሲጀምር የመነሻ ካፒታል ሁለት ሺህ ብር የነበረ ሲሆን አሁን ካፒታሉ ሶስት መቶ ሺህ ብር ደርሷል። እንዲሁም የሀምሳ ሺህ ብር እና የመቶ ሺህ ብር ብድር ተበድሮ ሁለቱንም ከፍሎ ጨርሷል። ይህ ድርጅት የመኖሪያ ቤት የአምስት ፎቅ በሮች እና መስኮቶች በአምስት ቀን የማጠናቀቅ አቅም አለው።

ሙስጠፋ ብረታ ብረት ፍሬንች በሮችን እንደ መጠናቸው ቢለያዩም ከዘጠና ሳንቲም ጀምሮ እስከ ሶስት ሜትር ስፋት ያለው በር ከስድስት ሺህ ብር ጀምሮ እስከ ሃያ አምስት ሺህ ብር ድረስ ያስከፍላል። በሚሠራቸው ሥራዎች ጥራት ብዙ  ደንበኞችን ማፍራት ችሏል። ይህም ምርቱ ጥራት ስላለውና እና ደንበኞች በአክብሮት ስለሚስተናገዱ እንደሆነ የድርጅቱ መሥራች ጠቅሰዋል።

 

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በሰው በሰው  ነው። ሩፋኤል፣ ኮዬ እና ሰሚት አካባቢ ሰፋ ያሉ ሥራዎችን ሰርቶ አስረክቧል። የቢሮ ሥራዎችን በስምምነት ሥራው ምን ምን ያካትታል የሚለው ታይቶ በመስማማት ይሠራል። ለምሳሌ መስታወት ሥራ፣ አሌክትሪክ መሥመር ዝርጋታ፣ መስኮት እና መጸዳጃ ቤት በሥራው ውል ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

አቶ ሙስጠፋ ችግሮች ሲፈጠሩባቸው በራሳቸው መንገድ እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ይፈታሉ።  “ቴክኖሎጂ መጠቀም ለሥራ ጠቃሚ ነው፤ ሥራን በጣም ያቀላል፣ ከጥራት እና ከጊዜ አንፃር በጣም ወሳኝ ነው” ኡላሉ አቶ ሙስጠፋ። እንዲሁም ኢንተርኔት በመጠቀም ዩቲዩብ ላይ ሥራዎችን በማየት ኮፒ እያደረጉም ይሠራሉ።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ ወደ ፊት የተሻለ ወርክ ሾፕ በመክፈት አዳዲስ ነገሮችን የመሥራት እቅድ አለው። አቶ ሙስጠፋ አዳዲስ ዲዛይኖች ያላቸው በሮች (ለምሳሌ በሪሞት ኮንትሮል የሚከፈቱ) ከውበት ጋር በማቀናጀት ዘመናዊ እና ውብ ሥራዎችን የመሥራት እቅድ አላቸው። ጨረታ ለመሳተፍ ሞክረው ነበር። በ kefta.merkato.com በኩል የዶሮ ቤት ጨረታ ሞክረው አሸንፈው ነበር፤ ግን በነበረው የሥራ የቦታ ጥበት ምክንያት ሳይሠሩት ቀርተዋል። ወደ ፊት ሰፋ ያለ የሥራ ቦታ ሲያገኙ አግልግሎቱን በመጠቀም ጨረታ የመጠቀም እቅድ አላቸው።

አዲስ ወደ ብረት ዘርፍ ለሚገቡ ሰዎች “ስለ ሥራው እውቀት ያስፈልጋል ምክንያቱም ዘርፉ በሰው አሠራዋለሁ የሚባል ስላልሆነ ማለት ነው፤ እውቀት በጣም አስፈላጊ ነው። የብረት አይነቶች ምን ምን ናቸው? የቱን ብረት ለምን አገልግሎት መጠቀም እችላለሁ? የሚለውን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው ስለዚህ ወደ ብረት ዘርፍ ሲገቡ እውቀቱ ኖራቸው ቢገቡ መልካም ነው ብለዋል” የድርጅቱ መሥራች።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …