ድርጅቱ የተመሠረተው በቤተልሔም አዳነ 2011 ዓ.ም የግል ኢንተርፕራይዝ በመሆን ነው። ይህ ድርጅት የጽሕፈት መሣሪያዎችን እና የፅዳት እቃዎችን በተባለው ጊዜ በጥራት ለተገልጋዮች ያቀርባል።
ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት
ድርጅቱ የሚያቀርባቸው ምርቶች
- የጽሕፈት መሣሪያዎች፦ ወረቀት፣ እስክሪብቶ፣ መጻሕፍት፣ ደብተሮች እና አጠቃላይ የቤት እና የቢሮ የጽሕፈት መሣሪያ እቃዎች
- የፅዳት እቃዎች፦ መወልወያ፣ ሳሙና፣ መጥረጊያ እና አጠቃላይ ለፅዳት አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት እቃዎች
የድርጅቱ መሥራች የራሳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት በኢንጂነሪንግ ሥራ ተቀጥረው ለሁለት ዓመት ሠርተዋል። ይሁን እና ተቀጥረው በሚሠሩበት ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ቢሮ ውስጥ ስለሆነ የሚያሳልፉት ይህ ደግሞ ብዙ ልምድ ለመቅሰም እና ራሳቸውን ማሳደግ እዳይችሉ አድርጓቸው ነበር። ስለሆነም በውስጣቸው በነበረው ትልቅ የማደግ ሀሳብ በጽሕፈት መሣሪያ ሥራ የሚያውቁት አንድ ሰው ስለነበረ፤ እሱ ጋር እየሄዱ በመማር እና ሥራውን በማየት በቂ ልምድ ከወሰዱ በኋላ በሦስት መቶ ብር ካፒታል ቤተልሔም አዳነ የጽሕፈት መሣሪያ ድርጅት መሠረቱ።
ድርጅቱ ማንኛውንም ዓይነት የግዢ እቃ በበቂ ሁኔታ የማቅረብ አቅም ያለው ሲሆን ይህን በዘረጋው በቂ ኔትወርክ በመጠቀም እና ከአስመጪዎች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሚፈለገውን እቃ በጥራት እና በተባለው ጊዜ ያቀርባል።
ይህ ድርጅት ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ የሚሠራው ጨረታ ላይ በመሳተፍ ነው። ይህም 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚወጡ ጨረታዎችን በ2merkato Tenders ሞባይል አፕ በመከታተል ነው የሚሳተፈው። ለዚህም ማሳያ ከሃምሳ በላይ ጨረታዎች ላይ የተሳተፈ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ወደ ሃያ አምስት ጨረታዎችን ማሽነፍ ችሏል። ድርጅቱ በዋናነት ከፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ጋር በመሆን ብዙ ሥራዎችን የሚሠራው። እንደ ተጨማሪ ከመንግሥት ቢሮዎች እንዲሁም ከትምህርት ቤቶች ጋር ይሠራል።
ድርጅቱ ሥራዎቹን የሚያስተዋውቀው መልካም የሆነ ሥራ በመሥራት ሲሆን ሥራው ጥሩ ከሆነ የተሠራለት ሰው ሌላ ሥራ ይዞ ይመጣል ለሌላም ሰው ስለ ሥራው መልካምነት ይመሰክራል። ሁለተኛው ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው በከፍታ ፓኬጅ በመጠቀም የገበያ ትስስር የሚያገኝበት በ2merkato.com ላይ ባለው ማስታወቂያ ሲሆን በዚህም ሰዎች እየደወሉ ሥራዎችን ሠርቷል።
ድርጅቱ በአሁን ሰዓት የካፒታል መጠኑን ወደ አምስት መቶ ሺህ ብር ያሳደገ ሲሆን በተጨማሪም ለሁለት ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል መፍጠር ችሏል። ይህ ድርጅት እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ የቻለው ችግሮች ሲያጋጥሙት ተስፋ ባለመቁረጥ ሥራውን በማስቀጠል እና ከሰዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ በመፈለግ ነው። በተጨማሪ ምንም አይነት ሥራ ትንሽ ወይም ትልቅ ሳይል ሁሉንም ሥራ ተቀብሎ መሥራቱ ለእድገቱ ጥሩ ምክንያት ሆኖአል።
የኮቪድ ተፅዕኖ
በኮቪድ ወቅት ሙሉ በሙሉ ሥራ ቆሞ ነበር። ከአዋሽ ባንክ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ብድር የወሰደ ቢሆንም ከነበረው ችግር አንጻር ብዙ ጠቃሚ አልነበረም። ከዚህም ጋር ተያይዞ የእቃ አቅርቦት ችግር እና የዶላር መጠን በበቂ ሁኔታ አለማግኘት፤ እንዲሁም ወቅታዊ የሆኑ ሀገራዊ ችግሮች ምክንያት ብዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጀት ወደ ሌላ መዞር፤ የሚወጣውን የጨረታ መጠን እንዲቀንስ አድርጎታል። ይህ ደግሞ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሥራዎችን የሚሠራው በጨረታ ስለሆነ ነገሮችን ከባድ አድርጓቸዋል።
ምክር እና እቅድ
ድርጅቱ ወደ ፊት ከሦስት ዓመት በኋላ ሌሎች ፈቃዶች በማውጣት ሌሎች ሥራዎችን ለመሥራት እና ብሎም ወደ ኅትመት ሥራ ለመግባት፣ ከዛም በረጅም ግዜ እቅድ ወደ አስመጪ እና ላኪ ሥራ ለመሠማራት እቅድ አለው።
“ወደ ጽሕፈት ሥራ ዘርፍ የሚገባ ሰው ሰዓት በአግባቡ መጠቀም የሚችል መሆን አለበት። ሥራው በጣም ጥረት ስለሚፈልግ የሥራ ተነሳሽነት ያለው፣ ተስፋ የማይቆርጥ ሰው ወደዚህ ሥራ ቢገባ ጥሩ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል” የድጅቱ መሥራች።