መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ብሩክ ኤፍሬም እና ጓደኞቻቸው ቀርከሃ፣ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ
bamboo-folding-table

ብሩክ ኤፍሬም እና ጓደኞቻቸው ቀርከሃ፣ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2013 ዓ.ም በአቶ ብሩክ ወልደ ሐዋርያት እና አራት መሥራች አባላት በአንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ካፒታል ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች የቀርከሃ እና አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን ነው። ድርጅቱ በቀን ሰላሳ ወንበር የማምረት አቅም አለው።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች

  • የእንጨት እና የቀርከሃ ጠረጴዛ
  • የእንጨት እና የቀርከሃ ሶፋ በተለያየ ዓይነት ዲዛይን
  • ከእንጨት እና ቀርከሃ የተዋቀረ ኮንትሮል ብፌ
  • የእንጨት እና የቀርከሃ አልጋ ለሕጻናት እና ለአዋቂዎች
  • የቤት ውስጥ እቃዎች ከቀርከሀ
  • የሆቴል ውስጥ ወንበሮች
  • ለሆቴል እና ለትንንሽ ምግብ ቤቶች እንዲሁም ካፌዎች የሚያገለግሉ ፓርቲሽኖች
  • የራስጌ መብራቶች
  • ማማሰያ
  • የፀጉር እና የተለያዩ ጌጣጌጦችን እንዲሁም በኢንተርኔት ላይ የሚገኙ አጠቃላይ የቀርከሃ መገልገያዎችን በጥራት ያመርታል

ምሥረታና ዕድገት

አቶ ብሩክ ወደ ቀርከሀ ሥራ ሊሰማሩ የቻሉበትን ምክንያት እንዲህ ሲሉ አስረድተዋል። አቶ ብሩክ ያደጉበት አካባቢ ዑራኤል አካባቢ ስለሆነ እዛ አካባቢ ደግሞ ብዙ የቀርከሃ ቤቶች ነበሩ። ልጅ እያሉ ከትምሕርት ሰዓት ውጪ ከጓደኞቻቸው ጋር ሥራ ያግዙ ነበር፤ ትንሽ ሥራ ሲለምዱ በሳምንት በአሥራ አምስት ብር ደመወዝ ሥራ ጀምረው ሠርተዋል። የሥራው ፍቅር ስለነበራቸው ቀስ በቀስ ሙያውን በደንብ እየለመዱ ሲመጡ ቻይና ድረስ በመሄድ የቀርከሃ ሥራ መሠልጠን በራሳቸው የመሥራት ፍላጎት አሳደረባቸው። በተጨማሪም የቀርከሃ ብዙ ጥቅሞችን በመመልከታቸው ወደ ሙያው ሊሰማሩ ችለዋል። የቀርከሃ ሥራ ላይ በደንብ ለማተኮር የቻሉበት ምክንያት የቀርከሃ ተክል አገራችን ወስጥ በስፋት ይገኛል። ሰው በአብዛኛው የሚጠቀምበት ግን ለእንስሳት ምግብ እና ለአጥር ብቻ ነው። ቀርከሃ ለተለያዩ ፈርኒቸር ሥራዎች እና የተለያዩ የቤት ውስጥ እቃዎች ብሎም ለምግብነት የሚውል እፅዋት ነው። የሀገራችን ማኅበረሰብ እነዚህን የቀርከሀ ጥቅሞች ግንዛቤ የለውም።

ድርጅቱ ወደ ቀርከሃ በተለየ ለማተኮር የቻለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

  • ቀርከሃ ከሎች ዕፅዋት አንጻር የተሻለ የካርቦን መጠንን የመቀነስ አቅም አለው
  • በሀገራችን ምንም ያልተነካ የጥሬ እቃ አቅርቦት አለ በዘርፉ
  • አንድ የቀርከሃ ተክል ከተተከለ በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ለምግብ ያገለግላል ከሶስት አመት በኋላ ደግሞ ለኮንስትራክሽን ያገለግላል።
  • ቀርከሃ ምግብ፣ ልብስ፣ ጫማ፣ ሴራሚክ፣ ኮርኒስ፣ ቦርድ፣ ይሆናል እና በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወለሎች  ላይ ተነጥፎ ለረጅም ጊዜ የማገልገል አቅም አለው።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ድርጅቱ በአሁን ጊዜ በብዛት የቡና ጠጡ መቀመጫ ወንበሮችን እያመረተ ይገኛል። ድርጅቱ ጥራቱን የጠበቀ ሶፋ ከዐሥራ ሁለት ሺህ እስከ ዐሥራ ሥፕስት ሺህ ብር ድረስ ለገበያ ያቀርባል። ደንበኛ የሚያገኘው ደግሞ በባዛር እና በሰው በሰው ወይም ደግሞ የቀርከሃ ሥራ ይሠሩ ከነበሩ እና ከሚሠሩ ሌሎች ባለሙያዎች በሚመጣ ጥቆማ ነው። ሌላው የቀርከሃ ምርት ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች እድሳት ወይም ጥገና ሲያስፈልጋቸው አገልግሎቶች በመስጠት በመገናኘት ሌላም ሥራ ሲፈልጉ ቀጥታ ወደ እነሱ ይመጣሉ። ድርጅቱ ለሦስት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ መጥፎ ነበር ሰው መጥቶ እቃውን እንኳን መንካት አይፈልጉም፤ ብዙ ሰው ይነካዋል ብለው ስለሚያስቡ ይህ ደግሞ ጥንካሬውን ምቾትን በመንካት ነው ማወቅ የሚቻለው – ሰው ደግሞ ዝም ብሎ ዐይቶ ያልፋል። ይህ አንዱ ጉዳት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሆቴሎች፣ ኑ ቡና ጠጡ ብዙ አዳዲስ ይከፈቱ ስለነበር ብዙ ትዕዛዝ ከነሱ ይመጣል። ኮቪድ ሲመጣ ግን አዲስ የሚከፈቱ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ቆመው የነበረ ሲሆን አዲስ ትዕዛዝ ምንም አልነበረም። እንዳንድ ለእድሳት ብቻ ሲፈልጉ ካልሆነ በቀር ማለትም ቀለም፣ ስብራት ሲያጋጥም ማደስ የመሳሰሉት ሥራዎች ካልሆኑ ሌሎች ሥራዎች በጣም ቀንሰው ነበር። አንዳንድ ቦታዎች ጋር በነጻም የሠሩበት ጊዜ ነበር።

ምክር

አቶ ብሩክ ለቀርከሃ ሥራ በተቻለ መጠን ዘመናዊ መሣሪያዎችን መጠቀም ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል። ለምሳሌ ቀርከሃ ለመሥራት አንድ ሰው በቀን ሃያ ወንበር ሊበሳ ይችላል። በቴክኖሎጂ ወይም በማሽን ግን ከአርባ እስከ ሥልሣ ወንበር መብሳት ይችላል። ድረ-ገጾች ላይ የሚታዩ፣ ሥራን የሚያሻሽሉ እና የሚያቀሉ ብዙ መንገዶችን መማር ይቻላል። እንዲሁም በዘርፉ የሚሠሩ ሰዎች በጣም ጥቂት ስለሆኑ  ወይም ብዙ ባለሙያ ስለሌለ የሚያማክሩት ሰው የለም  – አንዳንድ ደንበኞች  ሲመጡ ሀሳብ ከሚሰጡት በስተቀር – ስለዚህ ኢንተርኔት በመጠቀም ነው እስከአሁን እየተንቀሳቀሱ ያሉት። ስለዚህ ቴክኖሎጂን መጠቀም በጣም ጠቃሚ ነው ይላሉ የድርጅቱ መሥራች።

ቢዝነስ የሚሠራ ሰው ሠራተኞችን በደንብ መያዝ አለበት፤ ቻይ መሆን እና ምክንያታዊ መሆን ይስፈልጋል ። ደንበኛ ሲመጣ በፈገግታ መቀበል፣ ለማንኛውም ዓይነት ደንበኛ ደግሞ አክብሮት መስጠት ያስፈልጋል።

ድርጅቱ ምን ምን የሥራ እድሎችን እንዳሉ ለይቶ በማወቅ፣ ትልልቅ ማሽኖችን በማስገባት፣  ድርጅቱን ትልቅ ደረጃ ለማድረስ አቅዶ እየሠራ ይገኛል።  እያደገ ሲሄድ ደግሞ ቀርከሃ ምግብ፣ ልብስ፣ ጫማ፣ ሴራሚክ፣ ኮርኒስ፣ ቦርድ፣ ለኮንስትራክሽን ግባዓቶች፣ ከሁለት አመት በሁዋላ ቀስ በቀስ በትንሹ እንዚህን ነገሮች ለማምረት አስበው እየተንቀሳቀሱ ነው።

አቶ ብሩክ የሚከተለውን ምክር አክለዋል የቀርከሃ ምርት በብዛትስ ለሚገኝ በደንብ የመሥራት እድል አለ ስለዚህ እንጠቀምበት፤ ይህ ደግሞ ገበሬውንም ይጠቅማል። ጃፓን እና ቻይና ቀርከሃን በጣም ይጠቀማሉ ለጥርስ ብሩሽ፣ አልጋልብስ፣ ሸበጦች፣ ምግብ እና ልብስ ከቀርከሃ ነው የሚጠቀሙት፤ እኛ አገር ደግሞ ቢያንስ ከትንሹ ቀስ በቀስ መጠቀም ብንጀምር ጥሩ ነው ብለዋል።

ማኅበረሰባችን ለሀገር ውስጥ ምርት ያለው አመለካከት ቢሻሻል  እና የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ፍላጎት ቢጨምር ጥሩ እንደሆነ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …