መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ኤጀንሲው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሠራር ለውጦች አደረገ
document-authentication

ኤጀንሲው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሠራር ለውጦች አደረገ

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ጥሬ ገንዘብን ሥርዓት ለማስያዝ ሲባል መንግስት የተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎች መውሰዱን ተከትሎ አንዳንድ የአሠራር ለውጦች አደረገ።
ይህንኑ ተከትሎ ህገወጥነትን ለመከላከል እና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ሲባል ከዛሬ መስከረም 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ኤጀንሲው ባደረገው የአሰራር ማሻሻያ መሰረት የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ተገልጋዮች የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው በሚከተሉት መንገዶች መፈጸም ይኖርበታል።

  • በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት። 
  • በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት።
በመሆኑም የሽያጩ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ ክፍያው ከላይ በተገለጸው አግባብ የተፈጸመ ስለመሆኑ የሚገልጽና በባንኩ ማህተም የተደገፈ የሂሳብ ማስተላለፊያ (#Bank Transfer Slip) የሰነድ ማስረጃ መቅረብ ያለበት መሆኑን ጨምሮ አሳውቋል። 
በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል ሌሎች የአሰራር ማሻሻያዎች እስኪደረጉ ድረስ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ኤጀንሲው ላልተወሰነ ጊዜ እንደማይሰጥ ገልጿል።
የዜና ምንጭ፦ የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …