መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ የቆዳ ፋብሪካዎችን ጎበኙ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ የቆዳ ፋብሪካዎችን ጎበኙ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ሚ/ዴኤታ አቶ ተካ ገ/የስ ትናንትና ነሐሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም በተለያዩ የቆዳ ፋብሪካዎች ተገኝተው የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በቆየው የስራ ጉብኝት ላይ የውጭ ምንዛሬ፣ የመሬት፣ የመብራት መቆራረጥ፣ የተማረ የሰው ኃይል፣የመስሪያ ካፒታል ችግሮች እንዳሉ በዘርፉ ተዋንያኖች የተጠቆመ ሲሆን እነዚህንና መሰል ችግሮች ዘርፉን ወደ ኃላ እያስቀሩት በመሆኑ በመንግስት በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል የጉብኝቱ ዋና አላማ በአገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለውን የቆዳ ኢንዱስትሪ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ምን ችግሮች እንዳሉበትና በመንግስት በኩል እንዴት መፍታት እንዳለበት ከመድረክ ውይይቶች በተጨማሪ በፋብሪካዎች ተገኝቶ ሁኔታውን ለመረዳት ብሎም ከባለሃብቶች ጋር አብሮ የመስራትና ችግሮችን በጋራ የመፍታት ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ አስር አመታት ባስቀመጠው የልማት መሪ ዕቅዱ ላይ አዳዲስ ፋብሪካዎችን የማስፋፋት ነባር ፋብሪካዎችን የማጠናከርና የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬ ገቢን የማሳደግ እና የስራ ዕድል መፍጠር በእቅዱ ማስቀመጡን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ይህንንም ለማሳካት ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅትም አንዳንድ ፋብሪካዎች እስከ 15 በመቶ ሌሎች ደግሞ ከ15 በመቶ በታች የማምረት አቅማቸውን ተጠቅመው እያመረቱ እንደሆነ መረዳት ችለናል ያሉት አቶ መላኩ ያለንን እውቀት ሃብትና እና ልምድ ተጠቅመን የማምረት አቅማችን አሳደግን ማለት የወጪ ምንዛሬ የገቢያችን ፣ የስራ ዕድል እንዲሁም ሃገሪቱ ያላትን የቆዳ ሃብት በእጥፍ መጠቀም የሚቻልበትን አቅም የሚፈጥር በመሆኑ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉትን ችሮች ለመፍታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበት ገልጸዋል፡፡
የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …