መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / የምግብ ዝግጅት ሥራ – ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት
betelhem-belete

የምግብ ዝግጅት ሥራ – ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት

ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት የተመሠረተው በወ/ት ቤተልሔም በለጠ ነው።  የመሥራቿ የምግብ ሥራ ፍላጎት እና የሥራ ልምድ እንዲሁም እውቀት ተድምሮ ድርጅቱን ስትመሠርት ከነበረው አንድ የሰው ሀይል አሁን ለደረሰበት ዐስራ አንድ ሠራተኞች ሊደርስ ችሏል። ወ/ት ቤተልሔም ድርጅቱን ስትመሠርት የነበራት ሀሳብ ጠንክሮ በመስራት ራስን መለወጥ ብሎም ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ነው።

ወ/ት ቤተልሔም ሥራውን የጀመረችበት ምክንያት ለሙያው ያላት ፍቅር ትልቅ ተነሳሽነት በውስጧ ስላሳደረባት እንደሆነ ገልፃለች። እንዲሁም መርካቶ አካባቢ ስትሠራው የነበረው የንግድ ሥራ ለምግብ ዝግጅት ሥራው ትልቅ አስተዋጽዖ አለው ትላለች። ድርጅቱ በኮሮና ምክያት ትልቅ ችግር ገጥሞት የነበረ ሲሆን አሁን እየተሻለ እንደሆነ ወ/ት ቤተልሔም በለጠ አስረድታለች።

 

 

ወ/ት ቤተልሔም ከቤተሰቦቿ ጋር የሆቴል ሥራ ለመሥራት ያጋጠማት ዕድል ሙያውን በደንብ ለመለማመድ ረድቷታል፤ ቀጥሎ ደግሞ በሙያው ሥልጠና በመውሰዷ ሥራውን ስትጀምር በደንብ እንዳገዛት ትናገራለች።

 

ቤተልሔም ምግብ ዝግጅት ከሚሰጠው የምግብ ዝግጅት አገልግሎት መካከል

  • ለልደት
  • ለሰርግ
  • ለሀዘን
  • የብፌ ሥራዎች
  • ለምርቃት እና ለሌሎችም ፕሮግራሞች
  • ማንኛውም ስብሰባ ከሀምሳ ሰው በቻች ሰርቶ በማስረከብ ከሀምሳ ሰው በላይ ወደ ዝግጅቱ ቦታ በመሄድ
  • ጥብሳ ጥብስ ለሚፈልጉ ተገልጋዮች(ደንበኞች) ሁሉ ነገር በማዘጋጀት እና በማሸግ ያስረክባል። እንዲሁም አጠቃላይ የካፌ አገልግሎትም ይሰጣል።

ምሥረታና ዕድገት

ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት ከተመሠረተ አራት አመት ሆኖታል። በአንድ መስራች አባል እና በሦስት ሺህ ብር ካፒታል የተመሠረተ ድርጅት አሁን ለዐሥራ አንድ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። ድርጅቱ ማንኛውንም አይነት የምግብ ሥራ በጥራት መሥራት ይችላል። ለምሳሌ ለአምስት መቶ ሰው የሚሆን ምግብ ዝግጅት አገልግሎት በሁለት ወይም በሦስት ቀን በጥራት የማድረስ አቅም አለው።

 

 

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ በቢዝነሱ ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅዕኖ  አሳድሮ ነበር። በመጀመሪያዎቹ የኮሮና ወረርሽኝ ወራት ገበያ ምንም አልነበረም፣ ሰው የውጭ ምግብ መመገብ ሙሉ በሙሉ አቁሞ ነበር። ይህ ደግሞ ገበያ ሙሉ በሙሉ  ዘግቶብን ነበር፤ በጣም ዕዳ ውስጥ ይከታል። ለዚህ ያገኘነው መፍትኄ  ቢኖር ፋይናንሱን ማስተካከል፣ ሠራተኛ መቀነስ (ሃያ ሶስት የነበሩ ሠራተኞችን ወደ ዐሥራ አንድ ቀንሰናል)፣ እና እንደዚህ እይነት አርምጃዎችን በመውሰድ እንዲሁም የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም እንዳለፉት እና እያለፉት እንደሆነ ወ/ት ቤተልሔም አስረድታለች ።

ማስተዋወቅ፣ ማስፋፋት እና ምክር

ማስታወቂያ የሚጠቀሙት ብዙም አይደለም። ሥራቸው የሚተዋወቅላቸው በሰው በሰው (word of mouth) እና ቢዝነስ ካርድ በመጠቀም ነው። ለምግብ ሥራ ቦታ ትልቅ ሚና ይጫወታል፤ ጥሩ ቦታ ከሆነ ያለ ማስታወቂያም ጥሩ ገቢ ያስገባል ያለበለዚያ በጣም አስቸጋሪ ነው። ቴክኖሎጂ መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው። ለማስታወቂያ እንዲሁም ሥራ ለመሥራት እንዲሁም የተለያዩ እዳዲስ ነገሮችን ለመማር ይጠቅማል።

እንደ ቢዝነስ መመካከር ልምድ እና ተሞክሮ መቀያየር በጣም ጥሩ ነው። ተመሳሳይ ሙያ ዘርፎች ላይ ይህን እንዲህ ብታረጊው ወይም እዚህ ቦታ ላይ እኮ ይህን ብታረጊው ያዋጣል ወይም ይህን እንዲህ ብታረጊው ጥሩ ነው የሚሉትን ነገሮች ለማስተካከል ይረዳል።

ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት በምግብ ዝግጅት ሥራ የተማረባቸው ነገሮች ተመጣጣኝ የሆነ የሰው ሀይል ይዞ መንቀሳቀስ (ይህም ማለት አስፈላጊ ያልበዛ ወይም ያላነሰ) ለሥራው መሳካት እና ውጤታማነት አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ዋጋ ከመጨመር ይልቅ ምርት ማስቀረት የምንሄድበት የተሳሳተ አካሄድ ነበር። ይህ መንገድ የተሳሳተ እንደሆነ በማወቅ ዋጋ ጨምሮ ምርት ማቅረብ የተሻለ እና ውጤታማ እንደሚያደርግ በመረዳት ሊታረም ችሏል። አንድ ሥራ ስኬታማ ነው አድጓል የሚባለው በህይወት ላይ ለውጥ ካመጣ ለምሳሌ በራሱ የሚሄድ ከሆነ፣ ሥራው የነበረውን ጫና ካቀለለ፣ ራሱ መስመር እየያዘ ለውጥ ካመጣ እና በኔ ህይወት ላይ የሚታይ ለውጥ ሲያመጣ ሥራው አድጓል ለማለት ይቻላል ትላለች ወ/ት ቤተልሔም።

አክላም “መሪ ምንግዜም ከፊት ሆኖ መምራት መቻል አለበት አንተ ጠዋት ከገባህ ሁሉም ሠራተኞች ጠዋት ይገባሉ፣ ካረፈድክ ደግሞ ያረፍዳሉ። ማታ በጊዜ ከወጣህ ደሞ ክፍተትቱን አታውቅም፤ ማሻሻል ያለብህን አታውቅም። ስለዚህ መሪ ሁሌም ሥራውን በቅርብ በመከታተል ጥሩ አርአያ መሆን መቻል አለበት” ትላለች።

ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት ከአምስት እመት በኋላ ሰላሳ ሠራተኛ ለመቅጠር፣ እንዲሁም ሁለት ቅርንጫፍ ለመክፈት አቅዶ እየሠራ ነው። እቅድ ሲታቀድ ቦታ፣ ገንዘብ፣ አቅም፣ እውቀት ያገናዘበ መሆን መቻል አለበት።

ዐዲስ ወደ ምግብ ሥራ ለሚገባ ቢዝነስ ወ/ት ቤተልሔም የምትመክረው ምክር የምግብ ሥራ በጣም ከባድ እና አድካሚ ስለሆነ ትግስት ይፈልጋል፣  ሆደ ሰፊ መሆን ያስፈልጋል። ለምግብ ሥራ የተመቸ የመሥሪያ ቦታ ማግኘት ለቢዝነሱ ዕድገት ወሳኝ ስለሆነ ያንን ማሳካት ያስፈልጋል።

ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት በ2merkato ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የተዘጋጀውን የከፍታ (kefta.2merkato.com) የጨረታ መረጃ አቅርቦት እና የፕሮሞሽን (የገበያ ትስስር) አገልግሎት በተወሰኑ መልኩ ይጠቀማሉ። ወደፊትም የበለጠ በደንብ መጠቀም ያስባሉ።

የቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት በ2merkato ላይ ያለውን ሙሉ ፕሮፋይልን ለማግኘት፦ ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …