መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
dmt-sofa-1

ዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

ዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በ1999 ዓ.ም በአቶ ደረጄ አበራ ሲሆን የተለያዩ የቤት እና የቢሮ አቃዎችን ያመርታል።

ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል:-

  • አልጋ
  • ቁምሳጥን
  • የምግብ ጠረጴዛ
  • የቤት በር እና መስኮቶች
  • ሶፋዎች

የሶፋ ምርቶቹ ዓይነቶች በሦስት ይከፈላሉ፦ ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የዋጋ ተመን ያላቸው

  • ዝቅተኛ ሶፋዎች ከአስራ ሁለት ሺህ ብር ጀምሮ እስከ አስራ ስምንት ሺህ ብር
  • መካከለኛ ሶፋዎች ከአስራ ስምንት ሺህ ብር ጀምሮ እስከ ሰላሳ ሺህ ብር ድረስ
  • ከፍተኛ ሶፋዎች ከሰላሳ ሺህ ብር እስከ ስልሳ ሺህ ብር ድረስ

dmt-sofa

ምሥረታና ዕድገት

አቶ ደረጄ በራሳቸው ሥራ መሥራት ከመጀመራቸው በፊት የእንጨት ሙያውን የመማር አጋጣሚ ተፈጥሮላቸው ነበር፤ ከዛም በመቀጠል በጣልያናዊ ግለሰብ ቤት በእንጨት ሥራ በመቀጠር ዐሥራ ስድስት አመት ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ የሥራውን ዕድል በማየት እንዲሁም ትርፍ እና ኪሳራውን በማጥናት ዐይተው ሥራውን ሊጀምሩ ችለዋል። ዲኤምቲ በደንብ ከመጀመሩ በፊት አቶ ደረጄ በቤት ውስጥ አንዳንድ አነስ አነስ ያሉ ሥራዎችን ሲሠሩም ቆይተዋአል።

 

ዲኤምቲ ሲመሠረት የነበረው ካፒታል አርባ ሺህ ብር ነበር። አሁን ድርጅቱ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር (ብር 1,800,000) ካፒታል አለው። በደንብ አንቅስቃሴ በነበረት ጊዜ ለሃያ አምስት ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠር ችሎ ነበር። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ዐሥር ሠራተኞች እየሠሩ ይገኛሉ። የማምረት አቅም በተመለከት በፊት የኮሮና ወረርሽኝ ሳይመጣ በቀን ከዘጠኝ እስከ ዐሥራ ሁለት ሶፋ ያመርት ነበር፤ አሁን ግን በሳምንት ስድስት በቀን አንድ ሶፋ ይመረታል። በደንብ ከተሠራ በቀን እስከ ሁለትም ይመረታል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

“ኮቪድ ከባድ ነበር ምክንያቱም ዲኤምቲ የሚያመርተው ምርት ምግብ ነክ ነገር አይደለም ቢሆን ኖሮ ሰው ይግድ አስፈላጊ ስለሆነ ይገዛል፤ ነገር ግን የፈርኒቸር ሥራ የቅንጦት ሥራ ነው። ሰው ሲኖረው ሲተርፈው ነው መቀመጫ፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ የሚገዛው። ከዚህም በተጨማሪ በሥራ ቦታ ራሱ እንደልብ እየተነጋገርን ተቀራርቦ መሥራት አይቻልም።” ይላሉ አቶ ደረጄ።

ዲኤምቲ ለሥራ መቀዛቀዝ እንድ መፍትኄ አድርጎ የወሰደው እና የመጀመሪያዎቹን የኮቪድ ውቅቶች ያሳለፈው በኮሮና ወረርሽን ወቅት ቢዝነሱ ያጣውን ለማካካስ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ፣ ትርፍ ቀርቶ በዋና ወይም ትርፍ የሌለው ለድርጅቱ መሠረታዊ ፍጆታ አስፈላጊ የሚባሉ ነገሮችን ለሟሟላት እንዲሆን ተድርጎ በመንቀሳቀስ ነው።

ማስተዋወቅ፣ ማስፋፋት እና ምክር

እንደ አቶ ደረጄ ከሆነ ዐዲስ ወደ ሥራው ለመግባት የሚያስቡ ሰዎች መሠረታዊ ዕውቀት ሊኖራቸው ይገባል፤ በመጀመሪያ ሰው ራሱ ውስጡ የሚወደው ፍላጎቱን ማወቅ መቻልም አለበት። በመቀጠል የሚሠራውን ሥራ መውደድ። ሥራዬን እወደዋለሁ ወይ ብሎ ይጠይቅ። ከሱሶች ነጻ መሆን ለስራ ማደግ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። ገንዘብ አያያዝ በጣም ወሳኝ ነው። ገንዘብ አያያዝ ላይ ትልቅ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ስለ ገንዘብ አያያዝ ሥልጠና፣ በሙያው ሥልጠና፣ ስለ አደረጃጀት ሥልጠና፣ ይዘው ቢገቡ ጥሩ ነው ነገር ግን ዋናዎቹ እውቅት እና ፍላጎት ናቸው። ከዛ ይጀምሩት ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የጉለሌ ወረዳ ሥስት የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ለዲኤምቲ (DTM) የቤት እና የቢሮ እቃዎች እዚህ ለመድረስ አስተዋጽዖ እንዳለው አክለዋል።

ማሽኖች መጠቀም ጥሩ ነው፤ ነገር ግን በጣም ውድ ናቸው የራሳችው ቦታ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ሙሉ በሙሉ መተው ሳይተው ቀለል ያሉ ማሽኞች ስላሉ እነሱን መጠቀም በጣም ጠቃሚ ነው ይላሉ አቶ ደረጄ።

ዲኤምቲ ገበያ ውስጥ በደንብ ገብቷል። የደንበኛ ወይም የገበያ ችግር የለበትም፤ በፊት ድርጅቱ ሲመሠረት በተዘረጋው የገበያያ ትስስር አማካኝነት ቀጥታ የሚረከቡ አከፋፋዮች ከዐሥራ አምስት በላይ የብዛት ተረካቢ ደንበኞች እንዲኖሩት በማድረጉ በአሁን ወቅት ባለው ችግር ምክንያት (የጥሬ እቃዎች አቅርቦት መወደድ) ያለው የገበያ ትስስር በቂ ነው።

አቶ ደረጀ በቢዝነስ ውስጥ ምክር ስለመፈለግ እና ልምድ ስለማካፈል ሲናገሩ “ለአንድ ቢዝነስ መሳካት መመካከር ጥሩ ነው፤ አንድ ችግር ቢገጥም መፍትኄ ብዙ ሳይደክሙ እና ሳይከስሩ ማግኘት ስለሚቻል። ለምሳሌ አንድ ቢዝነስ ያለው ሰው የማይታየውን አቅጣጫ ሌሎች ቢዝነስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ያዩታል እንዲሁም እኛም የምናካፍለው ነገር አለ ስለዚህ መነገጋገር ጥሩ ነው። በፊት እሠራበት የነበረው ድርጅት የነበረው አለቃዬ ምንም ነገር አይደብቀንም ነበር፤ እኔ ውስጥ ያለውን እውቀት ተጠቀሙበት ይለን ነበር። ስለዚህ ልምድ ማካፈል በጣም ጥሩ እንደሆነ  በተግባርም ስላየሁት ልምድ ማካፈል ጥሩ ነው”

ዲኤምቲ በ2merkato ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በተዘጋጀው የከፍታ (kefta.2merkato.com) የጨረታ መረጃ አቅርቦት እና የፕሮሞሽን (የገበያ ትስስር) አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው። ከፍታ በሥራቸው ዘርፍ የሚወጡ የተለያዩ የጨረታ መረጃዎችን በማቅረብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ዲኤምቲ ወደፊት አሁን ካለበት ደረጃ የተሻለ ለመሆን አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ ደረጄ ጠቅሰዋል።

የዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር 2merkato ላይ ያለውን ሙሉ ፕሮፋይልን ለማግኘት፦DMT Household & Office Furniture 

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …