መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / እልልታ ሳሙና እና ዲተርጀንት ማምረቻ

እልልታ ሳሙና እና ዲተርጀንት ማምረቻ

እልልታ ሳሙና እና ዲተርጀንት ማምረቻ የተመሠረተው በወይዘሮ አዲስ ሕይወት እና አራት መሥራች አባላት በ2014 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የተለያዩ የንጽህና ውጤቶችን የሚያመርት ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በአጠቃላይ የልብስ፣ የእጅ፣ የእቃ ፈሳሽ ሳሙናዎችን በተለያየ መጠን ያመርታል፦

  • ፈሳሽ ሳሙና ባለ 5 ሊትር፣ ባለ 2 ሊትር፣ ባለ  1ሊትር
  • ሻምፖ  ባለ 5 ሊትር፣ ባለ 500 ሚሊ ሊትር
  • በረኪና ባለ 5 ሊትር፣ ባለ 800 ሚሊ ሊትር
  • ዲቶል ባለ 5 ሊትር፣ ባለ 500 ሚሊ ሊትር እና
  • ሌሎች የጽዳት ምርቶች በብዛት ጥራት ያላቸውን የንጽህና መጠበቂያና የኮስሜቲክስ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ድርጅቱ የተመሠረተው በሦስት ሴቶች እና በሁለት ወንዶች ነው። ወይዘሮ አዲስ ድርጅቱን ከመመሥረታቸው በፊት በመንግሥት ሥራ ተቀጥረው ሠርተዋል። የድርጅቱ አባላት ከማስተርስ የትምህርት ደረጃ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ የሚገኙ አባላትን በውስጡ የያዘ ነው። እልልታ ሳሙና እና ዲተርጀንት ሊመሠረት የቻለው አንደኛው ምክንያት የተሻለ ገቢ ለማግኘት፤ በንጽህና ዘርፍ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ማኅበረ ሰቡን እና ራሳቸውን ለመጥቀም፤ እንዲሁም ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በማሰብ፤ በተጨማሪ ደግሞ ያለውን የፋይናስ እና የጊዜ ነጻነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ድርጅቱ የተመሠረተው።

ንጽህና መጠቀሚያ ዘርፍ የመረጡት ብዙ ፈላጊ ስላለው ሲሆን፣ ብዙ ፈላጊ ስላለው ብቻ ግን ውጤታማ መሆን ይችላል ማለት አይደለም። እንደውም ብዙ ሥራ ይፈልጋል፤ ስለዚህ በሁሉም መለኪያ የተሻለ ምርት በማቅረብ ከቻልን ዘላቂነት አለው ሁለተኛ ደግሞ ሥራው ራሱ ደስ የሚል ሥራ ስለሆነ ነው ብለው ወደዚህ የሥራ መስክ ተቀላቅለዋል።

ድርጅቱ ሲመሠረት በአንድ ቀን አንድ መቶ ሊትር ፈሳሽ ሳሙና የሚያመርት የነበረ ሲሆን አሁን ግን የማምረቻ ማሽን በመግዛት በአንድ ቀን አምስት መቶ ሊትር ሳሙና እያመረተ ይገኛል። ከደንበኛ አስተያየት በመነሳት ድርጅቱ ሲመሠረት አሁን ትልቅ አቅም ያለው ማሽን መትከል እና  ምርቱ እያሻሻለ መምጣት ችሏል። ድርጅቱ በውስጡ ለሦስት ዜጎች የሥራ እድል መፈጠር ችሏል። እዚህ ደረጃ ለመድረስ ግን አንድ ቢዝነስ ሥራ ስላለ መዘናጋት የለበትም። ከሌሎች አምራቾች ጋር ውድድር ስላለ በየጊዜው ራስን ማሳደግ እና የተሻለ ሆኖ መገኘት አስፈላጊ ነው ሲሉ የድርጅቱ መሥራች ተናግረዋል።

እልልታ ሳሙና እና ዲተርጀንት ማምረቻ ምርቱን በር ለበር እየሄደ ያስተዋውቃል፤ በተጨማሪ ደግሞ ባዛሮች ላይ እና ሰንደይ ማርኬት ላይ በመሳተፍ ምርቱን ያስተዋውቃል። በዚህም እድል አብሮ ሰው በሰው የሚመጡ ሥራዎችን መሥራች ችሏል። በተጨማሪ ደግሞ በቴክኖሎጂ በኩል ሶሻል ሚዲያን ተጠቅሞ ደንበኖቹን ለመድረስ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። አሁን ደግሞ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት መጠቀም ምርቶቹን ማስተዋወቅና ጨረታ ላይ መሳተፍ ጀምሯል።

ዕቅድ እና ምክር

ድርጅቱ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ እንዲሁም በቀጣይ ከሦስት እስከ ዐምስት ዓመታት ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ የታወቀ የሳሙና እና ዲተርጀንት አምራችና አከፋፋይ የመሆን እቅድ አለው።

የድርጅቱ መሥራች ወደ ሳሙና ምርት ሲገቡ ዐጫጭር ሥልጠና የወሰዱ ቢሆንም ይህ በቂ ስላልሆነ በራስ ትጋት፣ ኢንተርኔት እና ሶሻል ሚዲያ በመጠቀም፣ እንዲሁም ከደንበኞች በሚመጣ አስተያየት ብዙ ዕውቀት በመቅሰም ራሳችውን አሳድገዋል፤ አሁንም እያሳደጉ ነው። ስለዚህ ማንም ሰው ወደ ዘርፉ ሲቀላልቀል አንደኛ ሥልጠና መውሰድ ወይም ሙያውን ማወቅ ያስፈልጋል፤ ሁለተኛ ደግሞ ዘወትር ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ቢገቡ ጥሩ ነው ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም “በደንብ የዲጂታል ማርኬቲንግ ሥልጠና  በፌስቡክ እና ቴሌግራም አጠቃቀም ላይ እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ የሚባሉ ሥልጠናዎችን ማግኘት ብንችል በጣም ይጠቅመናል። በከፍታ ተዘጋጅቶ የወስድነው የከፍታ አገልግሎቶችን አጠቃቀም እና የዲጂታል ሊትረሲ ሥልጠና በጣም ጠቅሞናል” ሲሉ የድርጅቱ መሥራች ሐሳባቸውን አክለዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ሀሌታው ሀ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ድርጅት የተመሠረተው በአቶ ዮናታን ታደሰ እና ሦስት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኅትመት …