መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሁሉንም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎችን አባል ለማድረግ ዓላማ ይዞ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር የፋይናንስ ተቋም ነው።

ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማ እና ዕሴቶች

ራዕይ

ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሁሉንም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች አባል ለማድረግና ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋምና በኢኮኖሚ የዳበረ ኅብረተ ሰብ መፍጠር ራዕይ ይዞ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ የገንዘብ ተቋም ነው።

ተልዕኮ

ፈቃደኛ የሆኑ የኅብረተ ሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ያላቸውን ዕውቀትን እንዲሁም ቴክኖሎጂን በመጠቀም አስተማማኝ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦት አባላቱ አንዲኖራቸው ማድረግ ነው።

ዓላማ

 • የአባላትን ገቢ ለማሳደግ የኑሮ ደረጃቸው እንዲሻሻል ማድረግ
 • የአባላትን በተለያየ ርዕስ የተሻለ ወለድ የሚከፈልበት ቁጠባ ማሰባሰብ
 • ለአባላት ፈጣንና ምቹ በሆነ መንገድ በተመጣጣኝ ወለድ የብድር አገልግሎት መስጠት
 • ከተለያዩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒዮኖችና ፌዴሬሽኖች ጋር ለተሻለ ዓላማና ልማት በትብብር መሥራት

ዕሴቶች

 • ግልጽነት
 • ታማኝነት
 • ታታሪነት
 • አለማዳላት
 • ተጠያቂነት
 • ምርታማነት

ድባብ፦ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

 • የመደበኛ ቁጠባ
 • የፍላጎት ቁጠባ
 • የጊዜ ገደብ ቁጠባ
 • የልጆች ቁጠባ
ድባብ የገንዘብ ቁጠባ ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማህበር እስከ 100,000.00 ሺህ ብር ድረስ የሚደርስ ብድር ለሚከተሉት ጉዳዮች ያበድራል።
 • ለንግድ
 • ለመኪና
 • ለቤት
 • ለትምህርት
 • ለማኅበራዊ ጉዳዮች የሚውል ብድር
የብድር ዓይነቶቹና ለመበደር በቅድሚያ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል፦

የበዓል ብድር፦ እስከ ብር 10,000.00 ድረስ

ብድሩን ለመበደር በቅድሚያ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
 1. አክሲዮን (ዕጣ) ቢያንስ 2 (ሁለት) እና ከዚያ በላይ ያለዉ
 2. የብድሩን 1/4 እና ከዚያ በላይ የቆጠበ
 3. በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሚመለስ
 4. በአባልነት ቢያንስ ሁለት ወር የቆየ
 5. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ካለው ያለዋስትና መበደር ይችላል
 6. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ከሌለው (ካነሰ)፣ ከማኅበሩ አባል የሆነ አንድ ሰው ዋስ ማቅረብ አለበት ወይም ከውጪ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ዋስ ማቅረብ ይገባዋል።

የሥልጠናና የትምህርት ብድር፦ ከ ብር 10,000.00 - ብር 20,000.00 ድረስ

ብድሩን ለመበደር በቅድሚያ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
  1. በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚመለስ
  2. አክሲዮን (ዕጣ) ቢያንስ 5 የገዛ
  3. የብድሩን 1/4 እና ከዚያ በላይ የቆጠበ
  4. በአባልነት ቢያንስ ሁለት ወር የቆየ
  5. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ካለው ያለዋስትና መበደር ይችላል
  6. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ከሌለው (ካነሰ)፣ ከማኅበሩ አባል የሆነ አንድ ሰው ዋስ ማቅረብ አለበት ወይም ከውጪ የመንግሥት ሠራተኛ የሆነ ዋስ ማቅረብ ይገባዋል

መደበኛ ብድር፦ ከብር 20,000.00 - ብር 50,000.00 ድረስ

ብድሩን ለመበደር በቅድሚያ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
  1. በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚመለስ
  2. የአባልነት 5 (ዕጣ) አክሲዮን በሙሉ የገዛ
  3. የብድሩን 1/4 እና ከዚያ በላይ የቆጠበ
  4. በአባልነት ቢያንስ ሦስት ወር የቆየ
  5. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ካለው ያለዋስትና መበደር ይችላል
  6. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ከሌለው (ካነሰ)፣ ከማኅበሩ አባል የሆነ አንድ ሰው ዋስ ማቅረብ አለበት ወይም ከውጪ የመንግሥት ሠራተኛ የሆነ ዋስ ማቅረብ ይገባዋል። የመንግሥት ሠራተኛ ካልሆነ ከሚታወቁ የግል ድርጅቶች ሁለት ዋስ ማቅረብ አለበት

እንዲሁም ለተለያየ አገልግሎት ሊውል የሚችል ብድር፦ ከብር 50,000.00 - ብር 100,000.00) ድረስ የሚደርስ ብድር

ብድሩን ለመበደር በቅድሚያ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
  1. የአባልነት 5 (ዕጣ) አክሲዮን በሙሉ የገዛ
  2. ብድሩን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ መመለስ የሚችል
  3. የብድሩን 1/4 እና ከዚያ በላይ የቆጠበ
  4. በአባልነት ቢያንስ ሦስት ወር የቆየ
  5. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ካለው ያለዋስትና መበደር ይችላል
  6. አባሉ በማኅበሩ የገዛው ዕጣ እና ቁጠባ ተደምሮ የብድሩ መጠን 75% ያህል ከሌለው (ካነሰ)፣ ከማኅበሩ አባል የሆነ አንድ ሰው ዋስ ማቅረብ አለበት ወይም ከውጪ የመንግሥት ሠራተኛ የሆነ ዋስ ማቅረብ ይገባዋል። የመንግሥት ሠራተኛ ካልሆነ ከሚታወቁ የግል ድርጅቶች ሁለት ዋስ ማቅረብ አለበት።

ከአዲስ አበባ የቁጠባ እና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን ጋር ማኅበሩ ተባብሮ የሚያበድረው ብድር፦ እስከ ብር 500,000 ድረስ

በተጨማሪ የኅብረት ሥራ ማኅበሩ ከአዲስ አበባ የቁጠባ እና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን ጋር በመተባበር እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ድረስ መበደር የሚቻልበትን መንገድ አመቻችቷል። ከዩኒየኑ ጋር በትብብር የሚወሰድ ብድር በዩኒየኑ የብድር መመሪያ መሠረት የሚወሰድ ብድር ይሆናል።
 • የሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት መስጠት
 • የህይወት መድህን ዋስትና
 • የህይወት ክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠና
 • ስኬታማ የንግድ ሥራ አጀማመር እና አመራር ሥልጠና
 • በንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ደግሞ ሥራቸውን የሚያግዙ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ይሰጣል
 • በኅብረት ሥራ መርህ የሚያምንና ደጋፊ የሆነ
 • የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነ
 • በሕግ መብቱ ያልተገደበ (ያልተገፈፈ)
 • ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
 • ለኅብረት ሥራ መርሕና ለማኅበሩ የሕግ ደንብ ተገዢ መሆን የሚችል
 • የመመዝገቢያ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) መክፈል የሚችል

ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ አድራሻ እና ስልክ

 • የቢሮ አድራሻ፦ ካሳንቺስ፣ ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤ/ክ መንገድ፣ ሙሉጌታ ኮሜርሻል ሕንጻ፣ 5ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 501
 • ስልክ ቁጥር፦ +251 965 266526 | +251 964 654632
 • ቴሌግራም ቻነል፦ https://t.me/joinchat/VOv0DFeJ9i27t2nd
 • ኢሜይል አድራሻ፦ dsccaaltd@gmail.com
 • ፌስቡክ ገጽ፦ https://www.facebook.com/DebabeSaving
 • ባንክ አካውንት፦ ንግድ ባንክ - 1000365634819 | አቢሲኒያ ባንክ - 51283128

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …