መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 626/2001 መሠረት በአንድ መቶ ሚሊዮን ብር (ብር 100,000,000) ካፒታል የተቋቋመ የፋይናንስ ተቋም ነው። ተቋሙ በቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ኤልሳቢ በዋናነት የባንክ አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ማኅበረ ሰቦች (ጥቃቅን ሥራ ፈጣሪ እና አነስተኛ አርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ወዘተ) በዘላቂነት የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአፍሪካ ያሉ የባንክ ተጠቃሚ ላልሆኑ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ግንባር ቀደም የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ መሆን ነው

ተልዕኮ

በገጠርና በከተማ ለሚንቀሳቀሱ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሙሉ አዳዲስ ፈጠራን የሚያራምዱትን በቴክኖሎጂ የታገዘ ጠንካራ ቁጠባ መር መካከለኛ የፋይናንስ ተቋም በመሆን ማገልገል ነው፡፡

ዓላማ

የኤልሳቢ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. አጠቃላይ ዓላማዎች ለአነስተኛ የንግድ ተቋማት፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በኅብረተሰቡ ውስጥ ተገቢውን የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ለውጥ አስተዋፅዖ ማድረግ ነው።

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

 • የፍጆታ ብድር
 • የመኪና ብድር
 • የእርሻ ብድር
 • የማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ብድር
 • የግል ብድር
 • የውዴታ ቁጠባ
 • የግዜ ገደብ ቁጠባ
 • የተማሪዎች ቁጠባ
 • የህጻናት ቁጠባ
 • ተቀጣሪ ሠራተኛ ከሆነ ገቢውን የሚገልጽ ከሚሠራበት መሥርያ ቤት ወይም ድርጅት ደብዳቤ ማቅረብ
 • ነጋዴ ከሆነ የንግድ ፈቃድና የገቢና ወጪ መግለጫ ማቅረብ
 • ለብድሩ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ
 • የሕይወት መድን ዋስትና የሚከፍል
 • የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍል
 • የጋብቻ ሁኔታ የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚች፣ ባለትዳር ከሆኑ ሁለቱም በአካል የሚገኙ መሆን አለባቸው
 • የብድር ማመልከቻ በአካል ተገኝቶ በተዘጋጀው የማኅበሩ ብድር ማመልከች መሙላት
 1. የደመወዝ ዋስትና
 2. የንብረት ዋስትና (የመኪና ሊብሬ፣ የቤት ካርታ)
 3. የቡድን ዋስትና (በቡድን በመደራጀት ዋስትና መውሰድ)
 4. የቁጠባ (በሚወሰደው ብድር ተመጣጣኝ የሆነ የግዴታ ቁጠባ)

የብቃት መስፈርት በቡድን ለተደራጁ

 • አምራች እና በኅብረተ ሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው
 • በልዩ ሁኔታ ካልታየ በስተቀር ዕድሜው ከ19 – 65 ዓመት የሆነ
 • የአንድ ቀበሌ ቋሚ ነዋሪ የሆነና የቀበሌ መታወቂያ ሊያመጣ የሚችል ኢትዮጵያዊ
 • የቡድን ተጠያቂነት ለመቀበልና በቡድን ለመደራጀት ፈቃደኛ የሆነ
 • ከቀበሌ መስተዳደር የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል (ለገጠር ደንበኛ)

የብቃት መስፈርት ለንግድና የግል ብድር

 • ምርታማ ሥራ ላይ የተሰማራ
 • የደመወዝ ወይም የንብረት ዋስትና (የቤት ካርታና መኪና ሊብሬ) ማቅረብ የሚችል
 • የማንም ዕዳና ዋስትና የሌለበት፣ በኅብረተ ሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው
 • በልዩ ሁኔታ ከልታየ በስተቀር ዕድሜው ከ19 – 65 ዓመት የሆነ
 • የአንድ ቀበሌ ቋሚ ነዋሪ የሆነና የቀበሌ መታወቂያ ሊያመጣ የሚችል ኢትዮጵያዊ

የብቃት መስፈርት ለፍጆታ ብድር

 • ቋሚ ደመወዝተኛ የሆነ
 • ዕድሜው ከ18-50 ዓመት ሆኖ ለጡረታ ያልደረሰ
 • የአንድ ቀበሌ ቋሚ ነዋሪ የሆነና የቀበሌ መታወቂያ ሊያመጣ የሚችል ኢትዮጵያዊ
 • የማንም ዕዳና ዋስትና የሌለበት
 • ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው፣ በዕዳ ምክንያት ደመወዙ ያልተቆረጠና በፍርድ ቤት ያልተከሰሰ
 1. ለመደበኛ ብድር ከ 1 ዓመት - 2 ዓመት
 2. ለመኪና ብድር 5 ዓመት
 3. ለቤት ብድር 5 ዓመት

የሞባይል መተግበሪያ

የአንድሮይድ እና አይኦኤስ መተግበሪያ በመጠቀም አገልግሎት ማግኘት።

የበይነ መረብ (internet) አገልግሎት

ለመቆጠብ እና ብድር ለማመልከት በይነመረብ (internet) ላይ መጠቀም ይቻላል።

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

ከጃክሮስ አደባባይ ወደ ጎሮ መታጠፊያ 100 ሜትር ዝቅ ብሎ MDK ሕንጻ ፊት ለፊት።

ስልክ

 • +251 11 6675793
 • +251 903 800008
 • +251 902 800008

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …