መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የሮያሊቲ ክፍያ ለባህላዊ ወርቅ አምራቾች ሙሉ በሙሉ ተነሳላቸው
artisanal-miner

የሮያሊቲ ክፍያ ለባህላዊ ወርቅ አምራቾች ሙሉ በሙሉ ተነሳላቸው

በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ የሚያቀርቡ አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረው የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች መነሳቱ ተገለጸ።

ይህን የገለጹት የማዕድን እና የኢነርጂ ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በፌስቡክ ገጻቸው ነው፤ ውሳኔውንም የሚመሰገን ነው ያሉት ሚኒስትሩ አክለውም “ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር የሰጠነው ትኩረት ማሳያ ነው” ብለዋል።

የባህላዊ እና አነስተኛ ወርቅ አምራቾቻችን ለሀገራችን የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ዋልታ ሆነው ዘመናትን እያሻገሩን ይገኛሉ፤ እነሱን በተለያየ መንገድ መደገፍ እና ከትከሻቸው ላይ ጫናዎችን ማቃለል ከእኛ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ያሉት ሚኒስትሩ በሌላ መልኩ ደግሞ በህገወጥ መንገድ የሃገር ሀብት ላይ አሻጥር በሚሠሩት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ስምምነት እንደተደረሰ አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ በ2013 ዓም በጀት ዓመት ከወርቅ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ማግኘቷ ይታወሳል።

የዜና እና የምስል ምንጭ:- የታከለ ኡማ (ኢ/ር) የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …