መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ኑ ነገን ዛሬ እንሥራ – ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር
finot-logo

ኑ ነገን ዛሬ እንሥራ – ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ኅብረተ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባ ባህልን በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በ379 መስራች አባላት (307 ወንድ እና 72 ሴት) መጋቢት 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ።

ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

በ2018 ዓ.ም. ሃገር አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኅብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ማየት

ተልዕኮ

አባላትን በማስተባበር፣ ተገቢውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በፍላጎት ላይ የተመሰረተ በሀገራችን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ላይ አስተዋፅዖ በማበርከት ለአባላት የተሻለ የቁጠባ፣ የብድር እና ሌሎች የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ የኑሮ ደረጃውን ማሻሻል።

ዓላማ

  • ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም በመፍጠር ባንክ ነክ አገልግሎት መስጠት
  • አባላት በኅብረት ሥራ የማኅበራቸውን ገንዘብ እንዲቆጥቡ በማድረግ ኑኖአቸውን ማሻሻል
  • ለአባላት ፈጣን እና ምቹ በሆነ መንገድ ተገቢ የሆነ የወለድ ብድር አገልግሎት መስጠት
  • ኅብረተሰቡ የሚያገኘውን ገቢ በአግባቡ እንዲጠቀምበት ስለቁጠባ ባህል ትምህርት መስጠት
  • ኅብረተሰቡ ኋላቀር ከሆኑ እና ለብዝበዛ ከሚያጋልጡ አራጣ አበዳሪዎች ማላቀቅ

ጠቃሚ መረጃዎች ስለ ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

  1. የቁጠባ አገልግሎት
  2. በተመጣጣኝ ወለድ የብድር አገልግሎት መስጠት
  3. አነስተኛ የብድር መድኅን አገልግሎት
  4. የትምህርት፣ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት
  • የማኅበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ወይም ከ30 ቀናት ገቢ ውስጥ 10% ሲሆን ይህን ቁጠባ ሳያቋርጥ በየወሩ መቆጠብ ይኖርበታል።
  • እያንዳንዱ አባል ከመነሻ የቁጠባ መጠን በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል።
  • አንድ አባል የቆጠበውን መደበኛ ቁጠባ ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ይወስዳል። ነገር ግን ተጨማሪውን ወይም የፍላጎት ቁጠባውን አስገዳጅ በሆነ ጊዜ ወጪ አድርጎ መጠቀም ይችላል።
ተ.ቁየብድር ዓይነትየገንዘብ መጠን በብርብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በመቶኛብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በብርብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ ጊዜ በተከታታይየብድር ወለድ መጠንየብድር መመለሻ የጊዜ ገደብ
1ለማኅበራዊ ጉዳይ100 ሺህ25%25 ሺህ6 ወር እና ከዚያ በላይ13%3 ዓመት
2

ለትምህርትና ለጤና100 ሺህ25%25 ሺህ6 ወር እና ከዚያ በላይ13%3 ዓመት
3ለአነስተኛ ንግድ400 ሺህ25%100 ሺህ6 ወር እና ከዚያ በላይ13%3 ዓመት
4ለቤት እና ለመኪና ብድር600 ሺህ35%210 ሺህ1 ዓመት ከ 6 ወር 14%5 ዓመት
5ለንግድ መኪና ብድር800 ሺህ35%280 ሺህ1 ዓመት ከ 6 ወር14.5%7 ዓመት
6ለቤት ብድር፣ መግዣ፣ መሥሪያ፣ ማደሻ1 ሚሊዮን35%350 ሺህ1 ዓመት ከ 6 ወር15%10 ዓመት
  • አንድ አዲስ አባል የብድር አገልግሎት ለማግኘት ቢያንስ ለተከታታይ 6 ወራት መቆጠብ አለበት።
  • ለመኪና እና ለቤት ብድር ደግሞ ቢያንስ አንድ ዓመት ከ6 ወራት መቆጠብ አለበት
  • በተጨማሪም የገቢ መግለጫ፣
  • ተመጣጣኝ ዋስትና
  • የራሱም የዋሱንም የጋብቻን ሁኔታ የሚገልጽ የምስክር ወረቅት፣ ባል ወይም ሚስት በአካል ማቅረብ እንዲሁም ዋስም በአካል መቅረብ ይኖርበታል።
  • ተበዳሪው ከጠቅላላ ብድሩ 1% የብድር መድኅን እና 2% ደግሞ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል አለበት።
  • በቁጠባ ዋስትና
  • በደመወዝ ዋስትና እና በአባል ዋስትና
  • በንብረት ዋስትና የሚሰጥ ብድር
  • የመኪና ብድርና የቤት ብድር የሚገዛው ንብረት ራሱ ዋስትና ይሆናል
  • ማንኛውም ብድር የሚሰጠው የተበዳሪው የመክፈል አቅም ያገናዘበና ባቀረበው ዋስትና መጠን ብቻ ነው
  • በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ክልል ነዋሪ የሆነና የነዋሪነት ማረጋገጫ ያለው
  • ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በመሆን በኅብረት ሰርቶ በኅብረት ለማደግ ዓላማ ያለው
  • በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ደንብና መመሪያ ተገዢ ለመሆን ፈቃደኛ የሆነ/ች
  • በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
  • አንድ አመልካች አባል እንዲሆን ሲፈቀድለት የመመዝገቢያ ለአንድ ጊዜ ብቻ በመተዳደሪያ ደንቡ የተወሰውን የገንዘብ መጠን ይከፍላል።
  • ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ በስንብት ወቅት ለአባላት ተመላሽ አይሆንም።
  • የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1000.00 ሲሆን አንድ አባል መግዛት ያለበት ዝቅተኛ የዕጣ መጠን ሁለት ነው።
  • አንድ አባል በጠቅላላ ጉባኤ ተወካይ አባላት እንዲሸጥ ከተወሰነው የዕጣ መጠን ከ10 በመቶ በላይ ድርሻ ሊኖረው አይችልም።
  • በማኅበሩ የዕጣ እና ቁጠባ ምጥጥን መሰረት እንድ አባል በየጊዜው 1፡3 ዕጣ መግዛት ይጠበቅበታል።
  • ትምህርት ቤት መሄድ ያልቻሉ ህፃናትን የትምህርት ድጋፍ መስጠት
  • አረጋውያንና አቅመ ደካሞችን መርዳት
  • መጸዳጃ ቤቶችን በመገንባት ኅብረተ ሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ
  • የህክምና ድጋፍ ማድረግ
  • በሀገራዊ ልማቶችና በመንግሥት ድጋፍ ሲጠየቅ መሳተፍ
  • የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ
  • ችግኝ ተካላ
  • ለኮኖና ወረርሺኝ የድጋፍ ጥሪ ምላሽ መስጠት
  • ለሀገር መከላከያ ድጋፍ መስጠት

ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ አድራሻ

ተ.ቁአድራሻስልክ
1ዘነበወርቅ፦ እድገት በኅብረት የገበያ ማዕከል፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 013+251 113 694337
2መገናኛ፦ ገነት ኮሜርሻል 6ኛ ፎቅ+251 116 686577

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …