መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / የአብሮነት ተምሳሌት በተግባር – ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም

የአብሮነት ተምሳሌት በተግባር – ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም

ዮቶር በዋናነት በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባላት ንግዳቸውን የሚያንቀሳቅሱበት እና የሚያስፋፉበት እንዲሁም አብሮነታቸውን የሚያጠነክሩበት፤ ብሎም መካከለኛ የገንዘብ ዓቅም በማዳበር የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለማሟላት የሚውል የገንዘብ አቅርቦትን ለመፍጠር በሠለጠነ የሰው ኃይል እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ጠንካራ የኀብረት ሥራ ማኅበር በመፍጠር እስከ 2026 ዓ.ም ድረስ የአባላቱን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግር የሚቀረፉበት፤  በኅብረተ ሰቡ ዘንድ መተሳሰብ፣ አንድነት፣ ወንድማማችነት እንዲሁም ዘላቂነት ያለው ፍቅር የሚኖርበት የሚሆን ማኅበር እንዲሆን ታስቦ የተመሠረተ የአብሮነት ማኅበር ነው።

ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

አካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ዕሴቶቻችንን በመጠበቅ በ2026 የአባላትን የገቢ ደረጃ ከፍ በማድረግ መካከለኛ ገቢ ያላቸው አባላት ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ ሞዴል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር የኅብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ማየት

ተልዕኮ

አባላት አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ የሚችል በሠለጠነ የሰው ኃይልና ቴክኖሎጂ የተደገፈ ጠንካራ የኅብረት ሥራ ማኅበር በመፍጠር የቁጠባና ብድር ባህልን በማሳደግ የአባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ።

ዓላማ

ተበታትኖ የሚገኘውን የአባላት ገንዘብ በቁጠባ በማሰባሰብ ለብድር ማዘጋጀት፣ ባንክ ነክ አገልግሎት መስጠት፣ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ጠቀሜታ እና አገልግሎትን በመግለጽ የቁጠባ ባህል እንዲዳብር ማድረግ፤ አባላት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታ በጋራ ማመቻቸት እና በአካባቢ ልማት ተሳታፊ በመሆን እርስ በርስ የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ባህልን ማዳበር።

ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

 • እድሜው ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት
 • ከማኅበሩ አባላት ጋር አንድ ዓይነት ዓላማ እና አስተሳሰብ ያለው
 • በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ሠርቶ ለማደግ ፍላጎት ያለው
 • መብቱ በሕግ ያልተገደበ እና መልካም ስነ ምግባር ያለው
 • ዝቅተኛውን 10 ዕጣ በ2000 ብር መግዛት የሚችል
 • መመዝገቢያ 1000 ብር መክፈል የሚችል
 • ወርሃዊ ቁጠባ 350 ብር የሚቆጥብ

መደበኛ ቁጠባ

ሁሉም አባላት በኅብረት ሥራ ማኀበሩ ውስጥ አባል ሆነው እስቀጠሉ ድረስ መደበኛ ቁጠባቸውን ማቋረጥ አይችሉም። የመደበኛ ቁጠባ መጠን በጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነ ለሁኑም እኩል የሆነ 350 ብር ነው።

ለመኪና የሚቆጠብ ቁጠባ

መኪና መግዛት የሚፈልጉ አባላት የሚቆጥቡት የቁጠባ ዓይነት ነው።

የጊዜ ገደብ ቁጠባ

ለተወሰነ የጊዜ ገደብ ሲባል 7 በመቶ በላይ ወለድ የሚታሰብለት በስምምነት የሚቆጠብ እና በአስፈላጊ ጊዜ ወጭ ማድረግ የሚቻልበት የቁጠባ ዓይነት ነው።

የህጻናት የተቀማጭ ሂሳብ

ይህ የቁጠባ አይነት ለህጻናት የሚፈቀድ እና ቤተሰቦቻቸው ለተለያየ ተግባር ከሚሰጧቸው ገንዘብ ላይ ያስተረፉትን እና ለነገ ተስፋ የሚሆናቸውን ቁጠባ የሚለማመዱበት እንዲሁም የተሻለ ወለድ የሚታሰብለት የቁጠባ አይነት ነው።

ለቤት የሚቆጠብ

ቤት መግዛት የሚፈልጉ አባላት የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው።

መደበኛ ብድር

ይህ የብድር ዓይነት 3 (ሦስት) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 25% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና ቢያንስ 10 እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራውም እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺኅ ብር) ድረስ ነው። የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወራት (4 ዓመት) ድረስ ይሆናል።

የቤት ብድር

ቤት ለመግዛት የሚፈልጉ አባላት የሚበደሩት የብድር ዓይነት ሲሆን በተከታታይ ለ18  ወራት የሚበደረውን 30% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ የቤት ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው እስከ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) ሆኖ የመመለሻ ጊዜውም እስከ 72 ወራት (6 ዓመት) ድረስ ነው።

የመኪና ብድር

የግል መኪና መግዛት የሚፈልጉ አባላት የሚበደሩት የብድር ዓይነት ሲሆን ለ18 ወራት በተከታታይ የሚበደረውን 35% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ አባል የመኪና ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው እስከ  ሆኖ ከፍተኛ የመመለሻ ጊዜውም እስከ 72 ወራት (6 ዓመት) ድረስ ነው።

የንግድ መኪና መግዛት ለሚፈልጉ

የንግድ መኪና ለመግዛት የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን ለ12 ወራት በተከታታይ የሚበደረውን 35% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ የንግድ መኪና ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው እስከ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) ድረስ ሆኖ ከፍተኛ የመመለሻ ጊዜውም እስከ 60 ወራት (5 ዓመት) ድረስ ነው።

የኅብረት ብድር

ይህ የብድር ዓይነት ወንድሞች እና እህቶች (አባላት) በብረት ተሰባስበው ለአንድ ለተወሰነ ዓላማ ተደራጅተው የሚበደሩት እና ትርፍ የሚያገኙበት የብድር ዓይነት ነው። ይህ የብድር ዓይነት በተለይም ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን በማበረታታት ለወደፊት በኑሯቸው የተሻለ እንዲሠሩ ለማድረግ የሚበደሩት የብድር ዓይነት ነው።
አንድ ሰው ከማኅበሩ ብድር በሚበደርበት ጊዜ የግድ ዋስትና ማቅረብ አለበት። የሚቀርበው ዋስትናም እንደሚበደረው የብር መጠን የተለያየ ነው። በተጨማሪም የዋስትናው (የመያዣው) ንብረት ሽያጭ የብድሩን ዕዳ በሙሉ ለመሸፈን ያልቻለ እንደሆነ ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ቀሪውን ዕዳ ለማስከፈል ተበዳሪን ለመክሰስና የተበዳሪን ሌላ ንብረት አሳግዶ መሸጥ ይችላል። የሚከተሉት የንብረት አይነቶች ለዋስትና የሚሆኑ ናቸው፦

የደመወዝ ዋስትና

በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች የሚሠሩ ግለሰቦች የወር ደመወዛቸውን ለመደበኛ ቁጠባ ብቻ እንደ ዋስትና ተጠቅመው ብድር መውሰድ ይችላሉ። ተበዳሪዎች ከታች የተጠቀሱትን አጠቃላይ ማስረጃዎች በማሟላት ብድር መውሰድ ይችላሉ።
 1. የዋስ ስም
 2. የደመወዝ መጠን
 3. የሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ሥም
 4. የሥራ ድርሻ
 5. ስልክ ቁጥር

የመኪና ዋስትና

የመኪና ባለንብረቶች መኪናቸውን እንደ ዋስትና በመጠቀም የሚጠየቀውን መስፈርት በማሟላት ከማኀበሩ ብድር መውሰድ ይችላሉ።
 • ለብድር ዋስትና የሚሆነው መኪና ሙሉ ኢንሹራንስ ያለው መሆን አለበት
 • መኪናው ተፈትሾ ለብድር ዋስትናው ብቁ መሆን አለበት
 • የመኪናው ባለቤት ስም
 • የሰሌዳ ቁጥር
 • ሞዴል፣ የተሠራበት ዘመን፣ የሞተር ቁጥር፣ የሻንሲ ቁጥር
 • የመኪናው ዓይነት እና የመኪናው ባለቤት ስልክ ቁጥር መሟላት አለበት

የቤት ዋስትና

 • ለብድር ዋስትና የቀረበው ቤት ካርታና ፕላን ሊኖረው ይገባል
 • ግንባታውም በፕላኑ መሠረት መሠራት ይኖርበታል
 • ቤቱ የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ያስፈልገዋል
 • የቤቱ ባለቤቱ ስም
 • ቤቱ የሚገኝበት ከተማ
 • ቤቱ የሚገኝበት ክፍለ ከተማ
 • ቤቱ የሚገኝበት ልዩ ቦታ
 • የካርታ ቁጥር
 • የቦታ ስፋት በካሬ ሜትር
 • የብሎክ ቁጥር ያስፈልጋል
 • በግለሰብ ደረጃ ሊፈቱ የማይችሉ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት እንዲችሉ ያደርጋል
 • በመደበኛ የገንዘብ ተቋማት ማግኘት የማይቻል ብድርን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል
 • አባላት ለቆጠቡት ገንዘብ ከመደበኛ ባንኮች እኩል ወይንም ከዛ በላይ የወለድ መጠን ያገኛሉ
 • በየዓመቱ ከሚገኘው የተጣራ ትርፍ ለአባላት ባላቸው የዕጣ መጠን የትርፍ ክፍፍል ይደረጋል
 • የዕጣ ጣሪያ ገደቡ እስካልደረሰ ድረስ ዕጣ ያለ ገደብ ለማሳደግ ይቻላል
 • የትርፍ ክፍፍሉ ከሌሎች የገንዘብ ተቋማት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው
 • መደበኛ ገንዘብ የመቆጠብ ባህል ያሳድጋል
 • በዝቅተኛ ወለድ የብድር አገልግሎት ይሰጣል
 • አብሮ በመሥራት የሕይወት ተሞክሮ ማግኘት ያስችላል

ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም፦ የተቋሙ አድራሻ እና ስልክ

 • ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቅርንጫፍ፣ ሳምሶን አረጋኸኝ ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ስልክ 0944 448333
 • አማኑኤል መሳለሚያ ቅርንጫፍ፣ 1ኛ ፎቅ፣ ፎቅ በረንዳ የገበያ ማዕከል፣ ስልክ 0913 822414
 • ቅድስት ልደታ ቅርንጫፍ፣ ፌደራል ፍርድ ቤት ወደ ብስራተ ገብርኤል አቅጣጫ ዞር እንደትባለ ያለው ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣  ስልክ 093 0523409
 • መገናኛ አገናኝ ቅርንጫፍ፣ መተባበር ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ 316A፣ ስልክ 0920 444096

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበር ድረ ገጽ ላይ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …