መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ፍጹም፣ ሜላት እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረት ሥራ

ፍጹም፣ ሜላት እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ፍጹም ዘላለም እና ጓደኞቻቸው በ2013 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች በዋናነት የእንጨት ምርቶች ሲሆኑ በተጓዳኝ ደግሞ የብረት ሥራዎችንም ይሠራል።

ድርጅቱ የፈርኒቸር እቃዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሠራ የሚገኝ ሲሆን በይበልጥ ደግሞ በሶፋ እና ኪችን ካቢኔት እንዲሁም ቁም ሳጥን ላይ በብዛት እየሠራ ይገኛል።

ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል ዋጋ በጥቂቱ

  • ደረጃቸውን የጠበቁ ሶፋዎች፦ በብር 40,00o (አርባ ሺሕ ብር)
  • ደረጃቸውን የጠበቁ ለሆቴል እና መኖሪያ ቤት የሚሆኑ ቅንጡ አልጋዎች፦ ከብር 30,000 (ከሠላሳ ሺሕ ብር) እስከ ብር 40,00o (አርባ ሺሕ ብር)
  • ኪችን ካቢኔት፦ ይህ ደግሞ በደንበኛው ፍላጎት እና በሚመርጠው የጥሬ ዕቃ ጥራት ደረጃ ይወሰናል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ፍጹም ወደዚህ ሙያ ከመግባታቸው በፊት ትምህርታቸውን ጨርሰው መርካቶ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ውስጥ የሴልስ ሥራ እና የሱፐርቫይዘርነት ሥራ ሲሠሩ ቆይተዋል። የእንጨት ሥራ በትምህርት ቤት እያሉ የመሥራት ፍላጎት ስለነበራቸው በአጋጣሚ ሥራውን የሚሠራ ዘመድ ያጋጥማቸውና እረፍት ሲሆኑ እዛ በመሄድ መማር ይጀምራሉ። መሠረታዊ ልምዱን በደንብ ካዳበሩ በኋላ በዐምስት መሥራች አባላት እና በብር 50,000 (ሃምሳ ሺሕ ብር) ካፒታል (አሁን ካፒታሉ ብር ሦስት መቶ ሺሕ ብር ደርሷል) ድርጅቱን መሥርተዋል። አሁን ድርጅቱ አጠቃላይ የዐምስት ዓመት የሥራ ልምድ አለው።

ድርጅቱ በአንድ ወር ውስጥ ዐሥራ ዐምስት አልጋዎች እና ዐሥር ሶፋዎች የማምረት አቅም አለው። በዚህ ደግሞ ዘጠኝ ለሚጠጉ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። አቶ ፍጹም በሴልስ ሥራ የነበራቸው እውቀት ለድርጅቱ ሥራ ማግኘት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቅሰዋል። ይህም ድርጅቱ ሥራዎችን ለተለያዩ አቅራቢዎች ማቅረብ እንዲችል አስችሎታል። ከዚህም ውስጥ ተጠቃሾች ሚና ፈርኒቸር፣ ማጂቴክ ፈርኒቸር፣ ቢኤች ፈርኒቸር፣ ፍስሐ ፈርኒቸር እና ማፋ ፈርኒቸር ናቸው።

ድርጅቱ አሁን ላይ የገጠመው አስቸጋሪ ችግር የሠራተኛ አለመቆየት እና ሲለቁ ደግሞ የድርጅቱን ዲዛይን አብረው ይዘው ስለሚሄዱ ይህ ደግሞ እንደ በፊቱ ሥራዎችን በሰፊው እንዳይሠራ አድርጎታል። ይህ ማለት ድርጅቱ ለብቻው የሚሠራቸው እና የሚታወቅባቸው ዲዛይኖች በሌሎች ድርጅቶች ስለሚሠሩ ነው። ስለዚህ ይህን ችግር ለመቅረፍ ጥናት በማጥናት ላይ ይገኛል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በሰው በሰው፣ አቶ ፍጹም ራሳቸው ሄደው በሚያመጡት ገበያ፣ እንዲሁም ባዛር እና ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ነው። አሁን ደግሞ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም ወረዳ ሁለት ጨረታ ወስደው አሸንፈዋል። ጨረታዎች አመራረጥ ላይ የነበራቸውን ችግር በሚገባ በመረዳት አሁን የሚሆናቸውን ጨረታ አፈላለግ ስለተረዱ በሚገባ እየተጠቀሙት ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ማስታወቂያ ቴሌግራም ላይ ሞክረዋል፤ አሁን ደግሞ ቢዝነስ ካርድ እያሳተሙ ነው። እንደ አቶ ፍጹም አስተያየት ትልቅ ባዛሮች የተሻለ መሥራት ይቻላል፤ አሁን ትንሽ ባዛሮች ላይ ሥራ የለም። የፈርኒቸር ውጤቶች ሰው መግዛት ትቷል በብዛት የሚገዙት ዕቃዎች የባልትና ውጤቶች እና ቀለል ያሉ ምርቶች ናቸው ሲሉ ሃሳባቸውን አክለዋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ እና ዕቅድ

በኮቪድ ጊዜ ከባድ ሁኔታ ነበር በዚህም ይህም ለማለፍ ድርጅቱ ብድር ተበድሮ የነበረ ቢሆንም ሁኔታዎች ከባድ ስለነበሩ ሠራተኞችን ቀንሶ ለመሥራት ሞክሮ ነበር። ነገር ግን የግዢ ፍላጎት በመቀነሱ ገበያ ምንም ስላልነበር ሥራ በማቆም ነው ያሳለፈው።

ድርጅቱ ወደ ፊት ድርጅቱን የማስፋት እና ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ ዘመናዊ ማሽኖችን በማምጣት ሥራውን አዘምኖ ለመሥራት ዕቅድ አለው።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …