መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ሊቋቋም ነው
coffee-plant

በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ሊቋቋም ነው

ኤስ ኬ ፎረስት ኩባንያ የተባለው የደቡብ ኮሪያ የደን ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ለማቋቋም ከኮሪያ የደን አገልግሎት ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሠራ ነው።፡፡

ኩባንያው እሮብ ዕለት እንዳስታወቀው በደቡብ ኢትዮጵያ የአካባቢው ተፈጥሮ እንዲያገግም ለማድረግ 700,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ 70,000 የእጣን እና ሌሎች የዛፍ ችግኞችን ለመትከል አቅዷል፡፡ ለዚህም በቡና እርሻ ወስጥ በሚገኝ እና 10,000 ካሬ ሜትር በሚሸፍን ቦታ ላይ የዛፍ ችግኞች ማፍያ ለማልማት ዕቅድ ይዟል።

በተጨሪም በደን-ግብርና (agro-forestry) ልማት ቴክኖሎጂ ዘርፍ እና በሌሎች የደን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ለሃገር ውስጥ ባለሙያዎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ እንዳቀደ ገልጿል፡፡

ደን-ግብርና (agro-forestry) በአንዴ አፈሩ ሳይጎዳ የእርሻ፣ የከብት እርባታ እና የደን ልማትን ሥራ በማካሄድ የተለያዩ ምርቶች ማስገኘት ያስችላል።

በእርሻው ላይ የሚለማው ቡና በ ‘ፌየር ትሬድ’ በኩል ለደቡብ ኮሪያ ገበያ ይቀርባል ተብሏል።

ምንጭ፦  The Korea Biz Wire

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …