ፊውቸር ቴክ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ እንዳልካቸው እና በአራት ጓደኞቻቸው መሥራች አባልነት በ2010 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ሶፍትዌሮችን ለደንበኛው ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ዲዛይን ማድረግ እና ማበልጸግ እንዲሁም የማማከር አገልግሎት ይሰጣል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

የድርጅቱ መሥራቾች የሶፍትዌር ማበልጸግን ዘርፍ የመረጡት ሁሉም አባሎች ሙያው በጣም የሚያስደስታቸው በመሆኑ እና በዘርፉ በሀገራችን ብዙ ችግሮችን መቅረፍ የሚችሉ ሥራዎችን መሥራት እንደሚቻል ስለሚያምኑ ነው። እንዲሁም በዘርፉ የተማረ የሰው ሃይል አጥረት ስላለ ይህን ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ፊውቸር ቴክ ድርጅትን መሥርተዋል።

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች በዋናነት የአይቲ ሶሉሽን ሥራ ነው። ይህ ማለት ማንኛውም ድርጅት ሥራውን ለማከናውን የሚያስፈልጉትን ሶፍትዌሮች ማበልጸግ እና ሥልጠና መስጠትን ያካትታል። ለሌሎች ድርጅቶች ደግሞ ተያያዥ በሆኑ ሥራዎች ሥልጠና እና ግንዛቤ መስጠትን ይጨምራል።

softwareድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች እና የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የሶፍትዌር ዲዛይን እና ማበልጸግ ሥራ
  • የአይ ቲ ማማከር አገልግሎት
  • የአንድሮይድ እና አይፎን (iOS) ብሎም ሌሎች ስልኮች (ሀይብሪድ) አፕልኬሽኖች ማበልጸግ
  • ዌብሳይቶችን ደንበኛው እንደሚፈልገው ማበልጸግ እና
  • የሃርድዌር ጥገና አገልግሎት መስጠት

የድርጅቱ መሥራቾች የራሳቸው ፍላጎት እንዳለ ሆኖ ይህን ድርጅት የመፍጠር ሀሳቡ ግን የተወጠነው በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ትምህርት ምደባ ሲገኛኙ እንደሆነ አቶ አንዳልካቸው ገልጸዋል። አቶ እንዳልካቸው ትምህርቱን ሲጀምሩ ሆነ በትምህርት ላይ እያሉም ሥራውም ብዙ አቅም ስለማይጠይቅ የነበራቸውን ኮምፒውተሮች በመጠቀም ቀለል ያሉ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር። ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ቀጥታ ወደ ሥራ የገቡት፤ ሃምሌ ተመረቁ፣ መስከረም ሥራ ጀመሩ። ሥራውን በት/ቤት እያሉ ሲሠሩት ስለነበር አልከበዳቸውም። ከድርጅቱ ምሥረታ በኋላ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ። ለምሳሌ አውት ሶርስ የሚደረጉ ሶፍትዌሮች፣ ኢአርፒ (ERP) አይነት የሆኑ ትልቅ ፕሮጀክቶች፣ ሜትሪክስ የመሳሰሉ ሥራዎች ሠርተዋል። የድርጅቱ መሥራቾች ቢዝነሱን ለማስኬድ መሠረታዊ ክህሎቶችን ያዳበሩት በማንበብ እንደሆነ የድርጅቱ መሥራች ጠቅሰዋል።

ድርጅቱ የሚመጡ ሥራዎችን እንደ ፕሮጀክቱ አይነት ከሦስት ሳምንት እስከ ሦስት ወር የማጠናቀቅ አቅም አለው። ይህ ድርጅት ሥራዎች ሲኖሩ (እንደ ሥራዎቹ ዓይነት) ከስምንት ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

ፊውቸር ቴክ ለሚሠራቸው ሥራዎች የሚጠይቀው ዋጋ እንደ ፕሮጀክቱ ዓይነት ቢለያይም ከ60 ሺህ ብር ጀምሮ እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር ድረስ የሚአስከፍሉ ፕሮጀክቶችን በብዛት ተቀብሎ ይሠራል።ድርጅቱ እንደ አጠቃላይ በዓመት ሦስት ትልቅ ፕሮጀክቶንች በሚገባ ጥንቅቅ አድርጎ የመሥራት አቅም አለው።

ድርጅቱ ሲመሠረት እንደ ጀማሪ የአይቲ  ድርጅት ሥራ ማግኘት በጣም ከባድ ነበር። የድርጅቱ መሥራቾችም ራሳቸው በመነጋገር ፊልድ እየወጡ አገልግሎታችንን ሊፈልጉ ይችላሉ (potential customers) የሚሏቸውን ድርጅቶች በር በር በማናገር ነበር ሥራ ለማግኘት የሚሞክሩት። እንዲሁም 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ባዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት የገበያ ትስስር (ማስታወቂያ) እንዲሁም የጨረታ አገልግሎቶችን በመጠቀም አንዳንድ ሥራዎች በጨረታ እያሸነፉ እና በስልክም ቀጥታ እየተደወለላቸው እንዲሠሩ ረድቷቸዋል። እሳቸውም ጨረታ ለመጠቀም የሚያስብ ሰው የ2merkato.comን አገልግሎት እንዲጠቀ ይመክራሉ። አሁን ላይ ድርጅቱ ያለው አቋም ጥሩ ነው፤ የሚሠራቸው ሥራዎች ጥራትም ስለሚመሰክር ሰዎችም እየመጡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው።

ድርጅቱ እንደ ድርጅት በሶፍትዌር ሥራ ከሃርድዌር ሥራ የተሻለ ልምድ ስላለው የሃርድዌር ሥራን ቀነስ በማድረግ ብዙ የድርጅቱን ትኩረትና  ወደ ሶፍትዌር ሥራ አዙሯል።

ድርጅቱ በአሁን ጊዜ በሰዎች እየታወቀ ነው በስልክም እየተደወለ ሥራዎችን ይሠራል፤ እንደቴክ ካምፓኒ መቀጠሉ ራሱ ትልቅ ስኬት ነው። ይህ ድርጅት እስካሁን ወደ ስድስት የሚጠጉ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ አስረክቧል።

ለምሳሌ ያህል ሂውማን ሪሶርስ ማኔጅመንት ሲስተም ትልቅ ሲስተም ነው፤ ከባዮሜትሪክ (የእጅ አሻራ) አቴንዳንስ ተቀብሎ የሠራተኛ ፔይሮልsoftware-development የሚሠራ ሶፍትዌር አበልጽገዋል። ኮቴክስ የሚባል ሥራ የሁለት አመት ፕሮጀክት ይህንም ከመንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች (NGO’s) ጋር እየሠራ ይገኛል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ድርጅቱ ኮቪድ እንደተከሰት ባለው መጀመሪያ ጊዜ ላይ ሥራ ሙሉ በሙሉ አቁሞ ነበር። ቀስ በቀስ አንዳንድ የሶፍትዌር ሥራዎችን እና የማማከር አገልግሎቶችን ብቻ ከቤት በመሥራት ነው የኮቪድን ጊዜ ያሳለፉት።

ምክር እና እቅድ

ፊውቸር ቴክ ወደ ፊት የሚመጣውን ቴክኖሎጂ መቀበል የሚችል የሥራ ከባቢና የድርጅት አቅም መፍጠር ትልቅ እቅዱ ነው። ድርጅቱ በሥራው የሚታወቅ ትልቅ የቴክ ካምፓኒ በመሆን በትምህርት፣ በፋይናንስ እና ቢዝነስ ላይ በሀገራችን ውስጥ ጠቃሚ የሆነ ለውጥ የሚያመጣ ድርጅት የመሆን እቅድ አለው።

ወደ ዘርፉ መሠማራት ለሚፈልጉ ሰዎች “አይቲ ጎበዝ ስለሆኑ ብቻ  ውጤታማ መሆን ከባድ ነው፤ ስለዚህ ነግሮችን ከሥር መሠርታቸው ጥርት አድርገው ማሰብ መቻል አለባቸው። ሀሳቡ ወርዶ ለአንድ ችግር መፍትሔ ማምጣት የሚችል መሆን አለበት እንጂ አንድ ሰው ኮድ ማድረግ ስለቻለ ብቻ ቢገባ ውጤታማ ላይሆን ይችላል። ማርኬቲንግ መታወቅ አለበት። የምሠራው ሥራ በእርግጥ ችግር ይቀርፋል ወይ? የሚለው መታወቅ አለበት። እነዚህን ነገሮች ይዞ ቢገባ ይመረጣል” ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም ለሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …