መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ቢንያም፣ አብዩ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ቢንያም፣ አብዩ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አብዩ ጌታቸው እና አራት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም. ሲሆን አጠቃላይ የእንጨት እና የብረታ ብረት ሥራዎችን ይሠራል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች

  • አጠቃላይ የቤት እና የቢሮ እቃዎች
  • የብረት ከንቾች
  • የኪችን ሳከሮች
  • ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የሻተር ሥራዎች እና
  • የብረት በር እንዲሁም መስኮት ሥራዎችን ይሠራል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ አብዩ ወደ እንጨት ሥራ የገቡት ለሙያው በነበራቸው ፍቅር እንደሆነ ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ሰላም ቮኬሽናል መንደር ኮሌጅ ገብተው ሙያውን ተምረዋል። ተምረው ሲጨርሱም በሙያውም ለአራት ዓመት ተቀጥረው ሠርተዋል። ከአራት ዓመት በኋላ ራሳችንን እናሳድግ በማለት ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ድርጅቱን መሠረቱ።

ድርጅቱ ሲመሠረት በዋናነት የሚሠራቸው ሥራዎችን የነበሩት የቤት እና የቢሮ እቃዎች ነበሩ። አሁን ግን አቅሙን በማሳደግ በስፋት የኪችን ሳከሮችን እየሠራ ይገኛል (ከሌሎች ከተጓዳኝ ሥራዎች ጋር)። ድርጅቱ አሁን ባለው አቅም በአንድ በወር 100 (አንድ መቶ) አልጋዎች የማምረት አቅም አለው። ኪችን ካቢኔት እና ቁምሳጥን የሚፈጀው ጊዜ እንደ ሥራው ዓይነት እና መጠን የሚወሰን ይሆናል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው ሰው በሰው ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከመንግሥት ጋር አንዳንድ ሥራዎችን ሠርቷል። አቶ አብዩ ባላቸው ተሞክሮ የመንግሥት ሥራ መሥራት አስቸጋሪ ነው ይላሉ። ይህም ድርጅቱ ብዙ ገንዘብ ስለሌለው የመንግሥት ሥራ ለመሥራት ደግሞ ሥራውን ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ነው ገንዘብ የሚሠጠው። እንዲህ ሆኖ ራሱ ብዙ ጊዜ ይፈጃል። የግለሰብ ሥራ ግን አንድ ወይም ሁለት ሰው ስለሆነ የሚወስነው ቀላል ያደርገዋል. በተጨማሪ ደግሞ የግለሰብ ሥራ ላይ ቀብድ ተቀብሎ ቀጥታ ሥራ መሥራት ይቻላል። ስለዚህ ድርጅቱ በተቻለው መጠን የግል (የመንግሥት ያልሆኑ) ሥራዎችን ነው የሚሠራው።

ድርጅቱ ካጠናቀቃቸው ሥራዎች መካከል

  • አራት ኪሎ የሚገኘው የብልጽግና ቢሮ የኪችን ሥራ
  • ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ዘጠነኛ ፎቅ የባር ሥራ
  • መንገድ ፈንድ የውጭ አጥር ሥራ እና የባልኮኒዎችን ሥራዎችን ሠርቷል

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች ዋጋ

  • ቁም ሳጥን አንድ ሜትር ከሃያ፦ ብር 15,000 (ዐሥራ ዐምስት ሺህ ብር)
  • አልጋ፦ ከብር 15,000 (አሥራ አምስት ሺህ) ብር ጀምሮ እስከ ብር 30,000 (ሠላሳ ሺህ ብር) ድረስ
  • ኪችን ካቢኔት ደግሞ በካሬ ሲሆን የሚሠራው ይህም በካሬ ከብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር) ጀምሮ እስከ ብር 15,000 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ድረስ
  • የቴሌቪዥን ማስቀመጫ ከብር 8,000 (ብር ስምንት ሺህ) ጀምሮ እስከ ብር 12,000 (አሥራ ሁለት ሺህ ብር)  ድረስ ይሠራል

ድርጅቱ ለዐምስት ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠር የቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሲመሠረት ከነበረው ብር 100,000 (መቶ ሺህ ብር) ካፒታል አሁን ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሻ ሺህ ብር) ደርሷል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮቪድ ጊዜ በአዘቦት ቀን የሚሠራ ሥራ ምንም አልነበረም። ስለሆነም የማስተር ካርድ የኮቪድ ማገገሚያ ብድር በመበደር እና በጊዜው በነበረው የፀጥታ ችግር ለደህንነት ብለው የሻተር ሥራ በመኖሪያ ቤታቸው የሚያሠሩ ሰዎች ስለነበሩ የሻተር ሥራ በመሥራት ነው የኮቪድ ጊዜን ድርጅቱ ያሳለፈው።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ አሁን ባለው የሥራ ቦታ ጥበት ሥራውን በስፋት መሥራት አልቻለም። ስለዚህ የግለሰብም ቦታ ቢሆን ተከራይቶ ሥራውን የማስፋት እና የምርት ማሳያ ሱቅ የመክፈት እቅድ አለው።

 

አቶ አብዩ ወደ እንጨት እና ብረት ሥራ የሚገባ ሰው ፍላጎት እና ተነሳሽነት ሊኖረው ይገባል። ሁለቱ ካሉ ውጤታማ መሆን ይችላል ሲሉ ምክራቸውን አክለዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …